Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
NBC ታለንት ሾው እጅግ አጓጊ የባለ ተሰጥዖ ድምፃዊያን እና የውዝዋዜ ውድድር!

የሙዚቃ ጠበብቶች ይዳኙታል ፤ አለም የደረሰበትን የመጨረሻ የድምፅ ጥራት በያዘ ዘመናዊ ባንድ ይታጀባል።

ለ17 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ውድድር ተሰጥዖዎን ያሳዩ ፤ አጓጊ ሽልማቶችን ያሸንፉ!

@nbcethiopiatalentshow የቴሌግራም ግሩፕ ናሙና ስራችሁን እና አድራሻችሁን በመላክ መወዳደር ይችላሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"Power Hour" የተሰኘ ሳምንታዊ የልምድ ልውውጥ እና የ ግንኙነት መድረክ በ ድንቅ ቲቪ ተዘጋጅቶ በዚህ ሳምንት እሮብ ቦሌ ርዋንዳ በሚገኘው የቀስተ ዳመና ሾው ሩም ውስጥ ከ አመሻሹ 12:00 ሰአት ጀምሮ ይካሄዳል።

በዝግጅቱም ላይ በመዝናኛ እና በሚዲያው ዘርፍ ትልቅ ቦታ የደረሱ እንግዶች የሚጋበዙበት ሲሆን እርሶም ለመመዝገብ
events@dinktv.com ላይ አድራሻዎን ይላኩ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የ8 ሺህ ብሩ ኮንሰርት ተሰረዘ

#waliya_entertainment : የመግቢያው ዋጋው 8,000 ብር የነበረው በስካይላይት ሆቴል ትላንት ምሽት ሊካሄድ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ተሰረዘ

ትላንት ምሽት የፈረንጆቹን አዲስ አመት ዋዜማ በማስመልከት አርቲስት ሚካኤል በላይነህ፣ አብርሃም ገ/ መድህን እና ሳሚ ዳን በመድረክ ይዘፍኑበታል የተባለው በስካላይት ሆቴል ሊካሄድ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ተሰርዟል።

እንደ ሆቴሉ ገለፃ ከሆነ የኮንሰርቱ መሰረዝ ምክንያት አዘጋጁ መራ ኢቭንት ኮንሰርቱን በሰአቱ ለማከናወን ፍቃድ ባለማግኘቱ ነው ብሏል።

ሆቴሉ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ጠይቋል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የትላንት ምሽቱ ኮንሰርት ለምን ተሰረዘ ?

አብርሃም ገ/መድህንን ከሳሚ ዳን እና ሚካኤል በላይነህ ጋር አጣምሮ ሊቀርብ የነበረው ኮንሰርት መሰረዙ የታወቀው ሊቀርብ ጥቂት ሰዐታት እየቀሩት ነው ።

በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል ተብሎ ቢጠበቅም አልተካሄደም ። ትክክለኛው መረጃ ግን እስካሁን ይፈሠ አልሆነም ።

ስካይ ላይት ሆቴል ኮንሰርቱ እንዲካሄድ መሟላት ያለባቸው ፍቃዶች እስከመጨረሻው ሰዐት እጄላይ አልቀረበም በመሆኑም አዳራሹን ከልክያለሁ ነው ያለው ።
የኮንሰርቱ አዘጋጅ ሜራ ኢቭንት አቢሲንያ ገብረእግዚአብሔር የተፈጠረው ነገር ያልተጠበቀ መሆኑን በገፅ ላይ ተጠቅሷል ። ይሁን እና ያ ያልተጠበቀው ነገር ምን እንደሆነ አያብራራም ። ይሁን እና ትኬት የገዙ ገንዘባቸው እንደሚመለስላቸው ያትታል ።

አብርሃም ገብረመድህን አዲስ አበባ ላይ ኮንሰርት ካቀረበ 4 አመታት አልፈዋል ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
#Sami-Dan #AbyssiniaGebregziabher
#meraEvents #SkyLightHotel Ethiopia
“የማዲንጎ አፈወርቅ አዲስ ስራዎችን የሚመርጥ እና የሚያሰባስብ ኮሚቴ ተዋቅሯል"
አቻሬ(የድምፃዊው የቅርብ ወዳጅ)

የተወዳጁ ድምፃዊ የማዲንጎ አፈወርቅ አዲስ አልበም በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ተነገሯል::

ድምፃዊው በሕይወት ሳለ የሰራቸውን የሙዚቃ ስራዎች የመምረጥ እና የማሰባሰብ ስራን የሚያከናውኑ ኮሚቴዎች መዋቀራቸውን የድምፃዊው ወዳጅ ቸርነት አሸናፊ (አቻሬ ጫማ) ተናግሯል።

በእዚህ ኮሚቴ ውስጥም አንጋፋው የሙዚቃ ባለሙያ ዘዓለም መኩሪያ፣ ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎን ጨምሮ የማዲንጎ አፈወርቅ ቤተሰቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል።

በእዚሁ አልበም ስራ ላይም እስከ 10 የሚደርሱ የሙዚቃ ስራዎች እንደሚካተቱም ቸርነት አሸናፊ (አቻሬ) አንስቷል።

በግጥምና ዜማ ሂደት ውስጥ ከእዚህ ቀደም ከድምፃዊው ጋር የሰሩ ባለሙያዎች እንዳሉበት የተናገረው አቻሬ የባለሞያዎቹን ስም ዝርዝር ከመጥቀስ ተቆጥቧል::

በሌላ በኩል ደግሞ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከድምፃዊው የቅርብ ምንጮች ባደረገው ማጣራት የአልበም ስራው ከ50 እስከ 60 በመቶ ሊጠናቀቅ ችሏል።

ከእዚህ ቀደም የክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ ፣ የድምፃዊ እዮብ መኮንን፣ ሚካያ በሀይሉ እና ሀጫሉ ሁንዴሳ የአልበም ስራዎች ከህልፈተ ሕይወታቸው በኋላ ለሙዚቃ አፍቃሪያን እንደደረሱ ይታወሳል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Madingo
በ 2023 በዩቲዩብ ላይ በደንብ የታዩ ምርጥ 10 የአፍሪካ ሙዚቃዎች.

1. People - 240 million views — Libianca
🇨🇲
2. Ekhtayaraty - 134 million views  — Ahmed Saad 🇪🇬
3. Ader Akmel - 125 million views  — Ahmed Saad 🇪🇬
4. Who Is Your Guy Remix - 114 million views — Spyro ft. Tiwa Savage  🇳🇬
5. Casanova  - 109 million views —  Soolking ft. Gazo 🇩🇿 🇫🇷
6. Water - 92 million views — Tyla 🇿🇦
7. Unavailable  - 83 million views — Davido ft. Musa Keys 🇳🇬 🇿🇦
8. This Year - 64 million views — Victor Thompson ft. This D Greatest 🇳🇬
9. Come Baby Come - 63 million views —
Mohamed Ramadan & Skales 🇪🇬 🇳🇬
10. Charm - 61 million views — Rema 🇳🇬

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ከ5 ቀናት በላይ ሳታቋርጥ ያዜመችው ጋናዊት

#Waliya_Entertainemnt : አፉዋ አሳንቴዋ ኡዉሱ አዱዎነም የተባለች ጋናዊት ዘፋኝ የዓለም ክብረ-ወሠን ለመስበር ከአምስት ቀናት በላይ ያለማቋረጥ ማዜሟ ተነግሯል፡፡

አፉዋ አሳንቴዋ “ሲንግ ኤ ቶን” በሚል ርዕስ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና ዋና ከተማ አክራ ያለማቋረጥ መዝፈን የጀመረችው በፈረንጆቹ የገና በዓል ዋዜማ መሆኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ሀገርኛ ዜማዋን ለ126 ሠዓታት እና 52 ደቂቃዎች ለታዳሚዎቿ ካቀረበች በኋላ ባሳለፍነው ዐርብ ማጠናቀቋም ነው የተመላከተው፡፡

በመርሐ-ግብሩ የቀድሞውን የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ፣ የአሁኑን ምክትል ፕሬዚዳንት ማሃማዱ ባዉሚያ ጨምሮ በርካታ ጋናዊያን ተገኝተው የሚያስደንቅ ድጋፍ ሲያደርጉላት እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ጋናዊቷ ዘፋኝ ÷ ለ105 ሠዓታት ባለማቋረጥ በመዝፈኑ የዓለም ክብረ-ወሠን ይዞ የቆየውን ሱኒል ዋግሜር የተባለ ሕንዳዊ ሙዚቀኛ ከመንበሩ እንዳወረደችውም ነው የተነገረው፡፡

ሕንዳዊው ሙዚቀኛ ሱኒል በጋናዊቷ አፉዋ አሳንቴዋ በ21 ሠዓታት እስኪበለጥ ድረስ ክብረ ወሰኑን ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ ይዞ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡

ጊነስ ወርልድ ሬከርድስ በፌስ ቡክ ገጹ የደረሰውን መረጃ ተከትሎ ምላሽ መስጠቱም ነው የተገለጸው፡፡

የዓለም ድንቃ ድንቅ ሁነቶችን የሚመዘግበው ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ዳኞቹ ትክክለኛ መረጃ እንዳገኙ ጋናዊቷ ዘፋኝ አፉዋ አሳንቴዋ በትክክል የግለሰቡን ክብረ-ወሰን ሰብራለች ወይም አልሰበረችም የሚለውን የሚወስን ይሆናልም ብሏል፡፡

Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
https://www.t.me/waliyaentmt
« ይለያል » የድምፃዊ ቴዎድሮስ አስፋ (ቴዲ ዮ) አልበም ለገበያ ሊቀርብ ነው።

#Waliya_Entertainemnt | ድምፃዊ ቴዎድሮስ አስፋ(ቴዲ ዮ) ከዞጃክ ወርልድ ዋይድ ጋር በመተባበር « ይለያል » የተሰኘውን እና ሦስተኛ አልበሙን ወደ ሕዝብ ለማድረስ አለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ የሙዚቃ አልበም አሰናድቶ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን እና በቀጣይ ሳምንት ለአድማጭ ተመልካች እንደሚደርስ ድምጻዊው በዛሬ እለት በማርዮት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቋል።

አዲሱ የሙዚቃ አልበሙ 10 ሙዚቃዎችን አካቶ የቀረበው ሲሆን በዚህ የሙዚቃ አልበም በአጃቢነት ላይ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል ፣ ካስማሰ ፣ ቃል ኪዳን ፣ ኩል ሱሬ እና እዮቤድ ተሳትፈውበታል።

በአይስ እና በአማዞን ላይ በቀጣይ ጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም በይፋ የሚለቀቀው አዲሱ የድምፃዊ አርቲስት ቴዎድሮስ አስፋ (ቴዲ ዮ) አልበም ስራዎች ውስጥ ሦስቱ የቪዲዮ ክሊኘ እንዳለው ድምጻዊው የገለጸ ሲሆን በቅንብር እና በሚክሲንግ ስራ ላይ ቢግ ባድ ሳውድ ተሳትፈውበቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddyo
🥰1👏1
"እየመጣ ነው"

#Waliya_Entertainemnt : በእናትዋ ጎንደር እና በካሲናው ጎጃም የምናውቀው ተወዳጁ አስቻለው ፈጠነ "አስቻለ" የተሰኜው አልበሙን ጥር 3/2016 ዓ/ም ለአድናቂዎቹ ሊያደርስ መሆኑን አርቲሥቱ ተናገረ።

"አስቻለ ከተማ ገባና፤ አስቻለ ምዘፍን ነኝ አለና፤
አምበለበላት ክራሪቱን፤ ይኼው ከእናንተ ፊት ቆመና።"

አስቻለው ፈጠነ
ጥር 3/2016 ዓ.ም.
ሁሌም አዲስ እሳቤ‼️ ሁሌም አዲስ እይታ‼️

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #enatwa_gonder
👍1
ዬሃና ሳህሌ እና አብይ ኦስማን በዚህ ሳምንት አርብ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በማሪዬት ሆቴል (አይቪ ላውንጅ) እናንተን በ RnB እና በ Soul ሙዚቃዎች ለማዝናናት ተዘጋጅተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Music_Events #Waliya_Entertainemnt #Music
ይምጡና ከኛ ጋር ይዝናኑ ያክብሩ!
ዛሬ ሃሙስ አመሻሽ ላይ ልዩ የሆነውን የ ገና የጃዝ ዝግጅት በ @atomosphere251 ከማራኪ ኢትዮ-ጃዝ ሙዚቀኞች ጋር ያክብሩ።

ዝግጅቱ ዛሬ ማታ 1:30 ላይ ይጀምራል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Music_event #Waliya_Entertainemnt #Music