Waliya Entertainment
287 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ከሰባት ሀገራት የተውጣጡ ሙዚቀኞች የተሳተፉበት "የደጋ ሰው" የተሰኘ አልበም ሊመረቅ ነው ተባለ
*********
*
የሙዚቃ ባለሙያው ሰርፀ ፍሬስብሀት "የእውነት የሙዚቃ ረሀብ ያለበት፣ ትክክለኛ ሙዚቃ ላዳምጥ ብሎ የሚመኝ ሰው፣ ከረጅም ዓመታት በኋላ ያገኘው ልዩ አልበም ይሄ ነው ብዬ አስባለሁ" ብለዋል።

አልበሙ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት በዛሬው እለት በተሰጠ መግለጫ ተነግሯል።

ድምፃዊት የማርያም ቸርነት(የማ) "የደጋ ሰው" በሚል መጠሪያ የተጫወተችው ይህ አልበም የፊታችን ቅዳሜ ታኅሣሥ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ይመረቃል ተብሏል፡፡

በዚህ አልበም የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ኢዩኤል መንግሥቱ በቅንብር፣ በዝግጅት፣በዜማ እና በግጥም ድርሰት መሳተፋቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም አንጋፋው የዘፈን ግጥም ደራሲ ይልማ ገብረአብና ጎላ ጎሕ በግጥም ድርሰት ተሳትፈውበታል ተብሏል፡፡ "የደጋ ሰው" አልበም፣ በሥነጽሑፋዊ ደረጃቸው የላቁ የዘፈን ግጥሞች፣ ለነፍስ በሚቀርቡ ዜማዎች ተቀንብበው በልዩ ጥንቃቄ የተሰሩ ሙዚቃዎችን አካቷል ተብሏል።

በሙዚቃ ስራው ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ከጊኒ ቢሳዎ፣ ከፖርቹጋል፣ ከኖርዌይ፣ ከቤልጂየም፣ ከኔዘርለንድስ እና ከብሪታኒያ የተውጣጡ የሙዚቃ ጠበብቶች ተሳትፈውበታል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
ዛሬ የምርጥ ድምፃዊ ፣ ገጣሚ እና ዜማ ደራሲ የሆነው የእሱባለው ይታየው ልደት ነው።
🎂🎂Happy Birthday🎂🎂

ከእሱቤ ስራዎች የቱን ትወዱታላችሁ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Esubalewu_yitayewu #Album  #Waliya_Entertainemnt
🎉1
ካሳሁን ገርማሞ (የቴዲ አፍሮ አባት) እና ፖሊስ

- ካሳሁን እጅግ ከተዋጣላቸው የመድረክ አስተዋዋቂዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡

- በፖሊስ ኦርኬስትራ ዝናው ጣራ የነካ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዘፈን ግጥሞችን ዜማዎችን ይደርስም ነበር፡፡

- ካሳሁን በ1939 ዓመተ-ምህረት በአዲስ-አበባ ከተማ ተክለሃይማኖት አካባቢ ነው የተወለደው።

- ቤተሰቦቹ በልጅነቱ ሲዳማ ውስጥ በምትገኘው ተፈሪ ኬላ ከተማ ይዘውት ሄዱ፡፡

- በዚያም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በተፈሪ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀመረ፡፡

- በኃላም ቤተሰቦቹ ወደ ተወለደባት አዲስ አበባ ተመልሰው የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በተስፋ-ኮከብ የሕዝብ ትምህርት ቤት ቀጠለ።

- ሚኒስትሪ በጥሩ ውጤት በማለፍም በወቅቱ፦"ልዑል-መኮንን" በኃላም፦"አዲስ-ከተማ" ከተባለው ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃውን ትምህርቱን ተከታትሏል።

- ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በታህሣሥ ወር 1961 ዓ.ም በፖሊስ-ሠራዊት ሙዚቃና ቴአትር ክፍል በመድረክ አጋፋሪነት ተቀጥሮ ሥራውን ጀመረ።

- የካሳሁን ግጥም እና ዜማ ከተጫወቱ መካከል ‹‹ሒሩት በቀለ፤ ታደለ በቀለ፤ በሃይሉ እሸቴ እና ተስፋዬ በላይ›› ይጠቀሳሉ፡፡

- ካሳሁን ግርማሞ ጋዜጠኛም ጭምር ነበረ፡፡ የፖሊስና ህብረተሰብ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ለበርካታ አመታት ሰርቷል፡፡

በተሾመ ብርሃኑ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Teddy_afro
1
በትናንትናው ለት የተካሄደው ኦዳ አዋርድ ላይ የተነሱ ፎቶዎች በጥቂቱ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Oda_Award
7ተኛው የኦዳ አዋርድ ሽልማት ተካሄደ።

በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ላይ ያሉ ባለሞያዎችን በማወዳደር የሚሸልመው "ኦዳ አዋርድ" ሰባተኛ ዙር የሽልማት መርሃ ግብሩን በስካይ ላይት ሆቴል ያከናወነ ሲሆን በዚህም መርሃ ግብር የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትንም ለመጀመሪያ  ጊዜ እንዳሳተፈ ተገልጿል።

በሙዚቃ ዘርፍ  የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ የኬኦል ናጋሳ "Jamare" ፤ የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ ሚፍታ ኑሩ፤ የአመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊት ፋክስ አኒያ፤ የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ጥምረት ከድር አህመድ እና ማርጊቱ ወርቅነህ፤ የአመቱ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ ነፃነት ሱልጣን፤ በአመቱ ብዙ የተደመጠ አርቲስት- ታዳለ ገመቹ ሆነዋል።

እንዲሁም የህይወት ዘመን ተሸላሚ አርቲስት ሻንታም ዳንሰር፣ አርቲስት ሙሀሙድ አህመድ፣ አርቲስት መሀመድ ሲርጋጋ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

በመጽሀፍ ዘርፍ፦ምርጥ የግጥም መፅሃፍ - የኤባዋቅ ግዛቸው፤ የአመቱ ምርጥ የልብወለድ መፅሃፍ - የሂካ ለማ ሆነዋል።

የምስራቅ አፍሪካ ተሸላሚዎች ፦ ሳህራ - ከሶማሌ ላንድ ፤ አብዱልቃድር ካሚል መሀመድ - ከጅቡቲ ፤ የመሽሩም ቡድን - ከኬንያ ፤ ኬኒ ሶል - ከሩዋንዳ ፤ኬኔት ሙጋቤ - ከኡጋንዳ ፤ ማኪ ሃጂ - ከሶማሊያ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

የሽልማቱ አካል እንዲሆኑ የተመረጡ የምስራቅ አፍሪካ አገራት  ኤርትራ፣ ሶማልያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሌላንድና ዩጋንዳ ናቸው፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt
👍1
የዳግማዊት ፀሀዬ "ወርቅ" አዲስ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ማታ 12 ሰአት ላይ ለአድማጭ ሊቀርብ ነው::

ድምፃዊቷ "ወርቅ" የሚል ስያሜ በሰጠችው በእዚህ የአልበም ስራ በፕሮዲውሰርነት እንዲሁም በአቀናባሪነት ትልቁን ተሳትፎ ከማድረግ አንፃር የሙዚቃ ባለሙያው አቤል ጳውሎስ ከፍ ያለ ሚና መወጣቱን ለ ዋልያ ኢንተርቴይመንት የገለፀች ሲሆን በርካታ ባለሙያዎች በተካፈሉበት በእዚህ የአልበም ስራ ውስጥ ለትዳር አጋሯ አርቲስት ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ) ያቀነቀችው ሙዚቃ እንዳለበትም አያይዛ አንስታለች።

አልበሙ ዛሬ ማታ (አርብ ታህሳስ 12 ቀን 2016ዓ.ም) በሁሉም አማራጮች እና መተግበሪያዎች በኢትዮጵያ እንዲሁም በተቀረው አለም እንደሚሰራጭ አስታውቃለች።

የስቱዲዮ ቁጥር ማነስ እና የባለሙያዎች እጥረት አልበሙ ፈጥኖ እንዳያልቅ ምክንያት ሆኗል የምትለው ድምፃዊቷ መቆየቱ ግን የተሻለ ስራ እንድሰራ አድርጎኛል ስትል ተናግራለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Dagimawit_tsehaye #werk_album
👍1