Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ቴዲ አፍሮ ሲሆን ፖለቲካውም ፣ ሀይማኖቱም ለሚታያችሁ !
" ቀና ካልክ ይተኩሱብሀል ! " ይላል ጋሽ ስብሐት ገእግዚአብሔር

ሰሞኑን የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ ) በእስራኤል ለአድናቂዎቹ ስራውን ማቅረቡን ተከትሎ ጉዳዩን የሀይማኖት ቅርጽ አስይዘው እንዲሰርዝ የሚጠይቅ ጽሑፍ አያየሁ ። እነዚህ የሀይማኖቱ ወገንተኞች ናቸው ። በቀደም ደግሞ ይኸው ድምጻዊ በእንግሊዝ ስራውን ሊያቀርብ ሲል ጥቂት የተደራጁ ብሔረተኞች እንዲሁ ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል ። እነዚህ ሰዎች ሌሎች ድምጻውያን እንግሊዝም ፣ እስራኤልም ሄደው ስራቸውን ሲያቀርቡ ያላነሱትን ጥያቄ ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ለምን እንደሚታያቸው ምክንያቱ ግልጽ ነው ። የድምጻዊው ጎላ ብሎ መታየት እሱን መቃወም የሀይማኖታቸውንም ፣ ብሔራቸውንም አጀንዳ ጎላ ስለሚያደስግላቸው ነው ። ቀና ስላለ ነው የሚተኩሱበት ። ጋሽ ስብሐት ይህን ነው የሚለው ። እስራኤል በፍልስጤም ላይ ላደረሰችው ቴዲ አፍሮ ተጠያቂ የሚሆነው እንዴት ነው ?

ካሁን ቀደም ( በቅርቡም ) እስራኤል በርካታ ድምጻውያን ሄደው ስራቸውን ሲያቀርቡ ምንም ትንፍሽ ብለው የማያውቁትን ጥያቄ ቴዲ አፍሮ ሲሆን የሚያነሱት ለምን ነው ? ለእስልምና ጭራሽ አብዱ ኪያር አይቀርብም ? እሱም እኮ እዚያው እስራኤል ሄዶ ስራውን አቅርቧል ፤ ነገም ቢጠራ ይሄዳል ። ስራ ነዋ ። እንግሊዝ ሄዶ ስራውን ያቀረበ አማርኛ ድምጻዊስ ቴዲ አፍሮ ብቻ ነው ? ( የእንግሊዞቹን እንኳን ራሱ ሰዉ መልስ ሰጥቷቸዋል ። ) እነዚህ ሰዎች የሚዘነጉት ሙዚቃ ለድምጻዊው ተሰጥዖው ብቻ ሳይሆን ስራው ፣ ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበት ብቸኛ ገቢው መሆኑን ነው ። ቤት ኪራዩን የሚከፍልበት ፣ ሲገዛ የሚገዛበት ፣ የተቸገረ ሲገኝ የሚያግዝበት ብቸኛ ገቢው ሙዚቃ ነው ። እሱን ነው " ዝጋ " የሚሉት ።
እነዚህ ሰዎች ማንም ላይ ምንም ሲደርስ መርካቶ ወይም መንደር ውስጥ ያለውን መደብራቸውን ይዘጋሉ ? " በእኔ ወገኖች ላይ በደል ስለደረሰ " ብለው ከመ/ቤት ይቀራሉ ? ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ ? መብላታቸውን ይተዋሉ ? ሰርግ ሳይሄዱ ይቀራሉ ? ልጃቸውን አይድሩም ? የትኛውን ገቢያቸውን ይተዋሉ ? ከሕይወታቸው ላይ ምን ይቀንሳሉ ? እነዚህ ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከእራኤል መንግሥት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲያቋርጥ ለምን መሬት አንቀጥቅጥ ሰልፍ አይጠሩም ? ሰዎች ለምን ወደ እስራኤል ወይም እንግሊዝ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲሰርዙ አያደርጉም ? ለምን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል ወይም እንግሊዝ የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ አላደረጉም ? አንዱንም አልሞከሩም ። ሌላ ቀርቶ ድምጻውያን እስራኤል ሄደው ሲዘፍኑ ማንም ምንም አይልም ። ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ምንድነው የሚታያቸው ? ኧረ ጎበዝ !

Via ቴዎድሮስ ተክላረጋይ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Teddyafro
የሙዚቃው ንጉስ ድምጻዊ ጥላሁን ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ዛሬ 16 ዓመት ሞላው።

መስቀል አደባባይ በነበረው ሽኝት መርሀ ግብር ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎችና አድናቂዎቹ መገኘታቸው የሚታወስ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Tilahungessese
በእስራኤል የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ዝግጅት

አቦጊዳ ባንድ በእስራኤል ቴል አቪቭ ከተማ “
April 30 2025 “ ለሚካሄደው የቴዲ አፍሮ
የሙዚቃ ዝግጅት ወደ ስፍራው አቅንተዋል::

📷Henok Henry
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddyafro #abogidaband
አርቲስት ዳግማዊት ፀሐዬ በፌስቡክ ገጿ እንደገለጸችው "አድናን ሱልጣን" የተባለ ግለሰብ "ለምን አታናግሪኝም" በሚል ሰበብ እኔን ለማሳገት እየዛተብኝ ጉዳዩን ወደ ህግ እስክወስደው እወቁልኝ ብላለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #dagimawit_tsehay
ታዋቂ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮች በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ይፋለማሉ

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከቅዳሜ ሚዲያ እና አድሽርታይዚንግ ጋር በመተባበር ልዩ የሆነ የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለጸ።

በዚህ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ድምፃውያን እና ቲክቶከሮች የሚሳተፉበት የእግር ኳስ ውድድር የፊታችን ሚያዚያ 23 እና ሚያዚያ 26 በልደታ በሚገኘው ብሪሞ ሜዳ ይካሄዳል።

የቅዳሜ ሚዲያ እና አድሽርታይዚንግ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ አዳረ ረጋሳ ይህንን መርሃ ግብር አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት " ከዚህ ቀደም መሰል ውድድሮች በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት የነበራቸው ሲሆን ዘንድሮም ይህንን የአብሮነት እና የመዝናኛ ጊዜ ለመፍጠር ታስቧል።

አክለውም በቅርብ ጊዜያት ህዝቡ በቤተሰቡ ልጆቹን ይዞ ወደ መዝናኛ እና ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች በስፋት እየሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ በእነዚህ ቦታዎች ላይ አዝናኝ ፕሮግራሞች ቢዘጋጁ ህዝቡ በሰፊው እንደሚታደም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ይህ የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫልም በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ በመሆኑ ብዙዎች በጉጉት እንደሚጠብቁት "ተናግረዋል።

በመግለጫው ላይ እንደተገለጸው ሚያዚያ 23 የዋንጫ ማለፍ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን የፍጻሜው የዋንጫ ጨዋታ ደግሞ ሚያዚያ 26 ይካሄዳል። ከዚህ የትኬት ሽያጭ የሚገኘው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ ይውላል።

@waliyaentmt
@waliyaemtmt
@waliyaentmt
እኔንም ስሙኝ ብሏል :-

እኔ አድናናን እባላለው ባለትዳር እና የሴት ልጅ አባት ነኝ::

ዳግማዊ ደቡብ አፍሪካ በነበርኩ ግዜ ጏደኛዬ ነበረች የባሏ ቤተሰቦች እና የባሏ የድሮ ፍቅረኛ የሚያደርጏትን ጭምር ታጫውተኝ ነበር:: ከዛ ለረዥም ግዜ ተለያይተን በድጋሚ ፃፍኩላት ይሄ ዛቻ ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ እኔ ለቀልድ ነው ያልኳት እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም እኔ የምኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም::

አድናን ነኝ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #dagimawittsehaye #adnan