Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
"የተሰበሰበው ገንዘብ ለአርቲስቱ አልተሰጠም" አዘጋጅ ኮሚቴው
"ስሜን ለማጥፋት ነው" ዲጄ ቤቢ

የአርቲስት ዓለማየሁ ደመቀን የ25 ዓመታት የኪነጥበብ ቆይታና አገልግሎት ለማክበርና አርቲስቱን ለማመስገን ዮቶር በሚል ርዕስ ሰኔ 15/2016 ዓ.ም የሙዚቃ ኮንሰርት በማርዮት ሆቴል አዳራሽ መከናወኑ ይታወቃል፡፡

በዝግጅቱ የተገኙ ገቢዎች የስፖንሰርሺፕ ገቢ፣ የቲኬት ገቢና ሌሎችም ገቢዎች ሂሳብ ተሰርቶ ርክክብ ባለመደረጉ በተደጋጋሚ ሂሳብ ተሰርቶ የአርቲስቱ ድርሻ ገቢ እንዲደረግለት ጥያቄ ቢቀርብም በተለያዩ ምክንያቶች ዲጄ ቤቢ መገኘት ባለመቻሉ ጉዳዩ እልባት ማግኘት አልቻለም ሲሉ ኮሚቴዎቹ ቅሬታውን በደብዳቤ ለሚዲያዎች ገልፀው ነበር።

ጉዳዩን አስመልክቶ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ለማጣራት እንደሞከረው ዲጄ ቤቢን አነጋግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል ደብዳቤው ቀድሞ ተልኮልኝ አይቼዋለሁ ያለው ዲጄ ቤቢ እንደአጋጣሚ ሆኖ አሜሪካን ሀገር በላስ ቬጋስ ከተማ በተዘጋጀው የአለም የሬዲዮና ቴሌቪዥን ብሮድካስተሮች ማህበር ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ አሜሪካ ሀገር ሄጃለሁ እሱን አጋጣሚ በመጠቀም "ሸሸ" በማለት ስም ለማጥፋት የተደረገ ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው፣ ሙሉ በሙሉ ውሸት ነው! ጉዳዩን ወደ ህግ ወስጄዋለሁ ብሏል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #djbaby #alemayehudemeke
" ልዑል ኮንሰርት ቱር "በ ሶስት ከተሞች የሙዚቃ ድግስ ሊያዘጋጅ ነው!

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በዘመናዊ ሙዚቃ በመጀመሪያ አልበም ከፍተኛ ተወዳጅነት እና ተቀባይነት ያገኘው ልዑል ሲሳይ በፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ እና ሸጋ ኢቬንትስ እና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የሙዚቃ ቱር "የልኡል ሙዚቃ"ቱር በሚል ስያሜ ይከናወናል ተባለ።

ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ "ልዑል'' ሲል በሰየመው የመጀመሪያ አልበሙ ውሰጥ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ስልተ-ምቶችን ጨምሮ ሬጌና ፖፕ ስልቶችን አካቶ መምጣቱ ይታወሳል።

ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ በሚሊኒም አደራሽ የመጀመርያ ኮንሰርቱን ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የፊታችን ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም ቅዳሜ ምሽት በጊዮን ሆቴል ስራዎቹን ከአዲስ ሙዚቃዎች ጋር በማካተት ለየት ባለ አቀራረብ ከአደናቂዎቹ ጋር ለመገናኘት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በዕለቱ በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙት ስካት ናቲ፣ሃና ግርማ እና ዊሃ በዝግጅቱ ላይ ስራዎቻቸውን በቶራ ባንድ ታጅበዉ ያቀርባሉ፡፡

በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የተዘጋጀው ኮንሰርት እንደተጠናቀቀ በሀዋሳ ግንቦት 2/ 2017 ዓ.ም እንዲሁም በድሬዳዋ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም ሌሎች ድምፃዊያንን በማካተት የኮንሰርት ቱር ይካሄዳል፡፡

አዘጋጆቹ እንደገለጹት ሦስቱም የኮንሰርቶች ላይ በአጠቃላይ ከ 22 ሺህ በላይ ተመልካች ይጠበቃል፡፡

በሶስቱ ኮንሰርቶች ቀድሞ ለሚገዙ ውስን የሚሆኑ ትኬቶችን በ400 ብር መደበኛ 600 በዕለቱ በር ላይ 800 ቪአይፒ 2500 ብር ሲሆን ትኬቱን መግዛት የሚቻለው በቴሌ ብር ብቻ መሆኑ ተነግሯል ::

Follow us on
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music