Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ተወዳጇ ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ ስለ ሞዴል ቀነኒ አዱኛ

ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ በሞዴል ቀነኒ አዱኛ ላይ የሚከተለውን ሃሳብ አስፍራለች «የሆነን ሰው ባውቀው ኖሮ ብላችሁ ተመኝታችሁ ታውቃላችሁ? ቀነኒን ባወኳት ኖሮ!» በማለት ሃሳቧን የጀመረችው ቬሮኒካ ክለብ በምትሰራበት ወቅት እና በኮንሰርት ላይ እንደተገናኙ ትገልጻለች «ክለብ በምሰራበት እና ለኮንሰርት ሁለት ጊዜ አግኝቻት አውቃለሁ Backstage ስለነበርን normal ሰላምታ አይቀርም የሆነ ጊዜ ግን ከመቀመጫዬ ተነስቼ አቀፍኳት እና በጣም እንደምታምር ነግሪያት ወደ stage ሄድኩ የዛን ለት ምናለ ባወራዋት? ይሄ ጥያቄ ሰሞኑን የሚለቀቁት ፎቶዎች ባየው ቁጥር ይመጣብኛል አሁን እንዲ ማለቴ ምንም ጥቅም የለውም ግን በቀነኒ ምክንያት እየታመምን ነው። በጣም!» ስትል ሃሳቧን አስፍራለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Veronica_adane #keneni
"ውጤት አልደረሰልኝም" ፖሊስ

በቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ ዛሬ ቀጠሮ የነበረ ሲሆን በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በነበረው ችሎት የፖሊስ የምርመራ ውጤት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ፖሊስ የ15 ሰዎች መረጃ ማሰባሰቡን ገልጾ የፌድራል ፖሊስ ፎረንሲክ የምርመራ ውጤቶቹ አሁንም አልደረሱኝም በማለት 14 ቀን ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል።

የአንዱዓለም ጠበቃ በበኩሉ የቀነኒ ዲያሪ እሱ ጋር እንዳለ ጠቅሶ ቀነኒ ሯሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ መድኃኒት ወስዳ እንደነበር ተፅፎ አግኝቻለሁ ብሏል።

ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መፈቀድ የለበትም አንዱዓለም የዋስ መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል ብሎ ተከራክሯል። በተጨማሪም ከእስር ወጥቶ የሙዚቃ ስራውን ለፋሲካ ያቅርብ የሚለው የዩቲዩብ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሊታረም ይገባል ብሏል።

ፍርድ ቤት የሁለቱን ክርክር ከሰማ በኋላ የክርክሩን ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ማክሰኞ ጠዋት ቀጥሮ ሰጥቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #andualemgossa #keneni