Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
❣️ የሶል ንግሥት አስቴር አወቀ
የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በሙዚቃ ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች 🇺🇸

#Ethiopia | የኢትዮጵያን ሙዚቃ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ አድማጮች ጋር እንዲደርስ በማስቻል ፈር-ቀዳጅ በመሆንሽ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ልባዊ ደስታውን በመግለፅ እንኳን ደስ አለሽ ይላል ።

በአፍሪካ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ለፈጠርሽው ከፍተኛ ተፅእኖና በዓለም አቀፍ ደረጃ ወጣቱን ትውለድ በማነቃቃት ያደረግሽው አርዓያነት ይህንን እውቅና እንድታገኚ አድርጓል።

እ. ኤ.አ ጥቅምት 13 ቀን 2024 በሚደረገው የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ይህ እውቅናና ሽልማት ተበርክቶልሻል።

የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ስነ ስርአት ሜሪላንድ በሚገኘውና ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል ዛሬ፣ እሁድ ኦክቶበር 13/2024 ምሽት በደማቅ ዝግጅት እተካሄደ ነው።

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን ያዘጋጀው የ2024 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር የሽልማት ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።

ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የተዘጋጀ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #aster_aweke
ዳዊት ጽጌን ጨምሮ የሙያ ባልደረቦቹ በአሜሪካ እውቅና ተሰጣቸው

#Ethiopia | ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የሙዚቃ አቀናባራው አበጋዝ ሺዎታ እና ፕሮሞተር ሰለሞን ገብረማሪያም (ኪንግ ሶሎን )ጨምሮ በሲያትል ከተማ እውቅና ተሰጣቸው ።

ደዊት ፅጌ በ2024 በአሜሪካን ከተሞች ያቀረባቸው የተሳኩ ዝግጅቶች በማስመልከት እና ልዩ ተስጦ ያለው ድምፃዊ በመሆኑ ለሙዚቃው ላበረከተው አስተዋፆ ጭምር እውቅና አግኝቷል።

የሙዚቃ አቅናባሪው አበጋዝ ሺዎታ በኢትዮጵያ የምርጥ ሙዚቃ አቀናባሪ በመሆኑ እና ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲሁ እውቅና በክብር ተሰጥቷቸዋል።

በተያያዘ ዜና - የኪንግ ሶሎ ፕሮሞሽን ባለቤት ፕሮሞተር ሰለሞን ላለፉት 10 ዓመት በሲያትል ውስጥ በርካታ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት እውቅና ተሰጥቶታል። ( City of Seattle • Office of the Mayor) የሲያትል ከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት ቢሮ እውቅናውን የሰጠ ሲሆን ምክትል ከቲባዋም (Adiam Emery ) በዝግጅቱ ላይ በመገኘት የእውቅና ሰርተፍኬቱን አበርክተው አድናቆታቸውን ለተሸላሚዎቹ ገልጸዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሃያላኑዋ አሜሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ከሚንቅሳቅስባቸው ዋንኛዋ ከተማ የሆነው ሲያትል ዋሽግተን ምክትል ከቲባዋ መሆናቸው ለኢትዮጵያን ትልቅ ኩራት መሆኑ ተግልጿል።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #dawit_tsige