ኦላን ይዤ አላፍርም ይህንን አውቃለሁ
ወደ ፍቅር ልሂድ ምን እጠብቃለሁ?
#Ethiopia | ግፎችን መዘንጋት ቀላል አይደለም። በደልን በበደል ከማወራረድ ይልቅ በደልን ሆን ብሎ መተው እንደ ምላስ ጂምናስቲክ ቀለል ያለ የቃላት ጥምዛዜ አይደለም። የቃላት ወገብን እንደማሠራት ቀሊል አይደለም። ለምጣዱ ሲባል አይጧን ለማሳለፍ፥ የምጣዱን ዋጋ ማወቅ ይፈልጋል። አይጧ በነባር ጥፋቷ ያልተቀጣችው፥ የትክክለኛነት ካባ አስደርቧት እንዳልሆነ የሚያውጠነጥን እሳቤ ይፈልጋል። ይህ እሳቤ ሊሰርጽ የሚሞከረው፥ ለአይጧ እና የቅጣት በትር ለጨበጠው አካል ነው። ዱላ ተይዞ ከአይጧ ሞት በላይ የምጣዱ ሕልው እንደሚልቅ ማሰብ ደግሞ እጅግ በጣም አዳጋች ነው። እንኳን “በደል ያሰለለው የተገዘገዘ አንጀት” ተሸክሞ ይቅርና እንዲያው ያለምንም ምክንያት መዶሻ የያዘ ሰው ሚስማሩን ለመሰመር እጁን ይከረክረዋል።
ፈረንሳዊው ሊቅ ሬኒ፦ "ሰዎች ሀገር ለመገንባት ከፈለጉ በታሪክ ውስጥ የተፈፀሙ አንዳንድ ግፎችን ለመርሳት ዝግጁ መሆን አለባቸው" ይላል። ለመርሳት መሞከር ደግሞ ሁነኛ የማስታወስ መንገድ ስለሆነ ግፎችን መርሳት ይበልጡኑ የማይቻል ያደርገዋል። ይህንን ተቃርኖ ማረቅ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው። ለተበዳዩ የመበደሉን ዕውቅና መስጠት የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው። ፍቅር ራሱ የበደል ካሳ ነው።
#ወደ ፍቅር ጉዞ
©ቢኒያም አበራ
Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent
#Ethiopia #waliya_entertainment #teddy_afro