Waliya Entertainment
290 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
September 13, 2024
September 14, 2024
ይህ ቃል በጊዜው ከሰጡት ውስጥ አንዱ ተስፋዬ ሳህሉ "አባባ ተስፋዬ " ነበሩ ። እሳቸውም ለአዲስ አመት የእንቁጣጣሽ አበባ ስለው በየሹማምንቱ ቤት በማዞር ሀምሳ ብር ይሰበስቡና ወዴት ነህ የሚለው ጥያቄ እንዳያስጨንቃቸው ሆን ብለው ብርድ ልብስ ቀደው ላሰፋ ነው ።  በሚል ሰበብ ከቤት ይወጣኑ ከአንድ ጣልያናዊ ሹፌር ጋር ተነጋግረው በትሬንታ ኳትሮል ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ ።

አጠያይቀውም ቃል የገቡላቸውን ሰዎች ያገኙና በአስራ አራት አመታቸው የሙዚቃ ትምህርታቸውን ይጀምራል ። ከትምህርታቸው ጋር አንድ ላይ ማደርያና የኪስ ገንዘብ ጭምር ይሰጣቸው ነበር ።  በወቅቱ ከእሳቸው ጋር አብረው ከነበሩት ሙዚቀኞች መሀል የሳክስፎኑ ንጉሥ ጌታቸው መኩሪያ አንዱ ናቸው ። ስድስት አመት በዚህ ሁኔታ ካሳለፉ በኋላ የጃንሆይ  25ኛ የብር ኢዩቤልዩ በአል ምክንያት በማደረግ የአሁኑ ብሄራዊ ቴአትር የቀድሞ ቀ. ኃ.ስ ቴአትር ቤት ሲቁቋም ከተመረጡት አስራ ሶስት ሙዚቀኞች መካከል አንዱ በመሆን መስራች ሆኑ ።

በአርመናዊው አስተማሪና አለቃቸው ሙሴ ነርሲስ በምግባራቸውም ሆነ በትምህርት አቀባበላቸው የሚደነቁት አርቲስት መርዓዊ ከሙሴ ነርሲስ ህልፈት በኋላ የሙዚቃ ክፍሉን ተረክበው ለሰላሳ አመታት በአለቃነት አገልግለዋል። በዚህም ወቅት ለአርቲስት ምኒልክ ወስናቸው ፣  ለመልካሙ ተበጀ  ፣ ጠለላ ከበደ ፣ ፍቅርተ ደሳለኝ . . .  ለበርካቶች ግጥምና ዜማ ደርሰዋል ። ሙዚቃ አቀናብረዋል ። ከነዚህም ውስጥ የምኒልክ ወስናቸው የእንጆሪ ፍሬ፣ ትዝታ አያረጅም፣ስኳር ስኳር፣ አፈር አትንፈጊኝ፣ በምድረ ሱዳን ያለሽው ፣ ጥቁሯ ጽጌረዳ፣ የመልካሙ ተበጀ፣ ብእር ብእር ፣ ሰላም ጤና ይስጥልኝ፣ ንቢቱ፣ የፍቅርተ ደሳለኝ ልማት ልማት ሌሎችም ይገኙበታል ።

ከዚህም ባሻገር ከ200 የማያንሱ አብዮታዊ  መዝሙሮችን፣ ለሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እና ለሌሎችም በርካታ ታዋቂ ቴአትሮች ማጀቢያ ሙዚቃዎችን ደርሰዋል ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብም የመጀመርያ የሆነውን የክለቡን መዝሙር የሰሩት አርቲስት መርዓዊ ስጦት ናቸው ።  በአፄ ኃይለስላሴ ፣ በዘመነ ደርግ እና በዘመነ ኢህዲግ ጊዜ በተሰራው የኢትይጵያ ህዝብ መዝሙር ላይ የጋሽ መርዓዊ ትንፋሽ ተቀርጿል! ዜማው በሚሰራበት ጊዜም ኦርኬስትራውን የመምራትና የማስተባበር ስራውን የሰረት ጋሽ መራዊ ስጦት ናቸው ። 

በሙያው All Black People Music Festival ጨምሮ በናይጄሪያ ፣  በግብጽ በሱዳን ፣ በቻይና በራሺያ ፣ በአሜሪካ እና ሌሎችም ሀገራት ሀገሩን ወክሎ ተሳትፈዋል ። በአሜሪካ ሀገርም ከሙዚቀኛ ያሬድ ተፈራ ጋር በመሆን አምባሰልና ትዝታ ለትውልድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲተላለፍ በካሴትና በሲዲ አስቀረጸዋል  ። ለዚህና መሰል አስተዋጽኦ በተለያዩ ጊዜያት ሽልማትን አግኝተዋል ።

★ ከጃንሆይ የማበረታቻና የመጻህፍት ሽልማት

★ በደርግ ጊዜ በማስታውቂያ ሚኒስትር የምስጉን ሰራተኛ ወርቅ ተሸላሚ።

★ የአለም አቀፍ ጎልድ ሜርኩሪ ሽልማት (ሽልማቱ አለማቀፋዊና ትላልቅ የአለም መሪዎችን ጨምሮ ሳይንቲስቶችና ምሁራን የሚሸለሙት ነው )

★ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር  የወርቅ ሽልማት

★ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ማህበር የክብር ሽልማት ።

★ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር (ባህል ማዕከል) የክብር ዋንጫ ተሸላሚ።

★ ከጠ/ሚ አብይ አህመድ የክብር ሜዳሊያ ሽልማት ጥቆቶቹ ናቸው።

ጋሽ መርዓዊ ጡረታም ከወጡም በኋላ ከሙዚቃው ሳይርቁ እስከ ቅርብ ጊዜ ከብሄራዊ ቴአትር ደጅ አይጠፋም ። የልብ ህመም አጋጥሞቸው የትንፋሽ መሳሪያ መጫወት እስከተከለከሉበት ጊዜ ድረስ ክላርኔታቸውን ይዞው መገኘት ባለባቸው ቦታ ሁሉ እየተገኙ ህዝብን ያስደስቱ ነበር ። በህይወታቸው ከኦርኬስትራው ተነጥለው በየትኛውም ምሽት ክለብ ሰርተው አያውቁም  ። በተሰጥኦ ያምናሉ ። አዳዲስ ወጣቶች በመጡም ጊዜ ካሉበት አድኖ በማግኘት እና በማበረታታት ይታወቃሉ።  

አርቲስት መርዓዊ ስጦት ባላቸው ጊዜ ሁሉ ባለተሰጦ ልጆች በማደን ችሎታቸውን እያደነቁ ፣  እየመከሩ የሚያበረታቱና ምን አይነት አርቲስት መሆን እንዳለባቸው ምሳሌ  በመሆን ጭምር የሚደግፍ የሙያ አባትም ጭምር ናቸው ! ለዚህም "የአለም አቀፍ ሜርኩሪ" ሽልማታቸው ወጣት ባለሙያዎች ባዩት ጊዜ እንዲበረታቱበትና እንዱነሳሱበት በማሰብ በስጦታ መልክ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ዋና ስራ አስኪያጅ ቢሮ እንዲቀመጥ አስረክበዋል ።

ሆኖም የኢትዮጵያ የሚዚቃ ወርቃማ ዘመን ባለውለታ አርቲስት መርዓዊ ስጦት ለዘመናት የኖሩበት መኖሪያ ቤት በቅርቡ ሊፈርስ እንደሆነ ተነግሯቸዋል ። ሆኖም 40/60 ኮንዶሚኒየም ምዝገባ በነበረበት ወቅት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተመዝግበው ሙሉ ክፍያ ፈፅመው ቤቱ ያልተሰጣቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ የሚመለከተው አካል ጋር በተደጋጋሚ አቤት ቢሉ ሰሚ አጥተው እጅጉን አዝነው ይገኛሉ ።

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበር ፣ የኢትዮጵያ ባህል እና እስፓርት ሚኒስትር ለእኚ ባለውለታ ለሀገር የዋሉትን ውለታ ተመልክቶ ለከፈሉት ክፍያ ተገቢውን ምላሽ ከከተማ መስተዳደሩ ያገኙ ዘንድ ጥሪ ለማስተላለፍ እወዳለሁ !

ባለውለታን ማክበር ነገ ባለውለታ ዜጋን ማፈራት ነውና ባለውለቶቻችንን እናክብር !!!

ታሪኩ ዘውዱ
ከካናዳ 🇨🇦

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
September 14, 2024
September 14, 2024
September 14, 2024
September 15, 2024
September 15, 2024
September 18, 2024
September 19, 2024
September 20, 2024
September 22, 2024
September 23, 2024
September 23, 2024
September 23, 2024