Waliya Entertainment
295 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
6 ሚሊየን ብር የወጣበት የቬሮኒካ አዳነ አዲሱ አልበም መውጫ ቀኑ ተራዘመ።

🛑 በህጻን ሔቨን ላይ የደረሰውን ጥቃት ድምጻዊቷ አውግዛለች።

#Ethiopia | ኪነት ኢንተርቴመንት የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ መጠሪያዬ የተሰኘው የመጀመሪያ አልበም በቀጣይ ሳምንት እንደሚለቀቅ በዛሬው እለት በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።

ይህ መጠሪያዬ የተሰኘው አልበም በግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ 4 ሙዚቃዎችን ፤አቡዲ ያሲን ሰባት ሙዚቃዎችን እና ሱራፌል የሺጥላ አንድ ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ የተሳተፉ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር ታምሩ አማረ ፣አዲስ ፍቃዱ ፣አብርሃም ኪዳኔ ሮቤል ፣ እንዳለ በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሰለሞን ሀ/ማሪያም ስርተውታል፡፡

መጠሪያዬ አልበም 12 ሙዚቃዎች ያሉት ሲሆን አልበሙን ስርቶ ለማጠናቀቅ 3 ዓመት ፈጅቷል አልበሙ ላይ ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች በአሜሪካ አትላንታ ተሰርተዋል፡፡

ይህ አልበም አጠቃላይ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ሲሆን የአልበሙ ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲዩስ የተደረገ ሲሆን አልበሙን በማኔጅመንት ኪነት ኢንተርቴይመንት ማኔጅ አደርጎቷል፡፡

ይህ መጠሪያዬ አልበም ብዙ የተደከመበት እና የተለፋት አልበም ስለፍቅር ስለሰላም ስለሀገር ስለተስፋ እና ስለምስጋና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ይዳስሳል ።

ይህ አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተሰኘ አለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ ጋር በ160,000 ዶላር በመላው አለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር ተስማምተዋል።
በኢትዮጵያ ብር አስራ ሰባት ሚሊየን ብር በላይ ሲሆን ይህም ክፍያ በኢትዮጵያ አልበም ክፍያ ታሪክ ትልቁ ክፍያ እንደሚያደርገው በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።

ዞጃክ ወርልድ ዋይድ መቀመጫውን በአሜሪካ ፍሎሪዳ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ አለማት ማለትም ሜክሲኮ ፣ ኢንዶኒዢያ ፣ ጀማይካ እና ኬንያ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ይህ ካምፓኒ የኢትዮጵያን አልበም ሲገዛ የመጀመሪያው ነው፡፡

መጠሪያዬ የተሰኘው አልበም የፊታችን ነሀሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል ፣ በካሴት የቴሌግራም ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል፡፡

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ሙዚቃው ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ይለቀቅ የነበረ ቢሆንም በህጻን ሔቨን ላይ የደረሰውን ጥቃት ምክንያት በማድረግ አንድ ሳምንት መራዘሙን ድምጿዊቷ ገልጻለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Veronica_adane
የቡሄዉ ንጉሥ ድምፃዊ ሰለሞን ደነቀ

" ስርቅታዬ "
....

ስመኝሽ ስመኝሽ አ ስመኝሽ አሃ

ስርቅ አለኝ ስርቅታዬ በዛ ምነው ታነሽኝ ይሆናል ስመኝሽ
ለትዝታ እንዳልጎዳብሽ ጨክነሽ .....
በልጅነቴ በልጅነትሽ
ያረግነው ሁሉ ትዝ ይበልሽ
ወይ ከመንገድ ዳር ደብተር ይዘሽ
እስከ ቤት ድረስ የምሸኝሽ
ፀባይ ቁንጅና የተላበስሽ
ከቶ ያየሽ መች ጠገበሽ
እኔም ባይሽ ብመኝሽ ብቃኝሽ
መች አገኘሁሽ
ጊዜው ቆይቷል ከተለየሁሽ
ግን ከልቤ አትጠፊም ወይ ማን ጠግቦሽ
...
ሆያ ሆዬ ሆ አዛ ማዶ ሆ ጭስ ይጨሳል
አጋፋሪ ሆ ይደግሳል ያቺን ድግስ ሆ ውጨ ውጨ
ከድንክ አልጋ ሆ ተገልብጨ ሆ ያቺ ድንክ አልጋ ሆ አመለኛ
ያለ አንድ ሰው ሆ አታስተኛ
ሆያ ሆዬ ጉዴ
ጨዋታ ነው ልማዴ
ዓውደ ዓመት ድገምና ዓመት
የእማምዬን ቤት ዓመት ወርቅ ይፍሰስበት የአባብዬን ቤት ዓመት ወርቅ ይፍሰስበት ዓመት ዓመት ....

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Buhe
[ ፈራሁ ]
👑 Teddy Afro

ደመናት በሰማይ ቅርጽ እየተፈጠሩ አይስሉም ትተዋል፣
የጓሮ ሰበዞች አበቦች እረግፈዋል፡፡
ወፎችም ጠፍተዋል እንደ ድሮ አይመጡም፣
ሽማግሌዎች ዛፍ ስር ሸንጎ አይቀመጡም፣
ያልጠኑ ጥጃዎች እየፈነጠዙ መስክ ላይ አይሮጡም፣
ልጆች ሲቆጧቸው ቶሎ አይደነግጡም፣
ህጻናት አውቀዋል እንደልጅ አይፈሩም፣
በእሳት ዙሪያ ከበው ተረት አያወሩም፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን አይባልም ቀረ፣
ያልኖረውን እድሜ ልጅም እየኖረ፡፡

ወንዞችም ደርቀዋል እያሉ አይፈሱም፣
ወጣቶች ደክመዋል ለሽበት አይደርሱም፣
ክረምትና በጋም ተናፍቀው አይመጡም፣
ቀኖቹ እሮጠዋል ምንም ጊዜ አይሰጡም፣

እየገሰገሰ እንዲህ እየጋለበ ጊዜ በቀን ፈረስ ዘመን ቢያስስም፣
በዓመት በዓል ቀን እንኳን ዓመት በዓል አይደርስም፣
አሁን እንደድሮ አሁን ያለ አይመስልም፣
ቀብር ይፋጠናል ለቅሶ አይደረስም፡፡

መርዶ አይተረክክም ሞትም አይፈራ፣
በሠርግ ቤት እንኳን አይሞቅም ጭፈራ፡፡

ለአደራ የሚበቃ ሰው አንሷል በአገሩ፣
ጎረቤት አይመጣም ጠንክሯል አጥሩ፡፡

እናቶች በፍቅር ቡና አይተጣጡም፣
ምን አገባኝ እያሉ የሰው ልጅ አይቀጡም፣

ሁሉም ነገር ቢኖር በቃ! ምንም የለም፣
ጥም አይቆርጥም ውሃ አይማርክም ቀለም፣
ገበታ ላይ ያለም እህል ቆርሶ ይዞ መተከዝ አያጣም፣
ይሰከራል ቶሎ በወግ አይጠጣም፣
በቃ!! በቃ!! ደስታ የለም፣
በቃ!! ምንም የለም፡፡

አብሮ መብላት ቀርቶ ፍቅር የጠፋ ዕለት፣
ደስታም ይጨክናል ተስፋም ይጨፍናል፣
የፊቱ አይታይም አሁን ይደፈናል፣
መልኩ አይናገርም ተፈጥሮም ዝም ይላል፣
ሙሉ ሕይወት የለም ሁሉም ባዶ ባዶ፣ ባዶ ባዶ ይላል፣
አሁን የኛም ነገር ይህንን ይመስላል፣
ግን ተስፋ አለ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል፡፡

ህዳር 2001 ተፃፈ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
ፍቅር ያሸንፋል!!

@waliyaentmt
የማስተዋል እያዩ እንዚራ አልበም ይመረቃል

እንዚራ የተሰኘው የ ድምፃዊ ማስተዋል እያዩ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ድግስ ቅዳሜ ነሃሴ 25  2016 ወዳጅና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል ጋዝ-ላይት ክለብ ይመረቃል:።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yelben #mastewal_eyayu
👤 Micheal Belayneh | ሚካኤል በላይነህ
🎵 And Kal | አንድ ቃል
━━━━━━━━━━━━━━
➠ RELEASED: 2024
➠ GENRE: #Ethiopian
➠ TYPE: #Album
➠ TRACKS: 13
➠ FORMATS: #Mp3
➠ CHANNEL: @Waliyaentmt
━━━━━━━━━━━━
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Micheal_belayneh #Album #Ethio_albums #Waliya_Entertainemnt