Waliya Entertainment
295 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
በየዓመቱ በደማቁ የሚከበረውን የሀዲያ አዲስ ዓመት የሆዴ በዓልን በጋር ለማክበር የጋራ የውል ስምምነት ተፈራረሙ።

መንግስት የፈጠረው ምቹ ሁኔታን በመጠቀም ህዝቦች ባህል፣ ቋንቋ፣ እሴቶቻቸውንና ባህላዊ ክዋኔያቸውን ማሳደግና ማበልጸግ ከብሔሩ ተወላጆች ባለፈ ለመላው አለም በማስተዋወቅ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን ለማስቻል እንደ ሸኩራ ፕሮዳክሽን አይነት ድርጅት ጋር መስራት ውጤት እንደሚያስገኝ የተናገሩት የሀዲያ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ ታምሬ ኤርሚያስ ናቸው።

በተያያዘ ዜና የሻኩራ ፕሮዳክሽን መስራቹ እውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሣ በሀገራችን የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ የራሱን አሻራ ያሳረፈና የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች የሙዚቃ ስልተ ምቶችን ያስተዋወቀ ስመጥሩ የሙዚቃ ሰው ሀገራችን ለይ አሉ ከተባሉ ኢቨንት ኦርጋይነዘሮች ጋር በመቀናጀት የሀዲያ ህዝብ የዘመን መለወጫ ያሆዴ በአልን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በደማቁ ለማክበር ከዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን በመጥቀስ በቅርቡ በመዲናችን ስለ አጠቃላይ መርሃግብሩ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kamuzu_kassa #gildo_kassa #shakura_studio
❤️❤️❤️🙏🙏🙏

ኢትዮጵያውያን

እንኳን ደስ አላችሁ

የኦሎምፒክን record በመስበር

በፓሪስ ኦሎምፒክ ታምራት ቶሎ በማራቶን ለኢትዮጵያ ወርቅ አስገኝቷላታል

ላይክ
ሼር
ኮሜንት

አድርጉት ደስ ብሎናል ደስ ይበላችሁ

ተመስገን

❤️❤️❤️🙏🙏🙏

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የመጨረሻ አልበሙ ከምን ደረሰ?

ብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና አድናቆትን ያተረፈው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የመጨረሻ አልበሙን እየሰራ በሚገኝበት ሰአት ላይ በህመም ምክንያት ማረፉ ቢታወቅም አጅናቂዎቹና የሙያ አጋሮቹ አልበሙን ከጥግ ሊያደርሱት ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው። ነገር ግን የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ እህት የሆነችው ድምፃዊ ትግስት አፈወርቅ ለታዲያስ አዲስ እንደገለፀችው የዜማ እና የግጥም ደራሲ የሆነው ዘላለም መኩሪያ ማዲንጎ በድምፅ ሙሉ በሙሉ ገብቶ ያልጨረሰውን ስራ ከማዲንጎ ድምፅ ጋር የሚመሳሰል አንድ ድምፃዊ ድምፁን በመቅዳት የማዲንጎ ስራ አስመስሎ ለመሸጥ እየሰራ እንደሆነ ቤተሰቦቹ በጭራሽ ይሄን ነገር እንደማይቀበሉትም ተናግራለች።

አልበሙን በዋናነት እየሰሩ የሚገኙት ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎ እና ዘላለም መኩሪያ ሲሆኑ ለዚህ ጥያቄ ዘላለም መኩሪያ ስራችውን የጀመሩት በየስቱዲዬው ያሉትን ስራዎች በማሰባሰብ ሲሆን ስራዎቹ አሁን ላይ ያሉት የመለማመጃ ወይም Sample ብቻ እንደሆኑ ሌሎች ድምፃዊያንንም የማስገባቱ ስራ ለሙከራ ያህል የተደረገ እሱንም በሃሳብ ደረጃ የተተወ መሆኑን ገልጿል።

አያይዞም አሁን አልበሙ የማሰባሰብ የመምረጥ እና እንዴት አድርጎ የመለማመጃ ድምፁን ወደ አሪፍ ሙዚቃ መቀየር ይቻላል የሚለውን ገና የማሰብ ደረጃ ላይ እንደሆነ የሚወጣበትም ቀን ያልተወሰነ መሆኑን ገልፀዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music  #Madingo_afewerk
ያሬድ ነጉ መልዕክቱን አስተላልፏል !
የመጨረሻው ሰዓት የመጨረሻው ደቂቃ አለፈች እኔን አስጨንቃ ! በመድሀንያለም እርዳታ

እግዚያብሄር ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻው ይመለከታል
የሆነውን ያውቃል !
የሚሆነውን ያውቃል !
ህመሜን ወስዷል

ሀዋሳ የአላቲዮን ሆስፒታል ዶክተሮች, ነርሶች, የሆስፒታል ሰራተኞች በሙሉ ከልቤ አመሰግናለው 🙏🙏🙏

አጎቴ ነጋሽ ከድር እግዚአብሄር ያክብርህ ❤️❤️🙏🙏 አላህ ይስጥልን

ስለተጨነቃቹልኝ እና ስትፅልዩልኝ የነበራቹ በሙሉ እስላም ❤️ክርስቲያን ❤️ወንድም ❤️እህቶቼ ❤️እናት ❤️አባቶቼ ❤️ክብር ይስጥልኝ ❤️🙏🙏🙏

ሰላም ነው 🙏

ይርጋለም ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ⛪️💒⛪️❤️❤️🙏
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yared_negu
መልካም ልደት ይልማ ገብረአብ!

የዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የግጥም ፈርጥ ተብሎ በብዙዎቹ ዘንድ አድናቆትን ያተረፈው ከ80ዎቹ አንጋፋ ድምፃዊያን ጀምሮ እስከ አሁን ላሉት ድምፃዊያን ጎልተው እንዲወጡ በግጥም ጥበብ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተው የይልማ ግብረአብ ዛሬ ልደቱ ነው።

ዋልያ ኢንተርቴይመንት መልካም ልደት ለይልማ ግብረአብ ይመኛል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ፈታ ሾው በትልቅ የሙዚቃ ሽልማት መጣ!!!

ከዚህ በፊት ሁለት አርቲስቶችን በመጋበዝ የትክክለኛ ዘፋኙን የአፍ እንቅስቃሴ አስመስሎ በመስራት (Lip sync) ሲያወዳድር የነበረው ፈታ ሾው በመባል የሚታወቀው ተወዳጁ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አሁን ደግሞ በትልቅ የሙዚቃ ሽልማት ዝግጅት ብቅ ሊል ነው።

ከዝግጅቱ ዋና አዘጋጅ ጌታነህ ፀሃዬ እንደሰማነው ዝግጅቱ እስካሁን ከለመድናቸው የሙዚቃ ሽልማት ፕሮግራሞች በብዙ መልክ የተለየ እንዲሁም ብዙ የሽልማት ዘርፎችንም እንደያዘ ገልፀዋል።

አያይዘንም ስለ ፈታ ሾው የመመለስ ሁኔታ አለው ወይ ብለን በጠየቅናቸውም መሠረት ፈታ ሾው በቅርብ ጊዜ በአባይ ቲቪ የሚመለስ እንደሆነ የገለፁልን ሲሆን ቅድሚያ ዝግጅቶች አልቀው የተወሰኑ ክፍሎችም አንደተቀረፁ ገልፀውልናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Feta_show
አፍሪክለብ ኦቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ ድምፃዊ ቤተልሔም ሸረፈዲንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

አፍሪክለብ ኦቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ ድምፃዊ ቤተልሔም ሸረፈዲንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን በዛሬው እለት በሳፋየር አዲስ ሆቴል ባካሄደው የድርጅት ትዉዉቅ መርሀገብር አስታውቋል

በመርሀገብሩ ላይ እንደተጠቀሰው መንግስት ለጀመረዉ የኢኮኖሚ ግንባታ የበኩሉን ለመደገፍ አፍሪክለብ አቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ የተማሩ ፣ የሰለጠኑና በከፊል የሰለጠኑ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በዉጭ ስራ ዓለም በመሰማራት ራሳቸዉንና ቤተሰባቸዉን እንዲጠቅሙ እንዲሁም አገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ የምታገኘዉ ዘረፈ ብዙ ጠቀሜታ ማለትም ከዉጭ ስራ ዕድል ተጠቃሚዎች ወደ አገር ዉስጥ የሚገባዉ የዉጭ ምንዛሪ ፤ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ ጥቅም እንደምታገኝ ታሳቢ በማድረግ የዉጭ የስራ እድልን በህጋዊ መንገድ ለማስኬድ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

ደርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የዉጭ አገር ስራ ዕድል ፈለጊ ኢትዮጵያዉያን የማማከርና የማሳለጥ አገልግሎት ፣ የዉጭ አገር የትምህርት እድል ማፈላለግ፣ ማማከርና ማሳለጥ ፣ በኦንላይን የዉጭ አገር ቋንቋ ስልጠና መስጠት ፣ የዉጭ አገር የንግድና የምርት ማስተዋወቅ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ነጋዴዎችና አምራቾች የማማከርና የማሳለጥ ስራዎች መስራት ፣ በዉጭ አገር ህክምና ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ቪዛ የሚያገኙበት ሂደት ማማከርና ማሳለጥ እንዲሁም ኢትዮጵያዉያን ዜጎች የቱሪስት ቪዛ የሚያገኙበትን ሂደት ማማከርና ማሳለጥ እንደሆኑ ተገልጿል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
ፈታ ሾው በአባይ ቴሌቪዥን በአዲስ መልክ ሊጀመር ነው ተባለ።

የፈታ ሾው ወደ ሚዲያ ሊመለስ እንደሆነ ዛሬ ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም በአባይ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ከአመታት በኋላ በአዲስ አመት መስከረም 1 በአባይ ቴሌቪዥን ፈታ ሾው "ፈታ ሙዚቃ ሽልማት" የተሰኘ አዲስ ነገር ይዘው መምጣቱን አርቲስት ጌታነህ ፀሐዬ ገልጿል።

በፈታ ሙዚቃ አዋርድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ያለምንም ቀጥተኛ ውድድር ላበረከቱት አስተዋጾ ለሰራቸው እውቅናን የሚያገኙበት ሁሉን ያካተተ እና አሳታፊ መድረክ ለመፍጠር እንደሆነ ጌታነህ ተናግሯል።

ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ባህላዊ እና ዘመናዊ ገፅታዎች ለማንፀባረቅ በትኩረት የታቀደ የሸልማት ትእይንት ብቻ ሳይሆን የባህል አከባበርም ነው ተብሏል።

የፈታ ሙዚቃ አዋርድ ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በብሄራዊ ቴአትር ሸልማት ሰርዓቱ የሚካሄድ ሲሆን መስከረም 1/2017 ዓ.ም በአባይ ቴሌቪዥን ይተላለፋል።

ፈታ ሙዚቃ አዋርድ በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን ሰኬት ከማክበር ባለፈ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን እንደያዘ የማክበር እና የመጠበቅን ስርዓት በማስቀጠል የሙዚቃውን ብሎም ሙዚቀኛውን ማስከበር ነው ተብሏል።

ፈታ ሾው "ፈታ በአባይ" በተሰኘ ስያሜ በአዲስ አመት በአባይ ቴሌቪዥን መተላለፍ ይጀምራል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"አንድ ቃል" ነሐሴ 17

የተወዳጁ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ "አንድ ቃል" የተሰኘው ሶስተኛው የሙዚቃ አልበሙ በዕለተ ዓርብ ነሐሴ 17 ይለቀቃል።

ከዚህ በፊት ከሰራቸው ስራዎች የቱን ትወዱታላችሁ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
#Album #michaelbelayneh #Andkal
የቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበም በ17 ሚሊየን ብር ተሸጠ።

በብዙ ተወዳጅ ዘፈኖቿ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈችው ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበሟ ነሃሴ 17 ለህዝብ ተመልካቹ የሚቀርብ ሲሆን በ160ሺ የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ17ሚሊየን ብር በላይ መሸጡን ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከውስጥ አዋቂዎች ማወቅ የቻለ ሲሆን ይህም በኢትዬጲያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ሪከርድ የሰበረ እንደሆነም ማወቅ ችለናል።

አልበሙን የገዛው "Zojak worldwide" የተሰኘው የአሜሪካ አሳታሚ ድርጅት ሲሆን በዋናነት የተለያዩ መተግበሪያዎች ላይ የአርቲስቶችን ስራ የሚያከፋፍል ነዉ።

አልበሙ 12 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ቅድሚያ ለ 2 ዘፈኖች ሺዲዬ በአሜሪካ ሃገር እንደተሰራላቸው አልበሙ በሚለቀቅበትም ቀን በእኩል ሰአት እንደሚለቀቁም በተጨማሪም ግዢው ቪዲዬ ክሊፖችንም እንደሚጨምር ለማወቅ ችለናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Veronica_adane
ያወቀ ይሸለማል🏆🏆🏆

የልጅቷን እና የአባትዋን ስም በስትክክል ለመለሱ ለ3 ልጆች የ 100ብር ካርድ ይሸለማሉ!!!!

ለመሸለም ሼር ማድረግ የግድ ነው!!!