Waliya Entertainment
291 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች 47ተኛ የልደት በአሉን በማስመልከት በስለ እናት የእርዳታ ተቋም ካሉ ልጆች ጋር አሳለፉ።

ቀናችሁን እና ጊዜያችሁን ሰውታቹ የንጉሱን ልደት በ Sele Enat Mahiber ከሚገኙ ልጆቻችን ጋር አብራችሁን ላሳለፋቹ ከበጎ ስራዎቻችን ጎን ለቆማቹ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ቤተሰቦች ፣የቅርብ ወዳጆች ፣አክባሪ አድናቂዎች እንዲሁም የወደ ፍቅር ማህበር እና የስለ እናት ቤተሰቦች ሁላችሁንም ከልብ ከልብ እናመሰግናለን ።" ከወደ ፍቅር ጉዞ ማህበር

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt
#Teddy_afro #happybirthday
# Teddy_Afro_Fans #ወደ_ፍቅር . .
👍1
ተራዘመ!!!

ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 13 በመስቀል አደባባይ ሊከናወን ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ኦሎምፒክ ኮንሰርት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር ለመግለፅ እንወዳለን ።

አዘጋጆቹ !

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት ተመልካች ያገኙ 10 የሳምንቱ ሙዚቃዎች

በዚህ ሳምንትም የአብዱ ኪያር 5 ሙዚቃዎች የደረጃ ሰንጠረዡን ተቆጣጥሯል፣ ባለፈው ሳምንት የተለቀቀው የሰላማዊት ዮሐንስ አዲስ ሙዚቃ በዚህ ሳምንትም ሁለተኛ ደረጃ አለቀቀም፣ አንዱአለም ጎሳ እና ሮፍናን በዚህ ሳምንትም ከቶፕ 10 አልወጡም ደረጃቸውን በማሻሻል ወደ ላይ ከፍ ብሏል።

1ኛ🔸አብዱ ኪያር (ገለመሌ) 🎶 1,024,491 እይታ
2ኛ🔸ሰላማዊት ዮሐንስ (ሰንቢደ) 🎶 717,604 እይታ
3ኛ አብዱ ኪያር (ፓ! ፓ! ፓ!) 🎶 522,697 እይታ
4ኛ🔻 አብዱ ኪያር (አይዞ) 🎶 509,086 እይታ
5ኛ አንዱዓለም ጎሳ (ቢሊሌ) 🎶 434,174 እይታ
6ኛ ሮፍናን (ሸግዬ) 🎶 349,646 እይታ
7ኛ🔻አብዱ ኪያር (ባይ ባይ) 🎶 332,182 እይታ
8ኛ🔸 አብዱ ኪያር (ቡቡዬ) 🎶 326,902 እይታ
9ኛ🔸 ናሆም መኩሪያ (ባዳ ባዳ) 🎶 320,199 እይታ
10ኛ🔸 ቬሮኒካ አዳነ (እናነይ) 🎶 304,092 እይታ

ደረጃ ያሻሻሉ
🔻 ደረጃ የቀነሱ
🔸ባሉበት ደረጃ የቆዩ

🎶 በሳምንቱ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት የታዩ ሙዚቃዎችን በትክክለኛ ዳታ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ምርጥ አስር ሙዚቃ ሰንጠረዥ ነው።

🎶 ቁጥሮች በሳምንት ውስጥ የጨመሩትን እይታ ብቻ ነው የሚያሳየው።

ቅዳሜ ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ከዛሬ 23 አመት በፊት 1993 ላይ "ለህይወትህ ዋጋ ስጥ" የተሰኘ በዘመኑ "ካርኒቫል" ባሁኑ ጊዜ ኮንሰርት እንደሚባለው ማለት ነው

ሙዚቃ ዳንስ፣ ቀልዶች፣ ፋሽን ትርኢት፣ የሰውነት ቅርፅ ውድድር፣ ዜማ ላስታ፣ ራፕ፣ ሬጌ ....... በዲኬቲ ኢትዮጲያ እና ፕሮሞተር ዲጄ ዚ ተዘጋጅቶ ነበር

ማንን አያችሁ ፖስተር ላይ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ንግድ ባንክ ያለኔ ፈቃድ የባንክ statement ለሌላ ሰው ሰጥቶብኛል " ዳግማዊት ፀሀዬ

#Ethiopia: አርቲስት ዳግማዊት ፀሀዬ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መልእክት አስተላልፋለች :- ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ officially ጥያቄ አለኝ ?
ለጊዜው ሀገር ውስጥ የሌለችው የሙዚቃ ዝግጅቷን በዱባይ እያቀረበች በመሆኑ አሁን ሃገር ውስጥ ስለሌለሁ አሁን head office መምጣት አልችልም ግን ካለ አንድ ሰው ፍቃድ የሰው አካውንት statement ለሌላ ሰው መስጠት ይቻላል እንዴት ያለ ስርአት ነው ፤
አልገባኝም ? ? በውስጥ የሚያወራኝ ተወካይ ካለ
ዝርዝር ጉዳዩን ላስረዳ ችላለሁ ብላለች ።

Via ዳግማዊት ፀሀዬ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
በጎፋ ዞን ጎዝዲ ቀበሌ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ በበርካታ ዜጎቻችን ሕይወት ላይ በደረሰው አስከፊ አደጋ ዋልያ ኢንተርቴይመንት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ምስሉ ላይ በተቀመጠዉ በዞኑ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ( 1000511561276 ) በመጠቀም የአቅማችንን እንድንለግስ ዋልያ ኢንተርቴይመንት በትህትና ይጠይቃል 🙏🏽

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ሽልማቱም ተገኝቷል ተሸላሚውም ታውቋል።

በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የሙያ ከፍታዎች የሚሰጡ ሽልማቶች አሉ እንደየ ዘርፉ። እነዚህ ሽልማቶች በተለያዩ ምክንያቶች ከተሸላሚዎቹ ከሚገባቸው ሰዎች እጅ በተለያዩ ምክንያቶች ይወጣሉ።

በሌቦች ይሰረቃሉ፣ በጨረታ ይሸጣሉ፣ በመታሰቢያነት ይሰጣሉ።

ታላቁን እና ከዘጠኝ አስርት አመታት በላይ የዘለቀውን የኦስካር ሽልማትን እንኳን ብናይ ሽልማቶቹ ተሰርቀው፣ ከተቀመጡበት ጠፍተው፣ ሊኖሩ ከሚገባቸው ስፍራ ሳይሆን እንደ ተራ ቁስ ተጥለው ተገኝተው ይታወቃል።

የመጀመሪያዋ ጥቁር የኦስካር ተሸላሚ ሃቲ ማክዳኒየል በጎን ዊዝ ዘዊንድ ያገኘችውን የኦስካር ሽልማት ለሀዋርድ ዩኒቨርስቲ በመታሰቢያነት ሰጥታ ተሰርቋል፣ ማይክል ጃክሰን የዚሁኑ ፊልም ጎን ዊዝ ዘዊንድ ምርጥ ፊልም ሽልማት ገዝቶት ነበር ለመታሰቢያነት ማለት ነው በ1.2 ሚሊዮን ዶላር።

ይህ ሽልማት ግን ተሰርቆ ከማይክል ጃክሰን እጅ ወጥቶ እስካሁን የት እንዳለ አይታወቅም። በአንድ ወቅት 55 የሚደርሱ የኦስካር ሽልማቶች ከሽልማቱ በፊት ተሰርቀው በፖሊስ ተገኝተዋል። ሌላም ሌላም ማንሳት ይቻላል።

ወደ ሰሞነኝው የሀገራችን ጉዳይ ስንሄድ ሰሞኑን አንድ የጉማ አዋርድ ሽልማት ምን አለሽ ተራ ተገኘ ተብሎ  ወሬው ሲናፈስ አስተውለናል። ሽልማቱ ካለ ቦታው የተገኘበትን አጋጣሚ በቅጡ ባለመገንዘብ የተነሳ ብዙ ብዙ ተብሏል።

ነገሩ እንዲህ ነው ሰለሞን አክሊሉ የተባለ አንድ ቅን ሰው ወደ ስልኬ ይደውላል ይህ በፌስቡክ ላይ ሲዘዋወር የታየውን ፅሁፍ እና ምስል አያይዞ በመላክም የተባለው ሁሉ መላምታዊ መሆኑንና እሱ ይሄንን ሽልማት በአጋጣሚ ከሌሎች የሽልማቱ ተሸላሚ ግላዊ ንብረቶች ጋር የፎቶ ግራፍ አልበምን ጨምሮ በኪሎ እንደገዛው ገልፆልኛል።
የኝህ ታላቅ ሙያተኛ ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው ቤታቸው ለልማት ተብሎ በፈረሰ ወቅት ይህ አጋጣሚ እንደተፈጠረ እና በጊዜውም ከሌሎች እርባና ከሌላቸው ቁሶች ጋር ተቀላቅሎ እንደተሰጠውም ገልጿል።

እኝህ ተዋቂ ጥበበኛ አሁን በህይወት የሉም ስማቸው እና ስራቸው ለምድር የከበደ፣ ለሰማይ የራቀ ነው። ለልጆቻቸው ለቤተሰቦቻቸውም ስንል ስማቸውን ከመጥቀስ እንቆጠባለን። ግን ደግሞ ለዘመናት የሙያ ስኬቶቻቸው የተስተዋሉባቸው ምስሎችን የያዘው አልበማቸውን ጨምሮ በጉማ አዋርድ አዘጋጆች የተሸለሙትን የህይወት ዘመን ሽልማት ከቻልን ለሽልማቱ አዘጋጆች ካልሆነም ለቤተሰቦቻቸው በዳግም ክብር መልሰን እንሰጣለን።

ይሄ እንዲሆን ያስቻለውን ሰለሞን አክሊሉን ግን ከልብ እናመሰግናለን ብዥታውንም ስላጠራልን።
ለዛ ።   - ብርሀኑ ድጋፌ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ መልዕክት ....🙏🙏

“በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።”

እስኪ የምትወዷት በላይክ ግለፁለት!!!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
Today's Best photo🥰🥰🥰

Youtube -  https://www.youtube.com/@waliyaent?sub_confirmation=1

#photo #photographychallenge
#photooftheday #photochallengesmilechallengetoday
#waliya_entertainment #Zeritu_kebede
👍21
ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የተሰሩት ገሚስ አልበም ዛሬ ይመረቃል

ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የተሰሩት "አዲስ ቀለም" የተሰኘ ገሚስ አልበም ዛሬ ሐምሌ 18 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ቦሌ ዓለም ሲኒማ አካባቢ በሚገኘው "The Jungle" ውስጥ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የዚህ ገሚስ አልበም ምርቃት መግቢያ በነፃ ተብሏል።

"አዲስ ቀለም" ገሚስ አልበም በውስጡ ምንድነው ፣ ኤሌክትሪክ፣ ማዕዘን፣ተው ተው፣አንድ ሰሞን የተሰኙ አምስት ሙዚቃዎችን የያዘ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

የገሚስ አልበሙ ግጥም ፣ ዜማ፣ እንዲሁም ከሙዚቃው ቅንብር እስከ ማስተሪንጉ ድረስ በያምሉ ሞላ ተሰርቷል።

በተጨማሪም በከበሮ አገረሰላም ሻፊ ፣ በመሰንቆ ሀዲንቆ፣በክራራ ፋሲካ ኃይሉ ተሳትፈዋል።

"አዲስ ቀለም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና የሙዚቃ አቀናባሪው ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ የተጣምሩበት ገሚስ(EP) የሙዚቃ አልበም በዩቲዩብ እና ስፖቲፋይ መተግበሪያዎች በኩል ባሳለፍነው አርብ እንደተለቀቀ ይታወሳል

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ከሰሞኑን በደቡቡ የሀገራችን ክፍል (ጎፋ) በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ እና ጉዳት በደረሰባቸው ኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ በደረሰውም አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች በሙሉ ከልብ መፅናናትን እመኛለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል !
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)