Waliya Entertainment
291 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
22. ሁለተኛ የአልበም ስራው ደግሞ በ1996 ዓ. ም ላይ በኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽን ለገበያ የበቃው ‹‹ታሪክ ተሰራ›› ነው፡፡ ‹‹ታሪክ ተሰራ›› በኢትዮጵያ የ10ሺ ሜትር አትሌቶች የቡድን ስራ በመማረክ በአንድ ሌሊት ተሰርቶ በማግስቱ በኤፍኤም ሬድዮ በመለቀቅ ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈ ነጠላ ዜማ መሆኑ ይታወቃል፡፡

23. በ1997 ዓም ላይ 3ኛው አልበም ‹‹ያስተሰርያል›› በሚል ርዕስ በናሆም ሬከርድስ ለመታተም በቅቷል፡፡ ይህ አልበም በጥቂት ወራት ሁለቴ ለመታተም የበቃ ሲሆን፤ ከሚሊዮን ቅጂዎች በላይ ተሰራጭቶ ክብረወሰን እንዳስመዘገበም ይገለፃል፡፡

24. በ1998 ዓም ‹‹ቤስት ኮሌክሽን ናሆም ቮሊውም 14›› ተብሎ በናሆም ሪከርድስ አሳታሚነት በተለያዩ ጊዜያት የሰራቸው ነጠላ ዜማዎች ተሰባስበውበት 4ኛው አልበም ለገበያ ቀርቧል፡፡

25. ‹‹ጥቁር ሰው›› በሚል በአዲካ ሬከርድስ አሳታሚነት ለገበያ የቀረበው የመጨረሻ አልበሙ ነው፡፡

26. ጥቁር ሰው የሚለው አልበሙን ለአሳታሚው አዲካ ሪከርድስ በ4.6 ሚሊዮን ብር መሸጡ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ሪከርድ ሲሆን ይህ አልበም በመጀመርያው እትም በቴፕ ካሴት 300ሺ እንዲሁም በሲዲ 500000 ቅጂዎች መሸጡና ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስገኘቱ በሙዚቃኢንዱስትሪው ክብረወሰኖች ሆነው የሚመዘገቡ ናቸው፡፡

27. ጥቁር ሰው ለተባለው ዘፈኑ የሙዚቃ ቪድዮው ከ500ሺ በላይ ወጭ በማድረግ ባለ ሪከርድ ነው፡፡

28. ጥቁር ሰው ያለውን የመጨረሻ አልበም ካወጣ አራት አመት ሲሆነው ይህን አልበም ለማስመረቅ በጊዮን ሆቴል ቀርቦ የነበረው ኮንሰርት በቅርቡ በአምባሳል አሳታሚነት ለገበያ እንደቀረበ ይታወቃል፡፡

29. አዲስ ሙሉ አልበሙንም እየሰራ ነው፡፡ ይህ አልበሙ በኒውዮርክ ከተማ በሚገኝ ታዋቂ ስቱዲዮ መዘጋጀቱ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ከቦብ ማርሌ ልጅ ዳይመን ማርሊ ጋር በጋራ የሚጫወቱት የሬጌ ስራ እንዳለውም ለማወቅ ተችሏል። በዚህ አልበም ውስጥ ከሚገኙ አዳዲስ ስራዎች አምስት ዘፈኖቹን የሚያቀናብርለት ታዋቂውና የሶስት ግራሚ ተሸላሚ የሆነው ዝነኛው አሜሪካዊ አቀናባሪ ጎርደን ዊሊያምስ ነው፡፡ ጎርደን፤ ለአሊሺያ ኪስ፣ ሎሬን ሂል፣ ካርሎስ ሳንታና፣ ኤሚ ዋይን ሀውስ እና ለፊፍቲ ሴንት የሰራና ሶስት የግራሚ ሽልማቶችን ያገኘ ትልቅ የሙዚቃ ባለሙያ ነው፡፡

30. በተለያዩ ጊዜያት በሚወጡ ነጠላ ዜማዎች ስኬቱም ይታወቃል፡፡ ነጠላ ዜማ ሲያወጣ አገር ይንቀጠቀጣል አገር ይቅበጠበጣል አቧራ ይነሳል፡፡ ይህ ደግሞ በኢንዱስትሪው ምርጥ ብቃት እንዳለው የሚያረጋግጥ ነው፡፡ እንደማስረጃ በተለያዩ ጊዜያት የተለቀቁ ነጠላ ዜማዎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ አቦጊዳ ከሚለው አልበም አቦጊዳ፣ ልጅነት አላት፣ ለማን ልማሽ እና ሞናሊዛ ፤ ያስተሰርያል ከሚባለው አልበም ያስተሰርያል፣ በል ስጠኝ፣ ላምባዲና አላምን የሚታወሱ ናቸው፡፡ መንታ ወድጄ፣ያረጋል፣ ላሜ ቦራ እና ስደት የተባሉት ሌሎች አራት ነጠላ ዜማዎችም ከፍተኛ ተደማጭነት በማግኘት የተሳካላቸው ሲሆኑ፤ የመጨረሻው አልበሙ ጥቁር ሰው ከመውጣቱ በፊት ደግሞ ሰላም ፣ ፊዮሪና ፣ ልረሳሽ አልቻልኩም ፣አባይ፤ ውዴ፤ አይደነግጥም ልቤ እና ትዝታ ይጠቀሳሉ፡፡ ከ5 በላይ ነጠላ ዜማዎች በአንድ ዘፋኝ እንዲህ በዝተው በአንድ ሰሞን ሲሰራጩ የተለመደ ስላልነበር እነዚህ ነጠላ ዜማዎች ለመጀመርያ ጊዜ በተሰሙበት ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ያነጋገሩ ነበሩ፡፡ ሰባ ደረጃ እና ኮርኩማ አፍሪካ ደግሞ እጅግ በጣም የተሳካላቸው ነጠላ ዜማዎቹ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

31. በመኪና ሰው ገጭቶ በመግደል ክስ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የ6 ዓመት እስራት እና የ18ሺ ብር ቅጣት ተላልፎበት ነበር፡፡ ይግባኝ ተጠይቆ እስሩ ወደ ሁለት ዓመት ወርዶለታል፡፡ በወንጀሉ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በፍርድ ውሳኔ እስር ቤት እስገባበት ድረስ 482 ቀናትን ካሳለፈ በኋላ በአመክሮ ሊፈታ ችሏል፡፡

32. በማህበራዊ ሚዲያዎች ከኢትዮጵያ ዝነኛ ሙዚቀኞች የሚስተካከለው የለም፡፡ በፌስቡክ ከ1 ሚሊዮን በላይ ወዳጆች አሉት፡፡ በትዊተር ገፁ ከ3ሺ በላይ ተከታታዮችን አፍርቷል፡፡ በዩቲውብ የተጫኑ ከ145ሺ በላይ የሙዚቃ ቪድዮች እና ተያያዥ መረጃዎች አሉት፡፡ አንዳንድ የዩቲውብ ቪዲዮቹ ከሚሊዮን በላይ ተመልካች ያገኙ ሲሆኑ ብዙዎቹን የሙዚቃ ቪድዮች፤ የኮንሰርት ትእይንቶች ፤ቃለምልልሶች እና ሌሎች ጉዳዮች በዩ ቲውብ በአማካይ ከ1 እስከ 10ሚሊዬን በላይ ተመልካቾች ይጎበኟቸዋል፡፡ በአድናቂዎቹ አማካኝነት በስሙ፤ በስራዎቹ እና ሌሎች በሚሰጡት ልዩ ልዩ ማዕረጎች የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክ ገፆችም ይገኛሉ፡፡ http://www.teddyafromuzika.com በአሁኑ ጊዜ ጥሩ እየተንቀሳቀሰያለ ድረገፁ ነው፡፡

33. በ1991 ዓም ከያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ከወጡ ሙዚቀኞች ጋር ላስታስ ባንድን አብሮ መስርቷል፡፡ ባንዱንም በበላይነት በመቆጣጠር እና በመምራትም ትልቅ ድርሻና ሃላፊነትም ነበረው:: ከላስታስ በኋላ አቦጊዳ ባንድን ማናጀሩ ከነበረው ታዋቂው አዲስ ገሠሠ ፤ በታዋቂው ዳሎል ባንድ ከሰሩ ሙዚቀኞች በመቀናጀት ሊመሰርት ችሏል፡፡ በዋናነት ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ የሆኑ ከ5 እስከ 7 ሙዚቀኞችን በአባልነት ያሰባስበው አቦጊዳ ጋር በኢትዮጵያ ፣ በሰሜን አሜሪካ ፣ በአውሮፓ እና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በርካታ ኮንሰርቶች በመሥራት ከፍተኛ ልምድ አለው ፡፡ በባንዱ የሚሰሩት ሙዚቀኞች ዓለም አቀፍ ደረጃ ባላቸው የሬጌ ሙዚቃ ባንዶች፣ ከአንጋፋ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ጋር በመስራት ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡

34. የመጀመርያው ኮንሰርትን የሰራው በ2003 እኤአ ላይ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ገቢ ማሰባሰቢያ በመስቀል አደባባይ በተዘጋጀበት ወቅት ነበር፡፡ በ2005 እኤአ ላይ የቦብ ማርሌይ 60ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ኮንሰርት በተዘጋጀበት ወቅት ላይ የተሳተፈው የዝግጅቱን መክፈቻ ሙዚቃዎች በማቅረብ ነበር፡፡

35. ከአገር ውጭ በመላው አለም በአፍሪካ፤ በአውሮፓ፤ በሰሜን አሜሪካ፤ በአውስትራልያ እና በመካከለኛው ምስራቅ በመዘዋወር በ40 ትልልቅ ከተሞች ኮንሰርቶችን አቅርቧል፡፡ በተለይ በ2006 እኤአ ላይ ለአስር ወራት በቆየ እና ወደ አገር ቤት በሚል ስያሜ የኮንሰርት ዝግጅቱ

የዓለም ከተሞችን ማካለሉ ይገለፃል፡፡ በ2009 እኤአ ላይ ከእስር ከተፈታ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታድዬም በተዘጋጀ ኮንሰርት ሙዚቃዎቹን ሲያቀርብ ከ60ሺ በላይ ታዳሚዎችን አግኝቷል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚያቀርባቸው የሙዚቃ ዝግጅቶች በአማካይ እስከ 15ሺ ዶላር እንደሚከፈለውም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

36. የኔዘርላንድ ኩባንያ ሄኒከን ከሚያስተዳድረው በደሌ ቢራ ጋር በመሆን በመላ አገሪቱ በመዘዋወር የፍቅር ጉዞ በሚል ርእስ ለሚያቀርባቸው ኮንሰርቶቹ 25 ሚ.ብር ተመድቦ ሊሰራ ነበር፡፡ በኢንተርኔት በተካሄደ የተቃውሞ ዘመቻ ከ20ሺ በላይ ሰዎች በሰበሰቡት ድምጽ ኮንሰርቶቹ ቢሰረዙም በውሉ መሰረት 4.5 ሚ. ብር ተከፍሎታል፡፡

37. ጥላሁን ገሰሰ እና ቦብ ማርሌይ ትምሳሌቶቹ ናቸው፡፡

38. በበጎ አድራጎት ስራዎቹም ይታወቃል፡፡ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት በመስራት፤ ለአበበች ጎበና የህፃናት ማሳደጊያ እና ለአካል ጉዳተኞች ማህበር የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት እንዲሁም በሱዳን ታስሮ ለነበር ኤርትራዊ ዋስትና 700ሺ ብር ለዋስትና በመክፈል የሰራቸው ተግባራት ይጠቀሳሉ፡፡
39. በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ በህይወት እያለ መፅሃፍ የተዘጋጀለት ብቸኛው ድምፃዊም ነው፡፡ ‹‹የቴዲ አፍሮ ታላቅነት ሚስጥር›› በሚል ርእስ የህይወት ታሪኩን የሚዳስስ መፅሃፍ ያዘጋጀው አቤል ዘነበ የተባለ ፀሃፊ ሲሆን አብዮታዊ ሙዚቀኛ ብሎታል፡፡

40. በካናዳ አገር በዊንፔግ ከተማ " የትውልዱ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና አርአያ ለሆኑ ሰዎች " የሚሰጠውን ሽልማት የወሰደው 40ኛ ዓመት ልደቱን ባከበረበት እለት ነው፡፡ በ2016 የኮራ አዋርድ ላይ በምርጥ ዝነኛ ድምጻዊ (LEGENDARY AWARD) ዘርፍ ታጭቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በ2014 እ.ኤ.አ ላይ ብራዚል ላስተናገደችው 20ኛው የዓለም ዋንጫ ዘፈን እንዲሰሩ በውድድሩ ዋና ስፖንሰር በኮካኮላ ኩባንያ ከተመረጡ ሙዚቀኞች አንዱ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም በወከለ የሙዚቃ ስራው ተደንቋል፡፡

☞ማስታወሻ;
ተጨማሪ መረጃዎችን መስጠት እና ማስተካከያዎችን መጠቆም ይቻላል
☞ ምንጮች;
አዲስ አድማስ ጋዜጣ፤ ፎርቹን ጋዜጣ፤ ዊኪፒዲያ፤ ቴዲ አፍሮ ሙዚቃ የተባለ ድረገፅ ፤ሰዋሰው…ሌሎች

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Teddy_Afro
👍1👏1
ጎሳዬ ተስፋዬ ለምን አለቀሰ ?
ድምፃዊ ጎሳዬ ዛሬ በተወለደበት አካባቢ ተገኝቶ የክብር እውቅና በጓደኞቹ ተበርክቶለታል ''አብሮ አደግ በፍቅር መረዳጃ ማህበር '' በመርካቶ አካባቢ የሚገኙ ወጣቶች የመሰረቱት ማህበር ሲሆን ጎሳዬን ስለመልካም ስራዎቹ እውቅና ሰጥተውታል ።

እንዲሁም ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ባለቤቱ በተገኘችበት ተዘክሯል ።
ጎሳዬ ካባ የለበሰ ሲሆን ስለተደረገልኝ ነገር አመሰግናለሁ እንዲሁም የገኔን ባለቤት በተቻለው አቅም ጎብኝቶ እንደሚያፅናናት በንግግሩ አስታውቋል ።


Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ የውጪ ሀገራት በትላንትናው እለት የዋለው የትውልድ ቀኔን በማስመልከት መልካም ምኞታችሁን ለገለፃችሁልኝ የሙያ አድናቂዎቼና ወዳጆቼ እንዲሁም ይህን ቀን በምስመልከት በየዓመቱ በበጎ አድራጎት ይህን ቀን አስባቹ ለምትውሉ ወገኖቼ በሙሉ ከፍ ያለ የአክብሮት ሰላምታዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።"

ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን
Teddy Afro (ቴዲ አፍሮ)

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro
ሚውዚኮሎጂ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ

#Ethiopia | ድምጻዊ እና የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋች ሄኖክ መሀሪ እስካሁን ሦስት የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጭ አድርሷል፡፡

የመጀመርያ አልበሙ እውነተኛ ፍቅር የሚሰኝ ሲሆን
ሁለተኛ አልበሙ ደግሞ 790 የሚል ስያሜ አለው
ሶስተኛ አልበሙን አዝማች በሚል ስያሜ ለአድማጭ አድርሷል
መሀሪ ብራዘርስ በሚል ስያሜ ከወንድሞቹ ጋር በመኖን በማቋቋም ላለፉት 18 አመታት ግዙፍ የሆኑ የሙዚ መድረኮችን አዘጋጅተዋል በማዘጋጀት ላይም ናቸው፡፡

በ2016 በአፍሪማ አዋርድ ምርጥ R and B እና ሶል የሙዚቃዎች ስልቶች ከመላው አፍሪካ አሸናፊ ነበር፡፡

በ2016 ኮክ ስቲዲዮ ላይ ኢትዮዽያን በመወከል አሸናፊ ነበር፡፡
በ2017 በስፔን ሀገር ሮቶ ቶም ሰን ስፕላሽ በተሰኜ ፌስቲቫል ላይ በመሀሪ ብራዘርስ ባንድ አማካኝነት ኢትዮዽያን ብሎም አፍሪካን ወክለው ተሳታፊ ነበሩ፡፡

አሁን ደግሞ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሚውዚኮሎጂ የተሰኘ ታዋቂ የሙዚቃ ዝግጅቱን ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍2
ፓስፖርታቸው ለ45 ቀናት የተያዘባቸው ድምፃውያን መጨረሻ ?

በቤልጅየም ሮንሲ ከተማ በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን 19ኛ አመት ፌስቲቫል ይካሄዳል ።

በዚህ ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ዝግጅታቸውን እንዲያቀርቡ ተጋብዘው የነበሩ አ.አ የሚገኙ ድምፃውያን እንከን አጋጥሟቸው ከርሟል ።
ቪዛ ለማግኘት ፓስፖርታቸው ቤልጅየም ኢንባሲ ገብቶ 45 ቀናት ቆይቷል ። በዚህ የመጣ እዛው አውሮፓ ስፔን እና ቤላሩስ እና በዱባይ ብሎም በኳታር ስራቸውን ለማቅረብ ከተዋዋሉት መካከል ድምፃዊ ካሳሁን እሸቱ አንዱ ነው ።

በተለይ ከ12 ቀናት በፊት በዱባይ አልበሙን ያስመርቅ የነበረ ቢሆንም ፓስፖርቱን ቤልጂየም ኤምባሲ ስለያዘበት ለመሰረዝ ተገዷል ።

ምክንያቱን ለማጣራት ባደረግነው ጥረት የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራቱ በኢትዮጵያ ላይ ከፓስፖርት ጋር በተገናኘ ይሰጡ የነበረውን እስከ 45 ቀን እንዲያዘገዩ በመወሰኑ ነው ። ተመላሽ ስደተኞችን በመቀበል ላይ ዳተኝነት አሳይታለች በሚል ከወራት በፊት ውሳኔውን ማሳለፏ ይታወሳል ።  በሳለፍነው ሳምንት አንድ ድምፃዊ በተለያዩ ሀገራት ስራ እያመለጡት ስለሆነ ''ፓስፖርቴን መልሱልኝ '' ብሎ ሊገባ ሲል የምስራች ሰምቷል ። ለድሜፃውያኑ ስለመፈቀዱ ። እናም በዚህ  በዚህ ሳምንት ለድምፃዊ ታረቀኝ ሙሉ ፣ አብነት ገርማ እና ካሳሁን እሸቱ ከአሰልቺ ቀናት ቆይታ በኋላ ቪዛ ተመቶላቸው  ፓስፖርታቸውን መቀበላቸውን ሁሉ አዲስ አረጋግጣለች ። የተከለከሉም እንዳሉ አረጋግጠናል ።

በቤልጅየም ከJuly 29 August 3 ድረስ በሚኖረው ፌስቲቫል አስቴር አወቀ፣ ፀሀዬ ዮሀንስ፣አብዱ ኪያር እና ናቲ ማን ከኢትዮጵያ ከሚያመሩት ድምፃዊያን ጋር በጋራ በመሆን ስራቸውን ያቀርባሉ ።

@waliyaentmt
@waliyaentmt
@waliyaentmt
የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች 47ተኛ የልደት በአሉን በማስመልከት በስለ እናት የእርዳታ ተቋም ካሉ ልጆች ጋር አሳለፉ።

ቀናችሁን እና ጊዜያችሁን ሰውታቹ የንጉሱን ልደት በ Sele Enat Mahiber ከሚገኙ ልጆቻችን ጋር አብራችሁን ላሳለፋቹ ከበጎ ስራዎቻችን ጎን ለቆማቹ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ቤተሰቦች ፣የቅርብ ወዳጆች ፣አክባሪ አድናቂዎች እንዲሁም የወደ ፍቅር ማህበር እና የስለ እናት ቤተሰቦች ሁላችሁንም ከልብ ከልብ እናመሰግናለን ።" ከወደ ፍቅር ጉዞ ማህበር

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt
#Teddy_afro #happybirthday
# Teddy_Afro_Fans #ወደ_ፍቅር . .
👍1
ተራዘመ!!!

ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 13 በመስቀል አደባባይ ሊከናወን ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ኦሎምፒክ ኮንሰርት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር ለመግለፅ እንወዳለን ።

አዘጋጆቹ !

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት ተመልካች ያገኙ 10 የሳምንቱ ሙዚቃዎች

በዚህ ሳምንትም የአብዱ ኪያር 5 ሙዚቃዎች የደረጃ ሰንጠረዡን ተቆጣጥሯል፣ ባለፈው ሳምንት የተለቀቀው የሰላማዊት ዮሐንስ አዲስ ሙዚቃ በዚህ ሳምንትም ሁለተኛ ደረጃ አለቀቀም፣ አንዱአለም ጎሳ እና ሮፍናን በዚህ ሳምንትም ከቶፕ 10 አልወጡም ደረጃቸውን በማሻሻል ወደ ላይ ከፍ ብሏል።

1ኛ🔸አብዱ ኪያር (ገለመሌ) 🎶 1,024,491 እይታ
2ኛ🔸ሰላማዊት ዮሐንስ (ሰንቢደ) 🎶 717,604 እይታ
3ኛ አብዱ ኪያር (ፓ! ፓ! ፓ!) 🎶 522,697 እይታ
4ኛ🔻 አብዱ ኪያር (አይዞ) 🎶 509,086 እይታ
5ኛ አንዱዓለም ጎሳ (ቢሊሌ) 🎶 434,174 እይታ
6ኛ ሮፍናን (ሸግዬ) 🎶 349,646 እይታ
7ኛ🔻አብዱ ኪያር (ባይ ባይ) 🎶 332,182 እይታ
8ኛ🔸 አብዱ ኪያር (ቡቡዬ) 🎶 326,902 እይታ
9ኛ🔸 ናሆም መኩሪያ (ባዳ ባዳ) 🎶 320,199 እይታ
10ኛ🔸 ቬሮኒካ አዳነ (እናነይ) 🎶 304,092 እይታ

ደረጃ ያሻሻሉ
🔻 ደረጃ የቀነሱ
🔸ባሉበት ደረጃ የቆዩ

🎶 በሳምንቱ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት የታዩ ሙዚቃዎችን በትክክለኛ ዳታ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ምርጥ አስር ሙዚቃ ሰንጠረዥ ነው።

🎶 ቁጥሮች በሳምንት ውስጥ የጨመሩትን እይታ ብቻ ነው የሚያሳየው።

ቅዳሜ ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ከዛሬ 23 አመት በፊት 1993 ላይ "ለህይወትህ ዋጋ ስጥ" የተሰኘ በዘመኑ "ካርኒቫል" ባሁኑ ጊዜ ኮንሰርት እንደሚባለው ማለት ነው

ሙዚቃ ዳንስ፣ ቀልዶች፣ ፋሽን ትርኢት፣ የሰውነት ቅርፅ ውድድር፣ ዜማ ላስታ፣ ራፕ፣ ሬጌ ....... በዲኬቲ ኢትዮጲያ እና ፕሮሞተር ዲጄ ዚ ተዘጋጅቶ ነበር

ማንን አያችሁ ፖስተር ላይ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ንግድ ባንክ ያለኔ ፈቃድ የባንክ statement ለሌላ ሰው ሰጥቶብኛል " ዳግማዊት ፀሀዬ

#Ethiopia: አርቲስት ዳግማዊት ፀሀዬ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መልእክት አስተላልፋለች :- ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ officially ጥያቄ አለኝ ?
ለጊዜው ሀገር ውስጥ የሌለችው የሙዚቃ ዝግጅቷን በዱባይ እያቀረበች በመሆኑ አሁን ሃገር ውስጥ ስለሌለሁ አሁን head office መምጣት አልችልም ግን ካለ አንድ ሰው ፍቃድ የሰው አካውንት statement ለሌላ ሰው መስጠት ይቻላል እንዴት ያለ ስርአት ነው ፤
አልገባኝም ? ? በውስጥ የሚያወራኝ ተወካይ ካለ
ዝርዝር ጉዳዩን ላስረዳ ችላለሁ ብላለች ።

Via ዳግማዊት ፀሀዬ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1