ወንዲ ማክ በ'ይንጋልሽ' አዲስ አልበሙ "ምን ሰንቆልናል?"
የተለያየ ይዘት ያላቸውን (የማህበራዊ ህይወታችንን መልኮች አመላካች፣ ፍቅርን አንጋሽ፣ ጀግንነት አወዳሽ፣ ስህተቶችን ጠቋሚ፣ መልካም ነገሮቻችንን አስታዋሽ፣ ታሪክ ነጋሪና ዘካሪ የሆኑ) ነጠላ የሙዚቃ ስራዎቹን በማስደመጥ ከአገር ቤት አልፎ በመላው ዓለም ተወዳጅነትን ያተረፈው ታዋቂው ድምፃዊ ወንዲ ማክ፣ አሁን ደግሞ "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ የአልበም ስራውን ይዞ መጥቷል።
ከባለፈው አርብ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ "WendiMak" በተሰኘ የራሱ ዩቲዩብ ቻናል በመላው አለም እየተደመጠ ያለው አዲሱ አልበሙ 15 አዳዲስ ሙዚቃዎችን ያካተተ ሲሆን፣ በርካታ ባለሙያዎችም በቅንብርን ሚክሲንግ ተሳትፈውበታል።
"ይንጋልሽ" በተሰኘው በዚሁ የወንዲ ማክ አዲስ አልበም ውስጥ፣ እጅግ ልብን የሚነኩና የተለየ እይታውን በማሳየት የደረሰበትን ከፍ ያለ የሙዚቃ ስብዕና የሚመሰክሩ ስራዎች ተካተዋል። ይህም በበርካታ ባለሙያዎች ዘንድ አድናቆትና ምስጋና እያስቸረው ይገኛል።
*"ይንጋልሽ"
የአልበሙ መጠሪያ በሆነው "ይንጋልሽ" የተሰኘ ዘፈኑ ስለእናት አገሩ ኢትዮጵያ ያለውን ጥልቅ ፍቅር እየገለጸ፣ የገጠማትን ህመም ሲታመም ይደመጣል። ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ትወጣ ዘንድ በመመኘትም፤
"...ጨረቃ ካንቺ ርቃ፣
ጸሐይም ተደብቃ።
ነጎድጓድ ምን ቢሰማ፣
በርቺልን ይንጋ እማማ..." እያለ "ይንጋልሽ ይብራልሽ" ሲል የልብ መሻቱን (ምኞቱን) ይገልጻል።
* "ያመኛል"
የአገሩን ጉዳይ እያነሳ በኪናዊ ለዛ ሀሳብ በሚያጋራበት ሌላኛ "ያመኛል" የተሰኘ ዘፈኑ ደግሞ የአንድን ኢትዮጵያዊ ወታደር ገጸ ባህሪ ተላብሶ እናገኘዋለን። የዚህን ወታደር ጫማ በማድረግም በቆመበት ቆሞ ልስልስ ባለ ዜማና በሚንቆረቆር መሳጭ ድምጽ እንዲህ ይለናል፤
"...ውስጤ ርብሽብሽ ይልብኛል
ክፉ ሲሉሽ ይከፋኛል
ያመኛል ያመኛል
አንቺን ሲነኩብኝ ቅር ይለኛል
ተወርዋሪ
ኮከብ ሆኜ ተወርዋሪ
ወቶ አዳሪ
ላንቺ ክብር ተጋዳሪ
ሀገሬ...
ያዳመነው ሰማይ ገፎ እስኪጠራ
ላንቺ ገፊ ያን ተራራ
ኢትዮጵያዬ...
እንኳን አሁን ከምፃቱም ሞት ተውሼ
ላንቺ መቆም እኔ ክንዴን ተንተርሼ
ያዳቆነ ላቅስ ብሎ ቢንጠራራ
እንዴት ላይሽ ልጅሽ ቆሜ በኔ ተራ..."
ራሱ ግጥምና ዜማውን ደርሶት ኪሩቤል ተስፋዬ ደግሞ ቅንብሩን፣ ሚክሲንግና ማስተሪንጉን በሰራው በዚህ "ያመኛል" ዘፈን ውስጥ የወቶ አደሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ ምኞት ብቻ ሳይሆን በአገሩ ጉዳይ የማይደራደርበት ጽኑ እምነቱም በግልጽ ይታያል። ለሴት ፍቅረኛ የተዘፈነ እንዲመስል ተደርጎ የቀረበበት ጥበባዊ መንገድም "በአንድ ድንጋይ..." ይሉት አይነት ሆኖ ግርምትን ይጭራል።
* "ከላይ"
በዚሁ አዲሱ አልበም ውስጥ ከተካተቱት የሙዚቃ ስራዎች፣ በወንዲ ማክ ግጥምና ዜማው ተሰናድቶ፣ ሚካኤል ሀይሉ (ሚኪ ጃኖ) ቅንብርና ሚክሲንጉን፣ ኪሩቤል ተስፋዬም የማስተሪንጉን ድርሻ የተወጡበት "ከላይ" የተሰኘ ዘመናዊ ሙዚቃ አንዱ ነው።
ወንዲ ማክ በዚህ ሙዚቃ፣ ከግጥም ጥልቅ ሀሳቡና የዜማ ፈጠራ ክህሎቱ እንዲሁም ሙዚቃውን ከተጫወተበት የድምጽ ከፍታው ጋር ለመንፈሳዊነት ያለውን የልብ ቅርበት አሳይቶበታል።
"አርሰሽ አላበቀልሽው አለምልመሽ በአንቺ ጥረት
የአምላክ እጅ ስራ ነው ያስገርማል ያንቺ ውበት
ከላይ ነው ከላይ
ውበትሽ ከላይ..." በማለት ውበቷን በልኩ ካሳየን በኋላ መለስ ይልና እንዲህ ይላታል፤
"ውቀት ለአንቺ ሰጥቶ በወቅቱ በተራሽ
ባለቤቱ ሌላ ምን ይሆን ያኮራሽ
አይደለም ከምድር ላይ
ከላይ ነው ከላይ
ቢያስበው ቢፈርደው አንቺ እንድትሰሪ
እናትና አባትሽን ሲያገናኝ ፈጣሪ
አይደለም ከምድር ላይ
ከላይ ነው ከላይ
ሚዛን ብትደፊ ሁሉ ቦታ
ለሰው አይን ሆነሽ ውብ ስጦታ
ከአፍሽ ቃል ወጥቶ ግብ ሲመታ
ቀና በይ በይ
ከላይ ነው ከላይ..." ወንዲ በዚህ ዘፈን የአለሙ ሁሉ ባለቤት በሆነው ፈጣሪ ያለውን እምነት በመግለጽ "ሁሉ በእርሱ መሆኑን" ምስክርነት ሰጥቶበታል። ይህም ከጥበብ ፋይዳ አንጻር ሲታይ መቶ በመቶ ግቡን የመታ ያደርገዋል።
የወንዲ አልበም ዘፈኖች ሁሉም አስደማሚ ናቸው። ለማሳያ ያክል እነዚህን ጠቀስኩ እንጂ 15ቱም የየራሳቸውን ቀለም ይዘው በተናጠል ለመተንተን ምቹ ናቸው። "እህቴ" በተሰኘ ሙዚቃው ያነጸረው የእኛ እህቶች ውለታም ብቻውን ሙሉ ቀን ሊያወያየን ኃይል አለው። የተቀሩትን "ባረገኝ፣ ተናፍቀሻል፣ ባባትሽ፣ ሞላልኝ፣ ሳሚኝ፣ መልከኛ፣ ፍቅር ያልቃል፣ መርቲዬ፣ ሆይ ሆይታ" እና ሌሎቹንም ሁሉ እያነሱ መወያየት ይቻላል። አንዳንዴ ግን ሁሉንም ከመንካት ለአድማጭም ዕድል መስጠት ያስፈልጋል። ለዚህ ነው እኔ ቀሪውን ለእናንተ በመተው እዚህ ላይ የምሰናበተው።
በወንዲ ማክ "ይንጋልሽ" የጨለመው ሁሉ ይብራላችሁ!!
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music

👍1
በ1994 ዓ.ም የኤልያስ መልካ አሻራ ያረፈበት በሚክሲንግ፣ ቤዝ ጊታር እና አሬንጅመንት ድንቅ ብቃቱን ያሳየበት ለብዙዎቻችን ከሀገር ጫፍ እስከ ጫፍ 90's ላይ ከልጅ እስከ አዋቂ ትዝታ እንደ እሳት የሚጭር ድንቅ አልበም ነው።
ኢቫንጋዲ አልበም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ታትሞ ለገበያ የቀረበ ሲሆን Copyright አልበም በ CD ታትሞ ገበያ ያስጨነቀበት ጊዜ ነበር። የዚህ ሙዚቃ አልበም አርት እንደሚከተለው ሲሆን ሙሉ መረጃዎች ተቀምጠዋል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music
ኢቫንጋዲ አልበም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ታትሞ ለገበያ የቀረበ ሲሆን Copyright አልበም በ CD ታትሞ ገበያ ያስጨነቀበት ጊዜ ነበር። የዚህ ሙዚቃ አልበም አርት እንደሚከተለው ሲሆን ሙሉ መረጃዎች ተቀምጠዋል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music
❤2
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲዬ ከሞት ተረፈ
በቅርቡ ይለያል የተሰኘውን አልበሙን ለህዝብ አድርሶ በብዙዎቹ ዘንድ አድናቆትን ያተረፈው ድምፃዊ ቴዲዬ በቅርቡ ለሚያቀርበው የሙዚቃ ኮንሰርት አሜሪካ መግባቱ ይታወቃል።
ድምፃዊውም በአሜሪካ የጥቁሮች የነፃነት ቀን በሰፊው በሚከበርበት በ june 20 የሙዚቃ ቪዲዬ ቀረፃ ላይ በቦታው ላይ የነበረውን አከባበር በማስገባት እየቀረፀ በነበረበት ሰአት በቦታው ላይ በጋንግስተሮች መሃል በተነሳ ጠብ የሽጉጥ ተኩስ ተነስቶ በቀኑ ቦታው ላይ ከነበሩት ሰዎች 15 ሰዎች ሲቆስሉ 1 ሰው ሞቷል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_yo

👤 Abdu Kiar | አብዱ ኪያር
🎵 pee | ፓ
━━━━━━━━━━━━━━
➠ RELEASED: 2024
➠ GENRE: #Ethiopian
➠ TYPE: #Album
➠ TRACKS: 13
➠ FORMATS: #Mp3
➠ CHANNEL: @Waliyaentmt
━━━━━━━━━━━━
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Abdu_kiar #Album #Ethio_albums #Waliya_Entertainemnt

🔥1🙏1
"ዱርዬ ተሰብሰብ "
ከአመታት በፊት ተ/ሀይማኖት ፊትለፊት ያለው አንበሳ ጫማ መደብር ያለበት ህንጻ ሰፊ በረንዳ የጎዳና ተዳዳሪዎች መናሀሪያ ነበር ። እና እዚህ ቦታ ፌስታል ሙሉ ክትፎ ይዞ የሚመጣ አንድ ሰው ነበር ፨
ይህ ሰው ኬኔዲ መንገሻ ነው ፡፡ ኬኔዲ አንዳንዴ ነሸጥ ሲያደርገው ወደዛ ይሄድና ዱርዬ ተሰብሰብ እያለ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስቦ በጊዜው ተ/ሀይማኖት ሱማሌ ተራ አካባቢ ዝነኛ ከነበረው ግዛው ክትፎ ቤት ገዝቶ ያመጣውን ክትፎ አብሯቸው እየተሻማ ይበላና ለያንዳንዳቸው የሻይ ሰጥቶ በብርቱካንማ ሬኖ መኪናው ይሄዳል ።
.......
አስገራሚው ነገር ኬኔዲ የትኛውም ታዋቂ ሰው የማያደርገውን ይህን መሳይ ነገር ሲያደርግ. .. በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ዝነኛ ከነበሩ አርቲስቶች መሀከል አንዱ ነው ። ሆኖም ዝናው አንድም ቀን ትከሻውን አጉብጦት አያውቅም ።
.......
አንድም ቀን በኩራት ልቡ ሳያብጥ ፡ አንድም ቀን ላይ ሆኖ አድናቂዎቹን ቁልቁል ሳያይ ፡ እንደጠዋት ፀሀይ ብልጭ ብሎ አፍታም ሳይቆይ ይህችን ምድር ተሰናብቶ ሄደ ።
RIP
የሰውነት ጥግ ።