Waliya Entertainment
289 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
‘’ኪነ_ጥበብ እንደ ኢንዱስትሪ ‘’ በሚል ረዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረትን ያደረገ ‘’የሀሳብ መዋጮ’’ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

አዲስ አበባ | ሰኔ 12016 ትልልቅ ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረትን ያደረገውና በአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት የሚቀርበው ‘’የሀሳብ መዋጭ’’ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ሰርፀ ፍሬስብሃት የመነሻ ጥናት ጽሁፍ አቅርበው በመድረኩ ውይይት ተደርጓል፡፡ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዘርፍ እንደ ኢንዱስትሪ ለመቆጠር ቀሪ በርካታ ስራዎች ሊተገበሩ እንደሚገባ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡ዘርፉ ወደ ኢንዱስትሪነት እንዳያድግ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ አለመዘጋጀት፣የአይምሯዊ ንብረት ህግ ወደ መሬት ወርዶ አለመተግበርና ዘርፉን የሚደግፉ ተቋማት በበቂ መልኩ አለመኖራቸው እንደምክያት ተነስቷል፡፡ዘርፉ የኢንቨስትመንት መስክ በሚሆንባቸው አስቻይ ሁኔታዎች ዙሪያ በመድረኩ ሀሳብ ተወጥቷል ፡፡

የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ሂሩት ካሳው(ዶ/ር) በበኩላቸው የኪነጥበብ ዘርፉን ለማሳደግ ከተናጥል ሩጫ ይልቅ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የሀሳብ መዋጮ መድረክ የኪነጥበብ ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ሌሎች ተከታታይ መድረኮች እንደሚዘጋጁ ተነግሯል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
አሸናፊ ከበደ (ፕ/ር) : የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል

#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት በአሸናፊ ከበደ (ፕ/ር) ስም የሰየመውን የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል መርቀዋል፡፡

የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከሉ በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
🌟 Beyond the Screen 🌟

Join us for an unforgettable event with the legendary Dawit Tsige, one of Ethiopia's most celebrated singers!

📅 Date: Tuesday, June 11
Time: 2 PM (8:00 PM Ethiopian time)

📍 Location: US Embassy, Addis Ababa

Remember to bring your 🪪 ID and arrive on time, as seats are limited and reserved.

Secure your spot now by registering at the link below and be a part of this incredible experience! Don’t miss out on this unique opportunity.

📋 Register here ➡️
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ገና በጥንስሱ... ሃሳብ ሲያብሰለስል፣ እያነሳ ሲጥል፣ ነገር ሲያውጠነጥን፣ ድርሰቱን ሲወጥን፣ የምናብ ስሜቱን በፊደል ሲያስቀምጥ፣ ሌት ተቀን ቃል ሲያምጥ፣ ያሰበውን ሲጽፍ፣ የጻፈውን ሲቀድ፣ የቀደደውን ጥሎ ደግሞ መጻፍ ሲቀጥል... ይህን ሁሉ ሲያደርግ ከጎኑ ቁጭ ብዬ እያየሁት፤ እገረምም፣ እደነቅም፣ እጠይቅም ነበር።

መቼ ይሆን ውጥኑ ለፍሬ በቅቶ የማየው ብዬ እንደጠየቅኩ እነሆ ጊዜው ደርሶ በማየቴ ተደሰትኩ!

እንኳን ለዚህ በቃህ ወንድም አለሜ !"

ከብስራት ሱራፌል ለ ገጣሚ እና ዜማ ደራሲ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን
ሰኔ 16 ቀን 2016 ለህዝብ ይፋ ይደረጋል

#Ethiopia | የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን የምሰረታ ይፋ ማድረጊያ መረሐግብር ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ደራራ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ ፋውንዴሽኑ በሀገር ውስጥና በውጭ ከተመሠረተ ዓመት ቢሆነውም የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን ሰኔ 16 ቀን 2016 ለህዝብ ይፋ ይደረጋል።

አርትስቱ በህይወት እያለ ባህልንና ማህበራዊ ጉዳዮችን በዜማና በጥበብ ለህዝብ ሲያደርስ መቆየቱን አስታውሰው ፋውንዴሽኑ የአርቲስቱን ስራዎች ለማስቀጠል እንደምሰራ ገልፀዋል።ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የፋውንዴሽኑ ዳይሬክተር አቶ አሳድ ፋህሚ በበኩላቸው የፋውንዴሽኑ ዋና አላማ የአርትስት አሊ ቢራን ሥራዎችና ራዕዎችን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ነው ብለዋል።

በዚህም መሠረት ኪነጥበብን ማጎልበት፣ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ማስፋፋት፣ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ በጎ ሥራዎችን ማከናወን ላይ በትኩረት መሥራት የፋውንዴሽኑ አላማ መሆኑ ተናግረዋል።

የአርትስቱ ባለቤትና የፋውንዴሽኑ መስራች ወ/ሮ ኢሊሊ ማርቆስ ቢራ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ አልሞ የተነሳው አርትስቱ በህይወት እያለ መሥራት የሚፈልጋቸውን ስራዎች እውን ማድረግ ነው።

ይህ እንድሳካ ሀገር ውስጥ ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
በሐዋሳ እና አካባቢው ምትገኙ የማስተር ክላሱን የትምህርት እና በተግባር የታገዘ ልምድ ልውውጥ ለመካፈል የምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ሙዚቀኞች: አቀናባሪዎች : ድምፃዊያን : የግጥም እና ዜማ ደራሲዎች : ዲጄዎች : የድምፅ ቅጂ እና ማስተሪንግ ኢንጂነሮች : እንዲሁም በኢንተርቴመንት ማርኬቲንግ ስራ ላይ ለተሰማራችሁ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች እድሉ ለሚፈቅደው የ150 ሰው ምርጫ ውስጥ ለመግባት ለአጭር ጊዜ ምዝገባ ክፍት ነው:: ይህንንም ስናገር ለሀገራችን የሙዚቃ እና ኪነጥበብ ሚያበረክተውን በጎ አስተዋፆ በማሰብ ትልቅ ደስታ እና እድለኝነት ይሰማኛል:: ምስጋናዬ ለሚመለከተው ሁሉ ይድረስ::

ቦታው ሌዊ ሲኒማ

ቀን ሰኔ 11 እና 12

ሊንኩን በመጫን ለመመዝገብ ትችላላችሁ::

https://rophnanmasterclass.et/

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
🔥🔥ሽሙንሙን ተለቀቀ🔥🔥   

በቅርቡ ለእይታ የበቃዉ በቲክቶክ በሚሰራቸው ስራዎች ተወዳጅነትን ያገኘው #Beki4kilo የተሳተፈበት አዲስ የሙዚቃ ቪድዮ #ሽሙንሙኔ በተለቀቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ  ከ100,000 በላይ ተመልካች አግኝቷል።🙏

#Waliya_Entertainemnt
ስራውን ስለወደዳችሁልን እያመሰገንን ያላያችሁት
ሊንኩን ተጭነዉ ይመልከቱት በጣም ይወዱታል!!!

ሊንኩን እዚህ አለ👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/kdm1sFyM47w
"ይሄ እንደ ሐገር ሚያኮራ ነው 🇪🇹🇪🇹🇪🇹💪💪

የሐገራችን ሙዚቃ በዚህ ደረጃ ከፍ እንዲል የራሳቸውን አስተዋጽዎ ካበረከቱ ጥቂት ባለሙያዎች አንዱ በመሆንህ እና የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በቆሙበት መድረክ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለመቆም በመብቃትህ፥ ሀገሩንና የሀገሪቷን ኪነጥበብ እንደሚወድ፥ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት ትልቅ ኩራት ይሰማኛል።

በሙያህም የደረስክበት የስኬት ጥግ ሌሎች የሀገራችንን ሙያተኞች የሚያኮራና ለላቀ ስኬት የሚያበረታታ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ኪነጥበብ ታማኝ አገልጋይን ትሻለችና የጥረት ጉዞህን አጠንክረ መቀጠልህን ከሚመኙና ከሚደግፉ አንዱ ነኝ።

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) June 30 በ Coca Cola Arena ለምታቀርበው የሙዚቃ ድግስ ከወዲሁ መልካም የስራ ጊዜ ተመኘሁ።" - ያሬድ ነጉ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
1
በታዋቂው ራፐር ኤሚነም ተይዞ የነበረውን የፈጣን ራፐር ሪከርድ በአፍሪካዊው ራፐር ላይሪካል ጆ ተሰበረ

በአፍሪካ በፍጥነት ራኘ ማድረክ ከዚህ በፊት አንደኛ የነበረው ላይሪካል ጆ አሁን ደግሞ "ቴክ ኦፍ" በሚለው ሙዚቃው ላይ በ30 ሰከንድ ውስጥ ከ 240 በላይ ቃላቶችን ራኘ በማድረግ የኤምኔምን ሪከርድ ሰብሯል።

የኤምኔም ሪከርድ በ 30 ሰከንድ ውስጥ ከ 225 በላይ ቃላቶችን ራፕ በማድረግ ነበር ሪከርድ ይዞ ለረጅም ግዜ የቆየው።