Waliya Entertainment
289 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ተታረቁ!!!!

ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከውስጥ ሰዎች እውነታውን ለማጣራት እንደሞከረው ከዚህ በፊት በተፈጠረ ችግር ተወዳጇ ድምፃዊት ታምር ግዛው ሙሉ አልበም ከ ሙዚቃ አቀናባሪው ታምሩ አማረ እና ከ ዜማና ግጥም ደራሲው ናትናኤል ግርማቸው ጋር እየሰሩ በነበሩበት ግዜ በአንዳንድ ምክንያቶች ተጣልተው እንደነበር በዚህም ምክንያት ለታምር ግዛው ሊሰራላት የነበረው ሙሉ አልበም በጠቡ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ለ ታዳጊዋና ተወዳጇ ድምፃዊት ቤቴልሄም ሸርፈዲን እንደተሰጠ #waliya_entertainment ያጣራ ሲሆን ነገር ግን አሁን ከብዙ ጊዜ ክፍተት በዃላ በይቅርታ ድጋሜ እንደተታረቁ ለማወቅ ችለናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
😱1
" እናቴ አባቴን ለማስታመም ስትል የጠወለገች ፡ አበባ ነበረች "

ከበፊት ጀምሮ ድምጻዊ ቡዜማንን በተመለከተ ብዙ ሞራል የሚነኩ ቀልዶችን እናያለን ፡ ግን እያንዳንዱ መርዛማ ቀልድ ይህንን ወጣት ሊጎዱ እንደሚችሉ አስበን አናውቅም ።

ቤተሰቡን ለማኖር ፡ ለአመታት ታመው ያለፉትን አባቱን ለማስታመም ሲሉ የተንገላቱ ፡ የደከሙ ፡ በመጨረሻም አባቱ ካለፉ በኋላ ፡ በህመም ላይ የወደቁትን እናቱን ለመርዳት ፡ እህቱን ለማስተማር ፡ ክለብ ዘፍኖ ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር ለሊቱን እያነጋ ህይወትን ለማሸነፍ ፡ በሙያው የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚጥር እናውቅም ። ግን ሳይደርስብን ለርካሽ ላይክ እና ሰውን ለማሳቅ ብለን የሰወችን ልብ እናቆስላለን ። ይህ ጉዳይ በጣም እጅ እጅ ስላለ ነው ዛሬ ሰይፉ ቡዜማንን ተፋቱት ያለው ።

ይህ ጉዳይ ዛሬ በቡዜማን ሰማነው እንጂ የብዙ ሰወች ታሪክ ነው ። ከያንዳንዱ ሙድ ከምንይዝበት ሰው ጀርባ ያለውን ታሪክ አናውቅም ። ለርካሽ ላይክና ለአጉል ቀልድ ስንል ሰወች ላይ ባንዘባበት መልካም ነው ።

✍️ዋሲሁን ተስፋዬ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
❣️ ማያዬ
ኤልያስ መልካ የተሳተፈበት አልበም ለሕዝብ ሊቀርብ ነው

#Ethiopia | ተዋናይት እና ድምፃዊት ለምለም ሐ/ሚካኤል አዲስ የበኩር አልበም ከዘጠኝ አመት በኃላ "ማያዬ " የተሰኘው አልበም ላይ የተሳተፉ የተለያዩ አንጋፋ እና ወጣት ከያኒያን ሲሆኑ በሕይወት የሌለው አንጋፋው አቀናባሪ ኤልያስ መልካ ሲገኝበት ሌሎች አንጋፋና ወጣት ባለሞያዎችም ተሳትፈውበታል።

#በሙዚቃ ቅንብር
👇👇👇
🎹አበጋዝ ክብረወርቅ
🎹ኤልያስ መልካ
🎹ሚካኤል ሃይሉ
🎹ታምሩ አማረ
🎹አዲስ ፍቃዱ እና ብሩክ ተቀባ ተሳትፈዋል።

#በግጥም
👇👇👇
✍️ወንድወሰን ይሁብ
✍️ናትናኤል ግርማቸው
✍️ሀብታሙ ቦጋለ
✍️ጥላሁን ሰማው የተሳተፉ ሲሆን፤

#በዜማ
👇👇👇
🎹ኤልያስ መልካ
🎹አንተነህ ወራሽ
🎹እሱባለው ይታየው
🎹ብስራት ሱራፌል
🎹ዘርአ ብሩክ ሰማው
🎹አህመድ ተሾመ ( ዲንቢ ) ተሳትፈዋል ።

👉በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሰለሞን ኃይለማርያም
👉በሪከርዲንግ ፕሮዲውሰርነት (Music producer, record producer) ወንድወሰን ይሁብ ተሳትፈውበታል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Lemlem_mayaye
5
የካሣሁን እሸቱ (ካስዬ) የአልበም ምርቃት በ ማርዬት ሆቴል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የውዝዋዜ ጥበብ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ

#Ethiopia| የኢትዮጵያ የውዝዋዜ ጥበብ ማኅበር ፣ ከዓለም የትምህርት ፣ ሳይንስና የባህል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለስድሰት ቀን የሚቆይ ስልጠና እና የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ተወዛዋዦች ጥበብ ማህበር ጉባኤ በፈንድቃ ባህል ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።

"ዳንስ፣ ባህል እና ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ የማኅበሩ አባላት እና ለአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቴአትር ጥበብ ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ድግሪና የፒኤች ዲ ተመራቂዎች በተገኙበት ከባሳለፍነው ሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በፈንድቃ ባህል ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ተወዛዋዦች ጥበብ ማህበር መስራችና ፕሬዚዳንት ፣ የፈንድቃ የባህል ማዕከል ባለቤትና የኢትዮ-ከለር ባንድ መስራች አርቲስት መላኩ በላይ የስልጠናውን አስፈላጊነት እና ዓላማ የገለጹ ሲሆን ሌሎች ክውን ጥበባት ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ሦስተኛ ድግሪ ትምህርት የሚሰጥባቸው ዘርፎች ያላቸው እና እስካሁን የውዝዋዜ ጥበብ ግን በድግሪ ደረጃ የትምህርት ዘርፍ እንደሌለው የውዝዋዜ ጥበብ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዲካተት ጥረት እንደተጀመረም ተናግረዋል።

“የኢትዮጵያ የውዝዋዜ ጥበብ ማኅበር" በ2010 ዓ.ም የውዝዋዜ ባለሙያዎችን መብት ለማስጠበቅና ሙያዊ አቅምን ለማጎልበት ታስቦ የተመሰረተ ሲሆን እስካሁንም ድረስ በመላው ኢትዮጵያ የማኅበሩን ቅርንጫፍ ቢሮ በማቋቋም ለሙያተኞች ከውጭ ሀገር ከመጡ የዘርፉ ምሁራኖች ጋር የልምድ ልውውጥ መድረኮችን አና ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ተገልጿል።

Telegram - https://t.me/waliyaentmt