Waliya Entertainment
287 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የዳግማዊት ፀሀዬ "ወርቅ" አዲስ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ማታ 12 ሰአት ላይ ለአድማጭ ሊቀርብ ነው::

ድምፃዊቷ "ወርቅ" የሚል ስያሜ በሰጠችው በእዚህ የአልበም ስራ በፕሮዲውሰርነት እንዲሁም በአቀናባሪነት ትልቁን ተሳትፎ ከማድረግ አንፃር የሙዚቃ ባለሙያው አቤል ጳውሎስ ከፍ ያለ ሚና መወጣቱን ለ ዋልያ ኢንተርቴይመንት የገለፀች ሲሆን በርካታ ባለሙያዎች በተካፈሉበት በእዚህ የአልበም ስራ ውስጥ ለትዳር አጋሯ አርቲስት ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ) ያቀነቀችው ሙዚቃ እንዳለበትም አያይዛ አንስታለች።

አልበሙ ዛሬ ማታ (አርብ ታህሳስ 12 ቀን 2016ዓ.ም) በሁሉም አማራጮች እና መተግበሪያዎች በኢትዮጵያ እንዲሁም በተቀረው አለም እንደሚሰራጭ አስታውቃለች።

የስቱዲዮ ቁጥር ማነስ እና የባለሙያዎች እጥረት አልበሙ ፈጥኖ እንዳያልቅ ምክንያት ሆኗል የምትለው ድምፃዊቷ መቆየቱ ግን የተሻለ ስራ እንድሰራ አድርጎኛል ስትል ተናግራለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Dagimawit_tsehaye #werk_album
👍1
ተወዳጁ ድምፃዊ እና ዳንሰኛ “ ሳንቾ “ የልጅ አባት ሊሆን ነው

* ሳንቾ ና በእምነት እንኳን ደስ አላችሁ
መልካም የትዳር ዘመን ይሁላችሁ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ዳግማዊ አሊ ጆሮዬን ቃኝቶታል"

ድምፃዊት ሄራን ጌዲዮን

ሄራን ጌዲዮን ከ4 አመት በኃላ ዝነኛው ዳግማዊ አሊ በሙዚቃ ቅንብር የተሳተፋበት አልበሟ ሊወጣ ነው::

"ባይ ባይ" በሚለው የመጀመሪያ ነጠላ ዜማዋ እንዲሁም የ80ዎቹ አጋማሽ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎችን በማቀንቀን የምትታወቀው ሄራን አዲስ አልበሟ ስለመጠናቀቁ ማርጋገጫ ሰጥታለች::

ሄራን ለአልበሙ መዳረሻም "አባብዬ" የተሰኘውን እና ተወዳጁ ድምፃዊ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲው ብስራት ጋረደው ስራ የሆነውን አዲስ ነጠላ ዜማ ለአድማጭ አድርሳለች::

ከመሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረገችው ድምፃዊቷ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ካደረሰቻቸው ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎች ማግስት በሙሉ የአልበም ስራ እንደምትመጣ ብትጠቁምም የአልበሙ መውጫ ጊዜ እንዳልተቆረጠ አስታውቃለች።

ከሶስት ዓመታት በፊት ከእዚህ ዓለም በሞት የተለየው ዕውቁ የሙዚቃ ባለሙያ ሱራፌል አበበን ጨምሮ በሙሉ የአልበም ስራ ከሙዚቃ ከመድረኩ የራቁት ብስራት ጋረደው እና ዳን አድማሱ እንዲሁም ቢኒአምር አህመድ በሄራን አዲሱ አልበም ስራ ላይ በግጥምና ዜማ ተሳትፎ ማድረጋቸውን አስታውቃለች።

ተወዳጁ የሙዚቃ ባለሙያ ዳግማዊ አሊ ፕሮዲውስ ባደረገው በእዚሁ አልበም ላይ በቅንብርም አሻራውን ከማሳረፍ ባለፈ "እራሴን እንዳገኝበት አድርጓል "ስትል ከመሰንበቻ ጋር በነበራት ቆይታ አንስታለች።

ናትናኤል ሀብታሙ አዘጋጅቶታል
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt
👍2
ተወዳጁ ድምፃዊ እና ዳንሰኛ “ ሳንቾ “ የልጅ አባት ሊሆን ነው

* ሳንቾ ና በእምነት እንኳን ደስ አላችሁ
መልካም የትዳር ዘመን ይሁላችሁ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ተወዳጇ ድምፃዊት ሚካያ በሀይሉ ህይወቷ ካለፈ ነገ ታህሳስ 15/2016ዓ.ም አስር አመት ይሞላታል::

👉በድምጷ ለዛ እና ውበት የሚደመሙ እንከን የለሽ አንጎራጓሪ ሲሉ ይገልጿታል።

👉 "የቀለም እናት ድንቅ መምህርትም ”ሲሉ የሚያሞካሿት ይህቺ ብርቱ ሴት ወደ ጋዜጠኝነቱም ጎራ ለማለትም ውጥን ነበራት።

👉ከልጅነቷ ጀምሮ ወደ ሙዚቃው ዓለም ያዘነበለችዋ ሚካያ የነብሷ ጥሪ ስምረት ተሞላበትና በ1980 ዎቹ አንድ አልበም ሰርታ ነበር።ያም ሆኖ ይህ አልበሟ በሚታሰበው ልክ ተደማጭ መሆን አልቻለም።

👉 ድምፃዊቷ በእዚያ ወቅት ላይ ባቀረበችው አልበም ራሷን ያገኘችበት ሳይሆን በአንጋፋዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀ የድምፅ ቀለም ተውጣ አሊያም ተፅዕኖ አርፎባት እንደነበር ይገለፃል።

👉 ያም ሆኖ ግን የነበራትን እምቅ አቅም መረዳት የቻለው ኤልያስ መልካ ድምፃዊቷን ዳግም ፈጠራት በሚያስብል ደረጃ እራሷን እንድታገኝ ምክንያት ሆኗል።

👉 "ሸማመተው" አልበም ከበገና ስቱዲዮ በላቀ ከፍታ መውጣት ችሏል። በስራዋ ውስጥ ከተካተቱ ሙዚቃዎች መካከል "ደለለኝ" የተሰኘው ስራ የአህጉሪቱ የውድድር መድረክ በሆነው ኮራ አዋርድ ላይ መውጣት ችሎ ነበር።

👉 ከድምፃዊነቱ ባሸገር የግጥምና ዜማ ድርሰት ላይም ድንቅ የሚባል አቅም እንደነበራት ይገለፃል። በ"ሸማመተው" አልበም ውስጥ የተካተተው "ሰበቤ ሁን ሲልህ" ሙዚቃ የዜማ ባለቤትነት የራሷ መሆኑ አንደኛው ማሳያ ነው።

👉 ይህቺ ተወዳጅ ድምፃዊት ልክ በዛሬው ቀን ታህሳስ 15 ቀን 2006 ዓ. ም ላይ ነበር ከእዚህ አለም በሞት የተለየችው።

Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
ተወዳጁ ድምፃዊ አብሌክስ እና ታዋቂ ኮንቴንት ክሬተሯ አናስታሲያ የልጅ አባት ሊሆን ነው

👉አብሌክ እና አናስታሲያ እንኳን ደስ አላችሁ
መልካም የትዳር ዘመን ይሁላችሁ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የማን አድናቂ ኖት?
ቴዲ አፍሮ እና ልኡል ሲሳይ Vs ጎሳዬ ተስፋዬ እና መሳይ ተፈራ?