Waliya Entertainment
293 subscribers
1.57K photos
16 videos
762 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ አንደኛ አመት መታሰቢያ

#Ethiopia | ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በሙዚቃ ስራዎቹ ከፍተኛ እውቅናን እና አድናቆትን ከማትረፍም በላይ በተለያዩ ቋንቋዎች የተጫወታቸው ሙዚቃዎች ዘመን ተሻጋሪ እና ሁሌም የሚደመጡ ናቸው ።

ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ጥቅምት27/2015 ዓ.ም ህይወቱ ያለፈ ሲሆኑ የአርቲስቱን አንደኛ አመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግም በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ ከፊታችን ሰኞ አንስቶ በተከታታይ አምስት ቀናት በተለያዩ መርሀ-ግብሮች እንደሚከበር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተናግረዋል ።

የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀ-ግብሮችም የጧፍ ማብራት ስነ-ስርአት ፣ የቢልቦርድ ምርቃት ፣ የፓናል ዲስከሺን ፣ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ፣ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ፣ በምድር ባቡር አደባባይ ላይ የሚዘጋጅ ኮንሰርት እንዲሁም በክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስም በተሰየመው ፓርክ ውስጥ የተለያዩ ፕሮግራሞች እንደሚዘጋጁ ገልፀዋል።

ክቡር ከንቲባ በዛሬው እለት ለሚዲያ ባለሞያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነዋሪው ህብረተሰብ በተዘጋጁት መርሀ-ግብሮች ላይ እንዲገኙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በይድነቃቸው አብርሃም
Waliya Entertainment

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent
#Ethiopia #Ethiopian_music