Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.7K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
አምሮትና እርግዝና

🖲 አንዳንድ ሴቶች አማረኝ የሚሉት ነገር ሲበዛ፣ በእርግዝና ግዜ እንዲሁም የተለያዩ ባእድ ነገሮችን መመገብ ሲመኙ ካጋጠማችሁ።

🖲 PICA ይባላል በስነአእምሮ ህክምና

🖲ከማህበረሰቡ ስርአተ አመጋገብ የወጣ እና ከምግብ ዘርፍ የማይመደብ ባእድ ነገር መመገብን ያመላክታል

🖲በምን መልኩ እንደሚመጣ የሚያሳውቅ ግልፅ የሆነ አንድ መንገድ ባይኖርም ነገር ግን አፈር መቃም በረዶ ማኘክ የመሳሰሉ በህሪዎችን የሚያሳዩ ነብሰ ጡሮች አብዛኛውን ግዜ በእርግዝናቸው ወቅት በቂ የሆነ ክብደት የማይጨምሩ እና እንዲሁም የ iron zink እና calsium የመሳሰሉ ጥቃቅን ንጥረ ነገሮች እጥረት የሚታይባቸው  ናቸው።

🖲 ይህ ሁኔታ ከፍ ያለ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ይልቅ ዝቅ ያለ የኑሮ ደረጃ የሚመሩ ማህበረሰቦች ላይ ያመዝናል።

🖲አፈርን እንዲሁም ባእድ ነገርን መመገብ፣ ለተጓዳኝ በሽታ አጋላጭ ከመሆኑ ባሻገር ምንም ጥቅም የለውም።

👉በእርግዝና ወቅት በቂ የሆነ እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
👉ከጤና ባለሞያ የሚሰጡ ምክሮችን እንዲሁም
👉የቅድመወሊድ ክትትል ማድረግ ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች በቶሎ ለመፍታት ያስችላል።

🖲በዚህ እና በማህፀን እና ፅንስ ህክምና ጉዳይ ከዶ/ር ቤቴል ደረጄ ( የማህፀን እና ፅንስ ስነ ካንሰር ሀኪም) የበለጠ መረጃና ተጨማሪ ህክምና በዊኬር አፕሊኬሽን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

👇👇👇👇👇👇

🖲መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
ሐኪሞችን ለማግኘት መተግበሪያውን በመጫን ቀጠሮ ይያዙ።

telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb

ዶ/ር ሰይፈ
👍231🥰1
ቀድሞ የመጨረስ ችግር

🖲አስቀድሞ የመጨረስ ችግር፣ በስነ እምሮ ህክምና መስፈርት ያለው ትርጓሜ

አንድ ወንድ በተሳተፈባቸውን ግንኙነቶች ለይ ፣ 75 በመቶ እና ከዛ በላይ የሚሆኑት የተጠናቀቁት ከ 1 ደቂቃ በታች ከሆነ።

ይህ ችግር በጌዜ ሂደት ሳይሻሻል 6 ወር እና ከዛ በላይ ከቆየ ከሆነ እና የስነልቦናዊ ጫና ካሳደረ።

እንዲሁም ከተጓዳኝ መዳኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት፣ የስነ አእምሮ ፣ እና የውስጥ ደዌ በሽታዎች ጋር የማይገናኝ ሲሆን።

👉ቶሎ የመጨረስ ችግርን ያመላክታል።

🖲የግንኙነት ቆይታ ግዜን መስፈርት በማረግ  ከፍተኛ፣ ዝቅተኛ ና መለስተኛ ተብሎ በሶት ደረጃዎች ይከፈላል።

ከፍተኛ፣- ግንኙነት ሳይጀመር፣ ወይም ግንኙነት በተጀመረ በ 15 ሰከንድ ውስጥ የሚያልቅ።

መለስተኛ፣ ግንኙነት ተጀምሮ ከ 15 እስከ 30 ሰከንድ ውስጥ ሲጠናቀቅ።

ዝቅተኛ፣- ግንኙነቱ ከ 30 ሰከንድ እስከ 1 ደቂቃ ባለው ግዜ ውስጥ ሲጠናቀቅ።

🖲ቀድሞ የመጨረስ ችግር፣ ከመጀመሪያ ግንኙነት ጀምሮ አብሮ የነበረ ወይም ፣ከግዜ በኋላ የመጣ ሊሆን ይችላል

🖲ለዚህ ችግር መፍትሔ የሚሆኑ ፣  በግንኙነት ግዜ የሚደረጉ ተግባሮች
👇👇👇 👇👇👇
👍9627😱14🙏1
ይቅርታ፣ ይህ 👉 @LEKETERO የክሊኒክ አድራሻ ነው ለቀጠሮ ብቻ ምልክቱን ተጭነው ስም እና ስልክ ያስቀምጡ

ለጥያቄ ይሄን ይጠቀሙ👉https://t.me/seifemedask
በስልክ ለማግኘት ከሆነ ለ ዶ/ር ሰይፈ +251974163424 ይደውሉ፣ ማታ ከ 12 ሰአት በኋላ እና ስራ ላይ ከሆነ ስልክ ስለማያነሳ በሌላ ግዜ ደግመው ይደውሉለት።

telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍10033😱10🥰9🤔7🙏7👏6🎉3🤩2🏆1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአይን መርገብገብ 

🖲 የላይኛው ወይ የታችኛው የአይን ክዳን ሲንቀጠቀጥ፣ ማንን ልናይ ነው ወይ በምን ልናለቅስ ነው ይባላል በተለምዶ

eyelid myokemia ይባላል በህክምናው።

🖲በአይን ክዳን ዙሪያ የሚገኙ ጡንቻዎች፣ ከቁጥጥር ውጪ ስስ የሆነ እንቅስቃሴ ሲኖራቸው የሚፈጠር ሁኔታ ነው።

🖲አብዛኛውን ግዜ በአንድ አይን ብቻ የተገደበ ሆኖ ከላይኛው ይልቅ የታችኛው የአይን ክዳን ላይ አዘውትሮ የሚታይ፣ በራሱ ግዜ የሚጠፋ እና ከምንም ተጓዳኝ ህመም ጋር ያልተገናኘ ሁኔታ ነው።

🖲አንዳንድግዜ ቡና በተደጋጋሚ ከመጠጣት ጋር ተያይዞ፣ እንዲሁም ጭንቀት እና ድካም ባለበት ሁኔታም ሊታይ ይችላል

🖲ነገር ግን፣ ለረጅም ግዜ የቆየ ከሆነ እና እንዲሁም አይን በተደጋጋሚ የማስጨፈን ጥንካሬ ካለው፣ የአይን መቅላት እና
ከአይን አልፎ የፊት ጡንቻዎች ላይ የሚታይ ከሆነ ሀኪምጋ መቅረብ ያስፈልጋል።

telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍504🙏2
poisining

መመረዝ

ክፍል 2


👉በእባብ መነደፍ (በእባብ መመረዝ)

👍የእባብ መርዙን በአፍ መጦ ለማዉጣት አይሞክሩ።

👍መርዙ በፍጥነት በደም ስርጭት ወደ ተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች እንዳይዛመት የሚከተሉትን ያድርጉ።

🎇 የተመረዘዉን የሰዉነት ክፍል ከልብ በታች ያድርጉ።

🎇 የሰዉነት እንቅስቃሴ ና በፍጥነት መንቀሳቀስን ይቀንሱ።

🎇ከቻሉ በጎን በኩል በመተኛት እረፍት ያድርጉ

👍ከተነከሰዉ አካል በላይ ያለዉን የሰዉነት ክፍል ማሰር የራሱ ጉዳት ያለዉ ቢሆንም ህክምና ቦታ ለመድረስ ከ 3 ሰዓትበላይ የሚፈጅ ከሆነ የመርዙን ስርጭት ለመቀነስ ይረዳል።

👍ከተነከሰዉ አካል በላይ ያለዉን ክፍል ጥብቅ አድርገዉ አይሰሩ።ይህ የደም ዝዉዉርን ሊጎዳ ይችላል።

👍እንደ ቀለበት ጌጣጌጥ ያሉ ነገሮች ካሉ ያዉልቁ ።

👉እብጠት ካለ የደም ዝዉዉርን ሊቀንሱ ይችላሉና ከቻሉ ወደ ሆስፒታል ሲመጡ የነደፈወትን እባብ ይዘዉ ይምጡ ።

👉መርዛማ መሆን አለመሆኑን ለመለየት ለሀኪሞች እገዛ ስለሚያደርግ ነዉ።

👉መርዛማ ከሆኑ እባብ መለያወች ዉስጥ የሶስት ማዕዘን ጭንቅላት ና ሞላላ የአይን ብሌን(pupil) ያላቸው ጥቂቶቹ ናቸዉ።


ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ
👍31🥰21
ቃጠሎ(BURN)

👉ቃጠሎ ሰዉነታችን በእሳት ሲያያዝ የሚከሰት ነገር ብቻ አይደለም።በኬሚካል፣በጨረር ወይም በኤሌክትሪክም ሊከሰት ይችላል።።
✍️ቃጠሎዉን ባስከተለዉ መንስኤ እንደሚከተለዉ ይከፈላል።።
🎇የእሳት ቃጠሎ..dry heat (የሚነድ እሳት)ወይም scald(ምሳሌ የፈላ ዉሃ)
🎇የኤሌክትሪክ ቃጠሎ
🎇የኬሚካል ቃጠሎ..አሲድ ወይም ቤዝ ሲደፋ የሚከሰት
🎇የጨረር ቃጠሎ..ሰዉነታችን ከሚችለዉ በላይ እንደ x.rayላሉ ጨረሮች ሲጋለጥ የሚከሰትነዉ።
👉በሚደርሰዉ የቃጠሎ ደረጃ እንዲህ ይከፈላል።

ሀ..አንደኛ ደረጃ ቃጠሎ-ይህ የቆዳ የላይኛዉ ክፍል በከፊል ሲጠቃ የሚከሰት ነዉ።

ለ..ሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎ..ይህ ደረጃ የላይኛዉ የቆዳ ክፍልና ዉስጠኛዉ የቆዳ ክፍል በከፊል ሲያጠቃ የሚከሰት ነዉ።

ሐ..ሦስተኛደረጃ ቃጠሎ..ይህ ዉጨኛዉና ዉስጠኛዉ የቆዳ ክፍል በሙሉ ሲያጠቃ የሚከሰት ነዉ።

መ..አራተኛ ደረጃ ቃጠሎ.ይህ ሁሉንም የቆዳ ክፍሎች አልፎ ጡንቻና ሌሎች ክፍሎችን ሲያጠቃ የሚከሰት ነዉ።።
👉ቃጠሎ ሲከሰትምን ማድረግ አለብን።
✍️ከቃጠሎዉ ቦታ ቶሎ አንስተን ንፁህ አየር ወዳለበት ቦታ መዉሰድ።
✍️የተቃጠለዉ ቦታ ላይ ሊጥ ቭዝሊን ና ሎሎች ቅባቶች አለማድረግ።
✍️አሲድ ወይም ቤዝ የተደፋበትን በዉሃ ብቻ አጥቦ(Irigate with water)ሆስፒታል መዉሰድ።
✍️ኤሌክትሪክ ለያዘዉ ሰዉ ደግሞ ቶሎ ኤሌክትሪኩ እንዲቋረጥ ማድረግ ና ቶሎ ሆስፒታል መዉሰድ ናቸዉ።።
👍👍ህክምናዉ እንደቃጠሎዉ ደረጃ ና አንደተቃጠለዉ የሰዉነት ክፍል ብዛት ይወሰናል ።ስለዚህ ቶሎ ሆስፒታል መወለሰድ ያስፈልጋል።
ዶ/ር ዮርዳኖስ.
👍331👏1😱1😢1🤩1
ቁንጭር(የቆዳ ሌሽማኒያሲስ)


🖲 ቁንጭር ሌሽማኒያ በሚባል ጥገኛ ተውሳክ ዝርያ የሚመጣ በሽታ ሲሆን በሴቷ  የአሸዋ ትንኝ sand fly አማካኝነት ይተላለፋል።

🖲በሽታው በሰውነት ውስጥ እና በቆዳ ላይ የሚከሰት ሲሆን የውስጥ አካል ሌሽማኒያሲስ በቆላ አካባቢ የሚታይና በአግባቡና በቶሎ ካልታከሙት ጉበትን በመጉዳት እስከ ሞት የሚያደርስ ነው።

🖲 የውስጥ አካል ሌሽማኒያስስ ትንኟ ከተናደፈች ከወራቶች በኋላ የሚጀምር ሲሆን ምልክቶቹም

👉 ለረጅም ግዜ የቆየ ትኩሳት
👉የሰውነት መጥቆር
👉ድካም ድካም ማለት
👉የሆድ እብጠት የመሳሰሉት ይገኙበታል

🖲ሌላኛው አይነት የቆዳ ላይ የአፍ፤ አፍንጫ ህብረ ህዋስ ሽፋን ሌሽማኒያሲስ በወይናደጋማና ደጋማ አካባቢዎች የሚታይ ሲሆን በተለይም ስስ የሰውነት ክፍል ላይ እየሰፋ የሚሄድ ቁስል በመፍጠር ዘላቂ የአካልና የስነ ልቦና ጉዳት ያስከትላል

🖲 ይሁን እንጂ እንዳገኘሁት መረጃ በዚህ በሽታ ተጠቂ የሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም (በሳሪስ እና በመገናኛ) አካባቢ የሚኖሩ ግለሰቦች በ አለርት ሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲያደርጉ እየታዩ ነው።

🖲ይህ በሽታ ሰዎችን የሚይዘው ከ20 አይነት በሚበልጡ ጥገኛ ተውሳክ ዝርያዎች አማካኝነት ሲሆን በሀገራችን ከ99.9% በላይ የሚሆነው ጥገኛ ተውሳክ ሌሽማኒያ ኢቶፒካ በመባል ይታወቃል።

🖲የቁንጭር መተላለፊያ ዑደት እና መንገዶች አሁንም በመጠናት ላይ ሲሆኑ እስካሁን ያሉት የቅርብ ጥናቶች በሽታውን አምጭ ጥገኛ ተውሳክ ተሸካሚ ናቸው ተብለው ከሚታሰቡት በድንጋያማ እና ገደላማ ቦታዎች የሚኖሩት አሽኮኮ(hyraxes) እና ሌሎች አጥቢዎች በሴቷ አሸዋ ዝንብ ንክሻ አማካኝነት ይተላለፋል።

🖲 ህክምናው አስቸጋሪ ስለሆነ ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየውን አይነት የቆዳ ለውጥ ሲመለከቱ በቶሎ የቆዳ ሀኪምን እንዲያማክሩ አሳስባለሁ
👍16
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ
ይሄን ተጭናችሁ 👉 @LEKETERO
ስም እና ስልክ አስቀምጡ

https://t.me/seifemed
https://t.me/seifemed
🥰3
የመሀፀን ፈሳሽ

🖲 አንድ ለ አቅመ ሄዋን የደረሰች ሴት፣ በአማካይ በቀን አንድ የሻይ ማንኪያ (1.5 g) የሚሆን ጤናማ የመሀፀን ፈሳሽ ሊኖራት ይችላል።

🖲ጤናማ የመሀፀን ፈሳሽ የወር አበባ ኡደትን ተከትሎ መጠኑና ይዘቱ ይቀያየራል። ይዘቱም ቀጭን ውሀ መሰል አንዳንዴ ነጣ ያለ መጥፎ ጠረን የሌለው መሆን አለበት።

🖲ይህ ፈሳሽ መነሻው መሀፀን በር ላይ ከሚገኙ ሙከስ አመንጪ ጥቃቅን እጢዎች እና የተቀረው ደሞ በመራቢያ አካል ግድግዳ ላይ ከሚገኙ ፈሳሽ አመንጪ እጢዎች ሲሆን፣ አብዛኛው የፈሳሹ ይዘት በመሀፀን በር አካበቢ ይጠራቀማል።

🖲የጤናማ ፈሳሽ ባህሪዎች

👉የወር አበባ እንዳለቀ የሚያጣብቅ እና ወፍራም ይዘት አለው

👉ከ ሁለት ሳምንት በኋላ  እንቁላል ወደመሀፀን ሲለቀቅ መጠኑ ይበዛና ይዘቱም ውሀ መሰል፣ የሚሳብ አይነት በህሪ ይኖረዋል

👉ቀጣይ  የወር አበባ ሲሰናዳ ደሞ ቀድሞ የነበረውን አይነት እና መጠን ተመልሶ ይይዛል።

👉በግንኙነት ግዜ እና ተነሳሽነት ሲኖር፣ የዚህ ፈሳሽ መጠን ይጨምራል።

🖲 ጤናማ ያልሆነ የመሀፀን ፈሳሽ ምልክቶች

👉ይዘቱ ቀለሙና ጠረኑ የተለወጠ ከሆነ
👉ማሳከክ እና ከ እንብርት በታች ህመም ካለ፣
👉በግንኙነት እና ከወር አበባ ጋር ተያይዞ ከግዜ በኋላ የመጣ ህመም ካለ።

🚩 ሀኪምን ማማከር ግድ ይላል።

telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍603😱1
ፈለግ

🖲ፈለግ በዋነኝነት የሚከሰተው በቆዳ ድርቀት ምክኒያት ነው፣ ፈለግ በተደጋጋሚ የሚያስቸግረው ሰው ካለ በዋነኝነት የእጅ ድርቀትን መከላከል ይኖርበታል

🖲ፈለግ የሚያስከትሉ ምክኒያቶች

👉እጅን በተደጋጋሚ ግዜ በልብስ ሳሙና መታጠብ
👉የቆዳ ቁጣ፣ የምግብ እጥረት
👉ቅዝቃዜ፣ዲተርጀንት፣ ኬሚካሎች እና ከመሳሰሉት ጋር
👉ለረጅም ግዜ የቆዳ ንክኪ ማረግ አጋላጭ ምክኒያቶች ናቸው

🖲 Vit C እና Vit C በውስጣቸው የሚይዙ የቆዳ ማርጠቢያ (moisturizer) ክሬሞችን አዘውትሮ በመጠቀም እና ለአጋላጭ ምክኒያቶች ትኩረት በመስጠት ይህን ችግር በቀላሉ ማስወገድ ይቻላል።

🖲 ነገር ግን በቦታው ላይ ከፍተኛ እብጠት ካለ እንዲሁም መግል የያዘ ከሆነ ተጓዳኝ የቆዳ ኢንፌክሽን መኖሩን ስለሚያመላክት ሀኪምን ማማከር ያስፈልጋል።

Telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb

YouTube
👇 https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw

Tiktok
👇
https://vm.tiktok.com/ZM8cRdRTQ/
👍26😱1
በዚህ ሳምንት ከተጠየቁት ጥያቄወች ዉሰጥ
'መጥፎ ሺታ ያለዉ የማህፀን ፈሳሺ አለኝ '
የሚለዉ በብዛት ቀርቧል።
✍️ስለ አባላዘር በሺታ ከአሁን በፊት የቀረበ ቢሆንም በድጋሜ አቅርበናል።

✍️የአባላዘር በሺታ የሴትን ወይም የወንድን የመሪቢያ አካል የሚያጠቃ ተላላፊ በሺታ ኘዉ።
✍️መተላለፊያዉ በንክኪ ሲሆን ዋነኛ የመተላለፊያ መንገድ የግብረ ስጋ ግንኙነት ነዉ።

* ምልክቶች*
👉ከማህፀን የሚወጣ መጥፎ ሺታ ያለዉ ፈሳሺ።ፈሳሹ ነጭ ወይም ቢጫ ሊሆን ይችላል።

👉የሚፈረፈር አይነት ነጪ ፈሳሺ

👉የብልት ማሳከክ፣ሺንት ሲሸና ማቃጠል ፣በግንኙነት ጊዜ ህመም

👉ብልት ላይ የሚከሰት መሰነጣጠቅ ወይም ቁስለት

👉ከወንድ ብልት የሚወጣ ነጭ ፈሳሺ

👉ታችኛዉ የሆድ ክፍል ላይ ህመም

👉የወንድ ልጅ ፍሬን የሚሸፍነዉ ክፍል ላይ እብጠት(scrotal swelling)

👉የአባላዘር በሺታ ካለባት እናት የተወለደ ህፃን ላይ ደግሞ የህፃኑ አይን ላይ የሚታይ ከፍተኛ የሆነ እብጠት :መቅላት እና አይን አር(Neonatal conjunctivites)

**በምን ምክንያት ይመጣል**

👉ባክቴሪያ፣ቫይረሶች፣ፓራሳይት ዋናዎቹ ናቸዉ።

**ህክምናዉ**

✍️በደምስር (በመርፌ የሚሰጥ) መድሀኒት cefttiaxone
👉የሚዋጥ መድሀኒት
👉ታይቶ እንደአስፈላጊነቱ በሴት ልጅ ብልት ዉስጥ የሚገባ ክኒን.....
✍️✍️✍️✍️መረሳት የሌለበት ነገር አንድ ሰዉ የአባላዘር በሺታ በሚታከምበት ጊዜ የትዳር ጎደኛዉን አብሮ ማሳከም ይኖርታል።የትዳር ጎደኛዉ ምልክት ቢያሳይም ባያሳይም።ይህ የሚሆንበት ምክንያት አብዛኛዉ ተጠቂወች በሺታዉ ቢኖርባቸዉም ምልክት ላያሳዩ ስለሚችሉ ነዉ።የትዳር ግደኛ ካልታከመ በሺታዉ በተደጋጋሚ በመከሰት ይመላለሳል ማለት ነዉ።

ካልታከም ምን ያስከትላል**

👉PID(pelvic inflamatory desease )
👉የእንቁላል መተላለፊያ ቱቦዉ ላይ ጠባሳ በመፍጠር የእንቁላል መጎጎዝን በማስተጎጎል መዉለድ አለመቻል (መሀንነት)

👉ከማህፀን ዉጭ ርግዝና

👉ለማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጋላጭነትን መጨመር

👉የመራቢያ አካል ኪንታሮት (Genital wart)

👉ወንዶች ላይ የሺንት ቧንቧ ጥበት(urethral stricture)...

👉👉👉👉ምልክቶቹ እንደታዩ ቶሎ ህክምና ማግኘት ይመከራል👈👈👈👈👈👈


ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ
👍493👌1
የእርዳታ ጥሪ

ስሜ ተማም ጀማል  ይባላል

ተወለጄ ያደኩት  በባሌ ጎባ  ስለሴ ቤ/ክሪስቲያን  አከባቢ ነው ከአዲስ  አበባ ዩኒቨርስቲ  በሚድዋይፈሪ ሞያ ተመርቄ 
ላለፉት 8 አመታት በባሌ ሮቤ ሆስፒታል  ህብረተሰቡን  ሳገለግል ቆይቻለሁ ከሁለት አመት በፊት  ባደረብኝ  ከፍተኛ የኩላሊት  ህመም  ምክንያት ሁለቱም ኩላሊቶቼ ተጎድተው
ላለፉት ሁለት አመታት  የኩላሊት  እጥበት  እየተደረገልኝ እገኛለሁ

ዉድ ወገኖቼ ከዚህ  ህመም  ለመዳን  የኩላሊት  ንቅለ ተከላ  ማድረግ ያስፈልገኛል

የኩላሊት  ንቅለ ተከላ በሀገራችን  እየተሰጠ ስለ ማይገኝ
ዉጭ ሀገር ሄዶ ማሰራት ግድ ሆኖብኛል

እኔም  ሆንኩ ቤተሰቦቼ  ወደ ዉጭ ሀገር ሄጄ ምታከምበት ገንዘብ ስለሌለን  ሁላቹም  አቅማቹ የቻለዉን ያክል ከታች በተጠቀሰው  የባንክ  አካውንት  እንድትረዱኝ  ስል በፈጣሪ  ስም  እጠይቃለሁ ።

ስለበጎነታችሁ በፈጣሪ ስም ከልብ አመሰግናለሁ

ተማም ጀማል  አህመድ  📞 091 179 1452

የኢትዮጵያ  ንግድ  ባንክ
1000040276053

አዋሽ ባንክ
01425154552700265

አቢሲኒያ ባንክ 54375816

ስለበጎነታችሁ በፈጣሪ ስም ከልብ አመሰግናለሁ
👍31
     የሴት ልጅ ዳሌ 

🖲የሴት ልጅ ዳሌ ለውበት ብቻ የተፈጠረ እንዳይመስላችሁ በስነተዋልዶ ህክምናም ራሱን የቻለ ጠቀሜታ አለው። አመቺ ዳሌ ያላት ሴት በወሊድ ግዜ አትቸገርም

🖲የሴት ዳሌ ብዙ አይነት አፈጣጠር ያለው ቢሆንም ነገርግን
መደበኛ የሴት ልጅ የዳሌ አጥንት አይነት ፣ (Gynacoid) ጋይናኮይድ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ በምጥ ለመውለድ ምቹ የሆነ እና 50 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የሚይዙት የዳሌ አጥንት አይነት ነው።

🖲ይህም ሲባል ሰፊ ዳሌ ያላት ሴት በምጥ ግዜ የሚደርስ መስተጓጎል አይፈጠርባትም ማለት አይደለም

🖲በምጥ ግዜ የሚከሰት መስተጓጐል ከዳሌ አፈጣጠር ውጪ የሚመጣበት መንስኤ ብዙ ነው

👉የፅንስ ክብደት ከ 4.5 ኪሎ በላይ መሆን
👉በምጥ ግዜ ያለው የፅንስ አቀማመጥ
👉ተጓዳኝ የውስጥ ደዌ ህመሞች እና
👉የ ስነፅንስ ተኮር ችግሮች መኖር

🖲አንድ ሴት በምጥ ከመውለድ ውጪ በቀዶ ጥገና (Cesarean Section (CS)) እንድትወልድ የምትገደድባቸው ምክኒያቶች ናቸው።

🖲ከዛ ውጪ የዳሌ አጥንት በምጥ ለመውለድ አመቺ መሆኑን ለማወቅ የህክምና ምዘና ይደረጋል

👉Pelvimetry
👉Obstetric ultrasound
👉Biophysical Profile
👉 የደም የሽንት እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ ተጨማሪ ምርመራዎች

🖲 እነዚህን ምዘናዎች እና ተጓዳኝ የምርመራ ውጤቶችን በማገናዘብ በምጥ የመውለድ እድልን አስቀድሞ መተንበይ ያስችላል።

🖲ለዚህ ሁሉ ስኬት በግዜ የሚጀመር የቅድመ ወሊድ ክትትል ወሳኝነት አለው።

ለህክምና ቀጠሮ ብቻ
ይሄን ተጭናችሁ 👉 @LEKETERO
ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ 0974163424

Telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍39
የማይግሬን ራስ ምታት (Migraine Headache)

🖲ማይግሬን ከፍተኛ እና በተደጋጋሚ ግማሽ ከፈሎ የሚከሰት ራስ ምታት ነው። ህመሙ ከአራት ሰአት እስከ ሁለት እና ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከጭንቅላት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ይባባሳል፡፡

👉👉ለማይግሬን አጋላጭ ሁኔታዎች👉👉

✍️ በፆታ ሴት መሆን
✍️በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ

🎇🎇የማይግሬን ምልክቶች🎇🎇

👉ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
👉ከፍተኛ የድካም ስሜት
👉ብርሐን፣ ድምፅ እና ሽታ መጥላት
👉 የምግብ ፍላጎት ማጣት
👉ዉሃ መጠማት/የከንፈር መድረቅ
👉የስሜት መዋዠቅ
👉ድርቀት ወይም ተቅማጥ
👉 ቅዠት(የሌለ ብርሐን፣ ጥቋቁር ነጠብጣብ መታየት)
👉ጣዕም እና ሽታ ለመለየት መቸገር
👉የእይታ መደብዘዝ
👉በግማሽ በኩል የሰዉነት መዛል/አለመታዘዝ
👉እግር እና እጅ ላይ የመክበድ ስሜት/መደንዘዝ
👉ጆሮ ላይ የደዉል ድምጽ መሰማት

😺😺ማይግሬንን የሚያባብሱ ሁኔታዎች😺😺

👉በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመም እና የሆርሞን መለዋወጥ
👉ጭንቀት
👉ምግብ አለመብላት/ርሀብ
👉የአየር ንብረት መቀያየር
👉ምግቦች (እንደየሰዉ ይለያያል) አልኮል
👉የእንቅልፍ መዛባት

✍️✍️✍️የማይግሬን ህክምና✍️✍️✍️

👉የህመም ማስታገሻ እና እንደደረጃው የህመም መከላከያ መድሓኒቶች በሀኪም ክትትል የሚወሰድ
👉ጨለማ እና ፀጥ ያለ ክፍል ዉስጥ በቂ እረፍት ማድረግ
👉በቂ ዉሃ መጠጣት
👉የዝንጅብል ሻይ ፣አፕል እንዲሁም
👉ፎጣ በቀዝቃዛ ዉሃ ነክሮ ወይም በረዶ ጭንቅላት ላይ ማድረግ
👉ጭንቅላት እና የእጅ መዳፍን ማሸት
👉 ቋሚ የሆነ ሰዉነትን የማሳሳብ እንቅስቃሴ እና አርማሞ መስራት :ቋሚ የሆነ መመገቢያ እና የሚተኛበት ግዜ መኖር
👉 የሚያባብስብንን ነገር ለይቶ ማስወገድ ችግሩ እንዳይከሰት ይረዳል።

✍️✍️ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ
👍61😢73🥰1
የእርግዝና ምርመራ

🖲 ገብስ እና ስንዴ ላይ በመሽናት ነበር በድሮ ግዜ እርግዝና የሚታወቀው በሽንት ውስጥ የተነከረው የስንዴ ወይም የገብስ ፍሬ እድገት ካሳየ እርግዝናን ያመላክታል

🖲ከዚህ ውጪም የወር አበባዋን ያሳለፈች ሴት ከ እንቅልፍ በፊት በውሀ የተበጠበጠ ማር ከጠጣች በኋላ የሆድ መነፋት እና የሆድ ቁርጠት ካጋጠማት እርግዝና ተፈጥረዋል ተብሎ ይተነበይም ነበር

🖲በ ፈረንጆች በ 1928 አካባቢ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው HCG በመባል የሚታወቀው የእርግዝና ሆርሞን አሁን ላይ ላለው የእርግዝና ምርመራ መሰረት ነው

🖲ይህ የእርግዝና ሆርሞን ከፅንስ ህዋሶች የሚመነጭ ሲሆን፣ ጥቅሙም ፣መሀፀን ለእርግዝና እንዲዘጋጅ የእንቁላል እጢን ለማነቃቃት ነው

🚩ይህ ሆርሞን ከእርግዝናም ውጪ የሚፈጠርበት የበሽታ አጋጣሚም አለ🚩

🖲እስካሁን ባለው ጥናት በእርግዝና ወቅት ይህ ሆርሞን ከለት ወደለት የሚያሳየው የመጠን መጨመር ፣ብቁ የእርግዝና መመርመሪያ እንዲሆን አድርጎታል

🖲ጥሩው ነገር ደሞ በሽንት የሚደረግ የእርግዝና ምርመራን በቤት ውስጥ ማረግ የሚቻል ሲሆን የወር አበባ ከቀረ በ አንድ ሳምንት ውስጥ እርግዝና መፈጠሩን ማሳወቅ ያስችላል

🖲በደም ምርመራ ሲሆን ደሞ፣ የወር አበባ ይመጣል ተብሎ ከታሰበበት ቀንም አስቀድሞ እርግዝና መኖሩን ለማወቅ ያስችላል

🖲የሽንት እርግዝና ምርመራ ውጤት ሊሳሳት የሚችለው

👉የወር አበባ መዛባት ከነበረ
👉እርግዝና መኖሩ ሳይታወቅ ተፈጥሮአዊ ውርጃ ካጋጠመ
👉የእርግዝና መመርመሪያው ግዜው ያለፈ እና አነስተኛ አቅም ካለው
👉እንዲሁም አንዳንድ የእንቁላል እጢ እና በመህፀን ውስጥ በሚፈጠሩ እጢዎች ምክኒያት ምርመራው ያልተጠበቀ ውጤት ሊሰጥ ይችላል

🖲በዚህም ምክኒያት፣ ማንኛውም በቤት ውስጥ የሚሰራ የእርግዝና ምርመራ ውጤት፣ በጤና ተቋም መረጋገጥ ያስፈልገዋል።
👍411🥰1
አዲሱ ጉንፋን

🖲ሰሞኑን የመጣ አዲስ የጉንፋን ስርጭት አለ
የኮሮና ቫይረስ አለመሆኑን በምን ማወቅ እንችላለን ?

🖲ጉንፋን ማለት፣ በቫይረስ የሚከሰት የላይኛው የመተንፈሻ አካል ቁጣ ማለት ነው ባጭሩ

🖲ጉንፋንን የሚያመጡት ቫይረሶች ደሞ ብዙ አይነት ዝርያ አላቸው። የ ኮሮና ቫይረስ  ዝርያም በነዚህ ውስጥ ይመደባል

🖲ማንኛውም የጉንፋን ቫይረስ እድሉን ካገኘ ወደ ሳምባ ምች የመቀየር አቅም አለው

🖲በዚህ ግዜ ከሳል እና ትኩሳት ብርድብርድ ማለት አልፎ  ቶሎቶሎ መተንፈስና አየር ማጠር የመሳሰሉ ምልክቶችን ያሳያል።

🖲ተጓዳኝ ስርሰደድ በሽታዎች መኖር እንዲሁም
በእድሜና በተለያዩ ምክኒያቶች የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ ካለ ጉንፋን ወደ ሳምባምች የሚቀየርበትን እድል ያሰፋል።

🖲ታዲያ ይሄንን አዲስ የጉንፋን ስርጭት የኮሮና ቫይረስ እንዳልሆነ ለማወቅ ፣ከምርመራ ውጪ ሌላ ምንም መንገድ የለም።

🖲ተመርምረን ከ Corona Virus ነፃ መሆናችንን ካላረጋገጥን በስተቀር

👉 ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን መሸፈን
👉የእጅ እና አካል ንክኪ መቀነስ
👉ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አለመገኘት
👉 መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን መውሰድ እና
👉ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ መሸፈን ፈፅሞ አይርሱ

🖲የቤት ዉስጥ ማድረግ የሚቻለው

👉 ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም ፣
👉ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
👉Vitamin C Vitamin D እና Zink የሚይዙ ምግቦችን መመገብ ይበረታታል። ወይም በ ኪኒን መልክ መውሰድም ይቻላል

🚩🚩አስተውሉ🚩🚩

👉አየር ማጠር
👉እስትነፋስ መቆራረጥ
👉በተለይ አዛውንቶች እና የስኳር ፣ የአስም፣ የደምግፊት፣ የስትሮክ እና የካንሰር ህክምና የሚከታተሉ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መድረስ አለባቸው።

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/
YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
👍311
#ሰው #ሰራሽ #እርግዝና

🖲ሰው ሰራሽ እርግዝና መሰለኝ የሚባለው፣ ምናልባት ከተሳሳትኩ አርሙኝ፣ በህክምናው IVF ይባላል

🖲Assisted Reproductive technology ከሚባሉት ውስጥ ይመደባል

🖲እንቁላልና ሀብለዘርን ወስዶ በላብራቶሪ ውስጥ ፅንስን መፍጠርና እርግዝና እንዲይዝ መልሶ በመሀፀን ውስጥ ማስቀመጥ ማለት ነው በቀላሉ ሲተረጎም

🖲ይህ ህክምና በሀገራችን ውስጥ መሰራት ከተጀመረ 4 አልፎታል። ከዚህም በበለጠ መልኩ ICSI የተባለ መንገድም በሀገራችን ውስጥ እየተጀመረ ነው።

🖲ውጤታማነቱ በእድሜ እና በእርግዝና ታሪክ ይወሰናል፣ ማለትም ከዚህ በፊት አርግዘው የሚያውቁ ሴቶች እና እድሜያቸው ከ 35 አመት በታች ከሆነ፣ በዚህ መንገድ የማርገዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው

🖲ይህ ህክምና ለሁሉም እርግዝና ላልተሳካላቸው ሴቶች የሚሰጥ አይደለም። ያለመፀነስ ችግር በብዙ ምክኒያቶች ከሁለቱም ፆታዎች ሊመጣ ይችላል።

🖲የመሀንነት ህክምና መጀመር ያለበት ሁኔታ

👉እድሜያቸው ከ 35 በታች ለሆኑ ሴቶች፣ ያለምንም የእርግዝና መከላከያ በሳምንት 2 ግዜ ግንኙነት እየተደረገ ለ 1 አመት ያህል እርግዝና ካልተፈጠረ

👉እድሜያቸው ከ 35 አመት በላይ ከሆነ ደሞ በዚሁ ሁኔታ ለ6 ወር ቆይተው እርግዝና ካልተፈጠረ፣  ሁለቱም ፆታዎች የመካንነት ምርመራ ማረግ ይጠበቅባቸዋል።

🖲መካንነት እንደ አመጣጡ የሚታከም የመራቢያ አካል ችግር ነው።


Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/
YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
👍213👏1
ደም ማነስ (Anemia) ምንድን ነው?

✍️በደም ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ሴሎች ማነስ ወይም በቀይ የደም ሴል ውስጥ የሚገኘው የ ሄሞግሎቢን ማነስ ነው።

✍️ሄሞግሎቢን የምንለው በደም ሴል ውስጥ የሚገኝ ብረትን የያዘ እና ኦክሰጅን ከአንዱ ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል ተሸክሞ የሚያጓጉዝ ነው።

✍️ደም ማነስ ና ደም ግፊት የተለያዩ ናቸዉ።ደም ግፊት የደም መተላለፊያ ቱቦ መጥበብ ጋር የተገናኘ ነዉ።አንድ ሰዉ ደም ማነስ ኖሮት የደም ግፊትም ሊኖረዉ ይችላል።

👉👉ማንን ያጠቃል?👈👈

✍️- በምግብ ዉስጥ የ ብረት እጥረት ያለባቸዉ ሰወች

✍️ሴቶች __በወር አበባ ደም ስለሚፈሳቸዉ

✍️ነፍሰ ጡሮች _የብረት ፍላግታቸዉ በርግዝና ጊዜ ስለሚጨምር

✍️ከባድ በሽታ ያላቸው እና እድሜያቸው የገፋ ሰዎችም ተጋላጭ ናቸው።

👉👉መንስኤዎቹስ?👈👈

1.የቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ
በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ በብረት እጥረት ምክንያት ፣ ቫይታሚን ቢ12 እና ፎሌት እጥረት ፣ የኩላሊት ችግር ፣ ካንሰር

2.የቀይ የደም ሴሎች ውድመት

3በደም መፍሰስ ና በመንጠቆ ትል መጠቃት

👉👉እንዴት ማወቅ ይቻላል?👈👈

- የደም ምርመራ በማድረግ

👉👉ምልክቶቹስ?👈👈
-እንደ የደም ማነስ አይነቶች የሚለያይ ሲሆን
*የድካም ስሜት
*በእቅስቃሴ ጊዜ ያልተለመደ ፈጣን የልብ ምት
*እራስ ምታት
*የማዞር ስሜት
*ትኩረት ማጣት
*የቆዳ መገረጣት
*ትንፋሽ ማጠር
*ጆሮ ላይ የመጮህ ስሜት
*የምግብ ፍላጎት መቀነስ

✍️ህክምናው

- የደም ማነሱን ያመጣውን ችግር ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ማወቅ እና ማከም

👉 በብረት የበለፀጉ ምግቦች( ቀይ ስጋ ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ለምሳሌ ካሮት ፣ አቮካዶ ፣ ጉበት ፣ አሳ ፣ የጥራጥሬ እህሎች ፣ ባቄላ) ምግባችን ዉስጥ ማካተት
👉 ደም መለገስ

ዶ/ር ዮርዳኖስ
👍57👏61
የሰገራ ነቅሎ ተከላ እና ከሰገራ የተሰራው መዳኒት

🖲Stool transplant ወይም Fecal microbiota transplant (FMT) ይባላል በህክምናው

🖲ከአንድ ጤናማ ሰው የተወሰደን ሰገራ ፣በንፁህ ውሀ ወይም ጨው በሚይዝ ውሀ (Normal Saline) እንዲሟሟ ይደረግ እና፣ ወደ ተረካቢው ህመምተኛ ፣ በማስተላለፊያ ቱቦ ወደ ትልቁ የአንጀት ክፍል ማስተላለፍን ያመላክታል

🖲 አሁን ላይ ደሞ በተሻሻለ መልኩ ከሰው ሰገራ የተሰራ መዳኒት ተሰርቶ አመርቂ የሙከራ ውጤትን አሳይቷል

🖲እነዚህ ህክምናዎች በዋነኝነት የሚሰጡት ብዙ ተጠቂዎች ላሉት Pseudomembranous Colitis ለሚባል የትልቁ አንጀት በሽታ ነው

🖲ይህ በሽታ Clostridium Difficile በሚባል ባክቴሪያ የሚከሰት ሲሆን፣ ባክቴሪያው በተፈጥሮ አፈር ላይ እና አንዳንድ ሰዎች ላይ በትልቁ አንጀት ውስጥ ከሚኖሩ ባክቴሪያዎች ጋር፣ መጠኑ በተገደበ መልኩ ይኖራል

🔴የዚህ በሽታ ዋነኛ መንስኤ ያለ ሀኪም ትእዛዝ የፀረ ተህዋስያን መዳኒቶችን አዘውትሮ በመውሰድ ነው🔴

🖲በዚህ በሽታ የተጠቃ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች

👉የሆድ ቁርጠት
👉ጠረኑ የተለወጠ በቀን እስከ 3 ግዜ የሚመጣ ተቅማጥ
👉የምግብ ፍላጎት እና ክብደት መቀነስ
👉ደረጃው ከፍ ሲል ደሞ ትኩሳት እና የሰውነት ላይ እብጠት መታየት ሊኖር ይችላል

🖲ይህ በሽታ በተደጋጋሚ ግዜ የመመላለስ ባህሪ ያለው ሲሆን፣ ህክምናው የሚያጠቃልለው

👉ያለሀኪም ትእዛዝ የ ፀረ ተህዋስያን መዳኒቶችን ከመውሰድ በመቆጠብ በሽታው እንዳይመጣ መከላከል

👉በሽታው መኖሩ በሀኪም ከተረጋገጠ በኋላም በሀኪሙ ትእዛዝ የሚሰጡ መዳኒቶችን ብቻ በአግባቡ መጠቀም እና

👉በተደጋጋሚ ግዜ ሲከሰት ደሞ የሰገራ ነቅሎ ተከላ ሌላው የህክምና አማራጭ ነው

Telegram 👉https://t.me/seifemed
👍311