Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.7K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
🔴🔴ማሳሰቢያ🔴🔴

🔴በአገራችን ውስጥ ገበያ ላይ የሚገኙ ህገወጥ የምግብ ግብአቶችን ፈፅሞ እንዳትጠቀሙ የ ኢትዮጵያ የመዳኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ያሳስባል።

🔴ግብአቶቹን በመምስል ለማየት ሊንኩን ይጫኑ 👉
https://www.facebook.com/854974084615919/posts/4664998560280100/?sfnsn=mo
👍11
የጓጎለ የወር አበባ

🖲 የወር አበባ ስጋ መሰል እና የረጋ ደም ከያዘ፣ ጤናማ አይደለም።

🖲 ጤናማ የወር አበባ ፍሳሽ፣ በውስጡ፣ የመሀፀን ግድግዳ ቅራፊ ህዋሶችን እንዲሁም ከመሀፀን በር እና ከመራቢያ አካል ፣የሚወጡ ፍሳሾችንም አብሮ ይይዛል።

🖲በቀን ከ 10 እስለ 80 ሚሊ ሊትር የሚሆን መጠን ያለው ከ 3 እስከ 7 ቀን የሚፈስ እና ከ 21 እስከ 35 ቀን ድግግሞሽ የሚመጣ ኡደት አለው

🖲የወር አበባ ፍሳሽ ከደም ስር እንደወጣ ደም አይጓጉልም፣ ምክኒያቱም በውስጡ የሚይዘው plasmin የተባለ ንጥረ ነገር እንዳይጓጉል ይረዳዋል።

🖲ነገር ግን በተለያዩ ምክኒያቶች፣ በተፈጥሮም ሆነ በበሽታ፣ የወር አበባ መውረጃ መስመር ላይ መስተጓጎል ካለ እና የወር አበባ መጠን እንዲበዛ የሚያደርጉ የመሀፀን በሽታዎች እና ቁስለቶች ሲኖሩ የወር አበባ የጓጎለ ደም ሊይዝ ይችላል።

🖲ከዛ ውጪ ደሞ አብዛኛውን ግዜ፣ ሳይታወቅ እርግእና ኖሮ በራሱ የመጣ ውረጃ ሲያጋጥም የተቆራረጠ ፣ ስጋ መሰል ይዘት ያለው የወር አበባ ይታያል።

🖲እንዲህ አይነት ችግር እና ተያይዞ በግንኙነት እና በወር አበባ ግዜ ህመም ካለ፣ የወር አበባ መዛባት እና ከእምብርት በታች ህመም መኖር። ሀኪምጋ መቅረብ ያለባቸው የህመም ምልክቶች ናቸው።

Telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb

Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/

YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
👍674😢3👏2
ይቅርታ፣ ይህ 👉 @LEKETERO የክሊኒክ አድራሻ ነው ለቀጠሮ ብቻ ምልክቱን ተጭነው ስም እና ስልክ ያስቀምጡ

ለጥያቄ ይሄን ይጠቀሙ👉https://t.me/seifemedask
በስልክ ለማግኘት ከሆነ ለ ዶ/ር ሰይፈ +251974163424 ይደውሉ፣ ማታ ከ 12 ሰአት በኋላ እና ስራ ላይ ከሆነ ስልክ ስለማያነሳ በሌላ ግዜ ደግመው ይደውሉለት።

telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍81
👍5
👍5
ህገወጥ ውርጃ

🖲 የጤና ባለሞያዎች ለሁለቱም ፃታዎች የእርግዝና መከላከያ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የሚመክሩት ያለምክኒያት አይደለም

🖲ጥንቃቄ በጎደለው ግንኙነት ምክኒያት ያልታቀደ እርግዝና ሲያጋጥም የአብዛኞች ውሳኔ እንደምታቁት ህገወጥ ወርጃ ነው።

🖲በሀገራችን ውስጥ ውርጃ የሚፈቀድባቸው 5 መንገዶች ብቻ ናቸው።

👉1. በመደፈር እና በዘመድ መካከል ግንኙነት የተፈጠረ አርግዝና ከሆነ

👉2. የእርግዝናው መቀጠል የእናትየዋን ህይወት የሚያጨናግፍ ከሆነ

👉3. ፅንሱ ሊድን የማይችል የአካል ጉድለት ካለው

👉4. እናትየዋ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ወይም የአእምሮ በሽታ እና የአካል ጉድለት ተጠቂ ከሆነች እንዲሁም

👉5. ግዜ በማይሰጥ ድንገተኛ አደጋ እና በበሽታ ምክኒያት አፋጣኝ ህክምና የሚደረግ ከሆነ። ውርጃ በህግ ይፈቀዳል

🖲 ከዚህ ውጪ የሚደረጉ ውርጃዎች ፣በፍርድቤት ውሳኔ ፣በባለሞያው እና ፈቅዳ ውርጃን የምታከናውነው እርጉዝ ሴት ላይ በወንጀል ህግ ያስቀጣል

🖲አሳሳቢው ሁኔታ በህግ ተጠያቂ መሆን ብቻ ሳይሆን
አንዳንዴ ከውርጃ በኋላ የሚያጋጥም የጤና ችግር፣ ከግዜ በኋላ የሚፀፅት የእድሜ ልክ ጠባሳንም ትቶ ሊያልፍ ይችላል።

🖲 በሀገራችን ውስጥ ውርጃን በተለመከተ የተቀመጠውን የወንጀል ህግ ከዚህ በታች በ PDF አስቀምጫለሁ።

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/
YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
👍323😱1
👍81
የልብ ትርታ ስሜት

🖲Palpitation ይባላል በህክምናው፣ በተፈጥሮ ያለምንም ምክኒያት የልብ ትርታ ስሜት ሊፈጥር አይችልም

🖲የልብትርታ ስሜት መኖር 3 የልብ እንቅስቃሴዎችን ያመላክታል

👉የልብ ምት ጥንካሬ መጨመር
👉የልብ ምት ፍጥነት መጨመር
👉የተዛባ የልብ ምት ድግግሞሽ መኖር

🖲የልብ ትርታ ያለገደብ ሲሰማ፣ አረፍት የሚነሳና አስጨናቂ ስሜት ይፈጥራል

🖲ድንገተኛ ዜና ሲሰማ ፣  ከፍተኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሲደረግ፣ ድንጋጤ እና ፍርሀት  ሲኖር ፣ የልብ ምት ድንገት ስለሚጨምር ለግዜው የልብ ትርታ ሊሰማ ይችላል

🖲ከዚህ ውጪ የልብ ትርታ ስሜት ተደጋግሞ የሚመጣ ከሆነ ምክኒያት አለው፣

🚩በተለይ ከልብ ችግር ጋር የተያያዘ ከሆነ ደሞ ለህይወት ስለሚያሰጋ አፋጣኝ ህክምና ያስፈልገዋል።

🖲ከልብ ችግር ውጪ የልብ ትርታ ስሜትን የሚፈጥሩ መዳኒቶች እና የተወሰኑ የጤና ችግሮች አሉ፣ ለምሳሌ፣

👉ቡናን ጨምሮ ካፌንን የሚይዙ መዳኒቶች
👉ከፍተኛ የደም ማነስ
👉የታይሮይድ በሽታ
👉የአየር እጥረት እና የደም ስኳር መጠን ማነስ እንዲሁም
👉ድባቴ እና ጭንቀት የመሳሰሉ የስነ አእምሮ በሽታዎች ለዚህ ችግር ተጠቃሾች ምክኒያቶች ናቸው

🖲 ይህ አይነት ችግር በተደጋጋሚ ግዜ ያጋጠማችሁ ከሆነ፣ ምክኒያቱ በምርመራ መጠናት ስላለበት ሀኪምን በማማከር አስፈላጊውን ህክምና እንድታገኙ እመክራለሁ።

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
👍396
👍4🙏1
ቫያግራ እና ኮቪድ

🖲Fox News ላይ ሰሞኑን ስንመለከት

"አንድ በከፍተኛ ሁኔታ በኮቪድ የተጠቃች ሴት፣ በመተንፈሻ መሳሪያ ስትታገዝ ቆይታ ለውጥ ባለማሳየቷ፣ ሀኪሞቿ ከፍተኛ መጠን ያለውን ቫያግራ ከሰጧት በኋላ ልትነቃ ችላለች"

የሚል ዜና ካያችሁ ፣-

🖲ምናልባት ብዙም የሚደንቅ ነገር ያለ አይመስለኝ፣ ምክኒያቱም ቫያግራ ከስንፈተ ወሲብ ችግር ውጪም

👉ለሳምባ ደምስር ግፊት ህክምና
👉ጣቶች ላይ ለሚከሰት የተጋነነ የደምስር ጥበት
Raynaud's phenomenon
👉ከከፍተኛ ቦታ ላይ ከመሆን ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የሳምባ እብጠት high altitude pulmonary edema ህክምናም ይውላል

🖲መዳኒቱ ጥቃቅን ደምስሮችን የማፍታታት ባህሪ አለው

በኮቪድ እና በተለያዩ ምክኒያቶች፣ የሳምባ ጥቃቅን ከረጢቶች ሲጎዱ ሳምባ አየርን ወደ ደምስር ለመስገባት ይቸገራል፣

🖲 በዚህ ምክኒያት፣ በቂ አየር ወደደም ሳይገባ ሲቀር ደሞ ፣ ጥቃቅን የሳምባ ደምስሮች ይኮማተሩና ለባሰ የአየር እጥረት ይዳርጋሉ

🖲ቪያግራን በመጠቀም እነዚህን ጥቃቅን የሳምባ ደምስሮችን በማፍታታት የሳምባ ድክመት ከመባባሱ በፊት ይህን ችግር ለመመለስ ነው ሀሳቡ

🖲ለበለጠ መረጃ በዚህ ጉዳይ ላይ ያገኘሁት ጥናታዊ ፅሁፍ ከዚህ በታች ተቀምጠዋል።
👇👇

https://ccforum.biomedcentral.com/articles/10.1186/s13054-021-03885-y

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍242
10👍3
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ ጥምቀት በዓል አደረሳችሁ
👍15🥰1
ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት

🖲ቀን አብራችሁ የዋላችሁት ሰው፣ በማግስቱ ሞተ ሲባል ስትሰሙ በጣም ከባድ ነው ስሜቱ።

🖲ከመመረዝ ፣ራስን ከማጥፋት እና ከድንገተኛ አደጋ ውጪ፣
በድንገት ህይወት የሚነጥቁ የታወቁ በሽታዎች አሉ

🖲ከነዚህ ውስጥ፣ የልብ ደምስር ጥበትና፣ የልብ የትርታ መዛባትን የመሳሰሉ የልብ ችግሮች፣ ዋነኛ ምክኒያቶች ናቸው

🖲ከዚህ በፊት ያልታወቀ፣ ያልታከመ እና በቂ የህክምና ክትትል የሌለው 🚩የደምግፊት ሲኖር ደሞ ፣በሚያስከትለው ድንገተኛ የአንጎል ደም ፍሰት እና የደምስር መዘጋት ምክንያት በድንገት ሊያሰናክል እና ህይወትን ሊቀጥፍ ይችላል

🖲ሌላው ፣ከዚህ በፊት ያልታየ የሚጥል በሽታ ምክኒያት እንዲሁም፣ እንደ እስም እና የሳምባ ደምስር በረጋ ደም መዘጋትን ተከትሎ የሚመጣ ድንገተኛ የአየር እጥረት መኖር 🚩 ከልብ ችግሮች ባሻገር ለድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የሚዳርጉ ምክኒያቶች ናቸው።

🖲 እናስተውል

👉 ከሱስ የፀዳ ህይወትን በመከተል፣
👉 ጤናማ አመጋገብን በመምረጥ እና ወትሮአዊ እንቅስቃሴዎችን በማረግ
👉 ደምግፊት፣ ስኳር እና አስምን ለመሳሰሉት በሽታዎች ጥብቅ የህክምና ክትትል በማድረግ፣🚩 ከበሽታ የሚመጣ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወትን መታደግ ይቻላል ።


📞 ዶ/ር ሰይፈ +251974163424
🚩መልእክት አትላኩ አላየውም
🚩 ማታ ከ 12 ሰአት በኋላ እና ስራ ላይ ከሆንኩ ስልክ እዘጋለሁ በሌላ ግዜ ደግመው ይደውሉ

🔴ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ምልክቱን ተጭነው ስም እና ስልክ ያስቀምጡ 👉 @LEKETERO

telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍545👏1
ደም ማስመለስ

🖲 ደም ማስመለስ ከ ሁለት ዋና ዋና መንገዶች ይጀምራል

👉 የአንጀት መስመር ቁስለት እና
👉 የሳንባ ቁስለት

🖲 የአንጀት መስመር ቁስለትን እናያለን፣ ወይም upper GI bleeding ይባላል በህክምናው

🖲 በድንገተኛ ህክምና ክፍል ዉስጥ ከሚያጋጥሙ ችግሮች ዉስጥ አንዱ ደም ማስታወክ ነዉ።

✍️✍️✍️ምልክቶች

👉ማቅለሺለሺ ና ማስታወክ
👉ክብደት መቀነስ
👉ጠቆር ያለ ደም
👉ንፁህ ደም ማስታወክ
👉የሰገራ መጥቆር
👉ነፁህና ቀይ ደም ከሰገራ ጋር መዉጣት

👌👌👌ምክንያቶቹ👌👌👌


ለረጂም ጊዜ የቆየ የጨጎራ ህመም
የጨጓራ ካንሰር
ጉሮሮ ላይ የሚገኘ የደም ስር መሰንጠቅ
ደም የመርጋት ችግር
የጉበት ህመም

👌👌👌የሚያጋልጡ ሁኔታወች👌👌👌

ቆየት ያለ ጨጓራ ህመም
ሲጋራ ማጨስና አልኮል መጠጥ


🖲ምርመራዎች

👍የደም ምርመራ
👍እንደአስፈላጊነቱ የሰገራ
👍የኩላሊት ና ጉበት
👍በጉሮሮ ገብቶ የሚሰራ(endoscopy )


👉👉👉ህክምናዉ👈👈👈


👉ማስታወክን የሚያስቆም መድሀኒት በደም ስር የሚሰጥ(omeprazole)
👉በዚህ በሺታ የተጠቃ ሰዉ ምንም አይነት ምግብም ይሁን ዉሃ እንዲወስድ አይመከርም ይህም የሆነበት ምክንያት ማስታወከን ስለሚያባብሱ ነዉ።

👉በኢንዶስኮፒዉ ዉጤት መሰረት መድማት ያመጣዉን ነገር ማከም።።።።


👉👉👉ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ
👍648
ኪንታሮት

🖲 ኪንታሮት ከሰው ወደሰው በቀላሉ ይተላለፋል። በደረት በእጅ እና በፊት ላይ የመውጣት ባህሪ አለው።

🖲በብብት እና በውስጠኛው የታፋክፍል ላይ ሲሆን ደሞ፣ በዝተው ሊወጡ ይችላሉ።

🖲መጠናቸው እና ብዛታቸው በጣም የበዛ ከሆነ ፣  የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅምን የሚቀንስ፣ ተጓዳኝ የውስጥ ደዌ ህመም እንዳለ ያመላክታል።

🖲አብዛኛውን ግዜ ከ2 እስከ 5 ሚሜ ስፋት አላቸው፣ አንዳንዴ ደሞ እስከ 1.5 ሴሜ ድረስ ያድጋሉ፣ እብጠቶቹ ፣ መሀል ለይ በሚታይ ስርጉድ ያለ ገፅታ መኖር፣ ከሌላ ቆዳላይ ከሚወጡ።እብጠቶች መለያቸው ነው።

🖲የቆዳ ንክኪ፣ አልባሳትን እንዲሁም ማናቸውንም ከቆዳ ጋር ንክኪ የሚፈጥሩ መሳሪያዎችን በጋራ በመጠቀም ፣በቀላሉ ከሰው ወደሰው ይተላለፋሉ።

🖲በአንድ ጤነኛ ሰው ላይ፣ ያለ ምንም ህክምና በአማካይ ከ6 እስከ 9 ወር ቆይታ በኋላ ሙሉ በሙሉ ይጠፋሉ

🖲ምንም እንኳን፣ ለነዚህ ኪንታሮቶች የተለያዪ የህክምና አማራጮች ቢኖሩም፣ ያለ ህክምና በራሳቸው ግዜ ቢጠፉ ተመራጭ ነው።

🖲ህክምና ካስፈለ ግን ሀኪምን ማማከር ያስፈልጋል።
👍649🥰2
👍29👏2
የቶንሲል ጠጠር

🖲ከጥርስ እና ከምላስ ችግሮች ባሻገር፣ መጥፎ የአፍጠረን የሚፈጠርበት አንዱ ምክንያት ነው

🖲በተደጋጋሚ የ ቶንሲል ኢንፌክሽኖች ምክኒያት፣ በቶንሲል ከረጢቶች ውስጥ በግዜ ሂደት የሚፈጠር፣ የባክቴሪያ ስብስብ እና ተረፈምርት፣ ጠጣር ጥርቅምን ይፈጥራል

🖲ጥርቀሙ በግዜ ሂደት ይጠጥርና መጥፎ ሽታን ይይዛል።

🖲አብዛኛውን ግዜ መጠፎ የአፍ ጠረን ከመፍጠር ውጪ ፣የህመም ስሜት አይኖረውም

🖲አንዳንዴ ፣መጠኑ ከፍ ያለ ከሆነ፣ ምግብ ወይም ፈሳሽ ሲወሰድ ጉሮሮ አካባቢ በመጠኑ የመቆርቆር ስሜትን ሊፈጥር ይችላል፣

🖲ሌላው ደሞ አንዳንዴ ከመተለቁ የተነሳ የቶንሲል እብጠት እና የጆሮ ህመም ሊፈጥር ይችላል

🖲ከዛ ውጪ የህመም ስሜት ስለማይፈጥር አብዛኛውን ግዜ በአጋጣሚ ለሌላ ህክምና በሚደረጉ ምርመራዎች ይገኛል።

🖲መጥፎ የአፍ ጠረን ካላስቸገረ እና ህመም ካልፈጠረ በቀር ህክምና አያስፈልገውም

🖲 በቤት ውስጥ የሚደረጉ ተግባሮች

👉ለብ ባለ ግማሽ ሊትር ውሀ ውስጥ 1 የሻይ ማንኪያ ጨው አሟምቶ፣ ጉሮሮን በተደጋጋሚ ማለቅለቅ፣ ወይም ጋርግል ማረግ

👉 ወይም ለመጉመጥመጫ ታስቦ የተዘጋጀ የአፍ ማጠቢያንም መጠቀም ይቻላል።

👉የሚታይ ከሆነ ደሞ ግፊት ባለው ውሀ ቶንሲል ላይ በመርጨት፣ በእጅ ወይም በማይቧጭር እና ስለት በሌለው መሳሪያ ማውጣት ይቻላል

🖲እነዚህ መንገዶች ውጤታማ ካልሆኑ፣ በህክምና የቶንሲሎችን ከረጢት ማፅዳት እና እንዲሁም ከዛ ካለፈ ደሞ፣ ቶንሲልን በቀዶ ህክምና የማስወገድ አማራጭ ህክምና አለው።

🖲ይህ ህክምና የሚሰጠው በ አንገት በላይ ሀኪሞች ወይም (ENT surgeon ) ነው።

አመሰግናለሁ

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/
YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
👍11917😢1
👍175
ከ ፖስት ፒል ውጪ

🖲ከፖስት ፒል የበለጠ ሌላ፣ የድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ መንገድ እንዳለ ታቃላችሁ።

🖲በአለም የጤና ድርጅት መሰረት፣ ከፖስት ፒል ውጪ ለድንገተኛ እርግዝና መከላከያ፣ ተብለው የተቀመጡ፣ 1 ከሆርሞን ነፃ እና 4 አይነት እንክብሎች አሉ

🖲ከነዚህ ውስጥ ዝናን እና ብዙ ተጠቃሚን ያገኘው ፖስት ፒል፣ በብቃቱ ከፍተኛ ሆኖ ሳይሆን፣ አጠቃቀሙ ቀላል እና የሀኪም ትእዛዝን የማይፈልግ ስለሆነ ነው።

🖲ለድንገተኛ እርግዝና መከላከያ የተቀመጡት መዳኒቶች፣ እና የመከላከል ብቃታቸው

5️⃣ Yuzpe (ባለ ሁለት ሆርሞን)
4️⃣ Levonogestrel (Post Pill, ባለ አንድ ሆርሞን)
3️⃣ UPA (Ulipristal acitate)
2️⃣ Mifepristone (በሀኪም የሚታዘዝ)
1️⃣ Copper IUD (በመሀፀን የሚቀመጥ)

🖲የመሀፀን ሉፕ፣ ከረጅም ግዜ የእርግዝና መከላከያ መንገዶች ውስጥ አንዱ እና፣ ለድንገተኛ እርግዝና መለከላከያነት በብቃቱ የመጀመሪያ ነው

🖲ከተቀመጡት የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ አማራጮች ውስጥ post pill በብቃቱ አራተኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን ከመሀፀን ሉፕ ጋር ሲወዳደር

👉Post pill ፣ በ 72 ሰአት ውስጥ መወሰድ ያለበትና፣ አንዴ እንቁላል እና የስፐርም ህዋስ ከተገናኘ በኋላ ደሞ፣ እርግዝናን አይከላከልም ፣በሚፈጠረው ፅንስ ላይም ጉዳት አያስከትልም።

👉በመሀፀን የሚቀመጥ የኮፐር ሉፕ ግን ፣ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት ከተፈፀመ እስከ 5 ቀን ድረስ መጠቀም የሚቻልና፣

👉እንዲሁም የስፐርም ህዋስን ከማሰናከል ዋነኛ ተግባሩ ባሻገር ፣ የእንቁላል እና የስፐርም ህዋስ አልፎ ፣ውህድ ቢፈጠር እንኳን፣ የተፈጠረው ውህድ ማህፀን ላይ እንዳይቀመጥ የማሰናከል አቅም አለው።

🖲 ሌላው በብቃቱ የ ሁለተኝነት ደረጃ የያዘው የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ደሞ mifepristone ነው። ይህ መዳኒት ከሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት እና እንዲሁም ለሌላ የህክምና አላማም ስለሚውል፣ እንዳስፈላጊነቱ በሀኪም ትእዛዝ ብቻ የሚሰጥ ነው።

🖲 በብቃቱ በ ሶስተኝነት ደረጃ ላይ የሚገኘው UPA ወይም በገበያ ስሙ ella one በመባል ይታወቃል። ይህ መዳኒት ድንገተኛ እርግዝናን ከመከላከል ባሻገር፣ በሀኪም ትእዛዝ ለ ማህፀን እጢ ህክምናም የሚውል መዳኒት ነው።

🔴በመጨረሻም ለማሳሰብ የምወደው፣ ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት ትርፉ ያልተፈለገ እርግዝና ብቻ ሳይሆን፣ ለሚድኑና ለማይድኑ የአባላዘር በሽታዎች ተጋላጭ መሆን ነው

🔴ምንም እንኳን በእነዚህ መንገዶች ያልታቀደ እርግዝናን መከላከል ቢቻልም፣ ጥንቃቄ በጎደለው ግንኙነት፣ ለአባላዘር በሽታ ተጋላጭ መሆንም እንዳለ እንዳትዘነጉ አሳስባለሁ።

💥አመሰግናለሁ

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/
YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
Instagram 👉 https://www.instagram.com/invites/contact/?i=yicuvnbbuipm&utm_content=g6o8ksk
👍21230👏6👎5😱2