Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.7K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
⛔️እስኪ ስንቶቻችሁ ናችሁ ይሄንን የምታውቁት?

🖲 በHIV የተያዙ ህፃናቶች 50 በመቶ የሚሆኑት የ 2 አመት ልደታቸውን ሳያከብሩ ህይወታቸው ያልፋል፣

🖲30 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት ደሞ እስከ 10 አመት በህይወት የመቆየት እድል አላቸው።

🖲በህፃናቶች ላይ የሚከሰት የHIV  ስርጭት 90 በመቶ የሚሆነው፣ መነሻው፣ ከእናት ወደልጅ በሚተላለፍበት ግዜ ነው

🖲በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ግዜና፣ ጡት በማጥባት ፣ HIV ከእናት ወደልጅ የመተላለፍ አቅም አለው

👉የቅድመ ወሊድ ክትትል ከሌለ
👉በምጥ ወይም በቤት ውስጥ መውለድ
👉ከምጥ በፊት የሚመጣ የሽርት ውሀ ፍሰት መኖር
👉የፀረቫይረስ መዳኒት አለመውሰድ
👉እንዲሁም፣ ጡት ማጥባት ፣ የጡት ወተት እና ሌላ ምግብ እያፈራረቁ መስጠት

🔴የተወለደው ልጅ በHIV የመያዝ እድሉ እንዲጨምር ያደርጋል።

🖲የቅድመ ወሊድ ክትትል በግዜ የጀመረች አንድ በHIV የተጠቃች እናት፣ የፀረቫይረስ መዳኒት በግዜ ስለምትጀምር ፣ የባለሞያ ክትትልና ምክር ስለማይለያት፣ ከ ቫይረሱ ነፃ የሆነ ልጅ የመውለድ እድሏ ከፍተኛ ነው።

🔴በግዜ የሚጀመር የቅድመወሊድ ክትትል፣ ትልቅ ባለውለታ ነው።

አመሰግናለሁ

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/
YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
Instagram 👉 https://www.instagram.com/invites/contact/?i=yicuvnbbuipm&utm_content=g6o8ksk
👍14033😁6
ቦርጭ እና ቢራን ምን ያገናኛቸዋል? የሚል ጥያቄ ተጠይቆ ነበር። ምላሽ ለመስጠት ያህል፣

🖲አልኮልን በማዘውተር የሚመጣ ውፍረት ፣በአንጀት ዙሪያ የሚጠራቀም ስብን ይጨምራል

🖲በዚህ ዙሪያ፣ በቢራ በምትታወቀው አገር፣ ጀርመን ውስጥ የተካሄደ አስራ ዘጠኝ ሺህ ሰዎች የተሳተፉበት ለ ስድስት አመት የቆየ አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ እንደሚያሳየው፣

🖲በቀን 3 እና ከዛ በላይ ቢራ የሚጠጡ ሰዎች 17 በመቶ ቦርጭ የመጨመር እድል አላቸው።

🖲በ ተለይ ደሞ፣ ከቢራ ጋር፣ ሲጋራ የሚያጨሱና ጣፋጭ እና ስብ የበዛበት ምግብ የሚያዘወትሩ ሰዎች ላይ የበለጠ  ውጤት አለው።

🖲 ይሄንን ጥናታዊ ፅሁፍ ከዚህ በታች አስቀምጫለሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👍17544👏11😱5🎉1
ቦርጭና ቢራ.pdf
206 KB
👍10331👏9😢8
ስለጡት ካንሰር እና የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በተመለከተ በTV9 ከኔጋ የነበረ ቃለ ምልልስ እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ፣ አመሰግናለሁ


https://youtu.be/4svtjSBONsM
👍17550🥰19👏17🤔2
የድብርት በሽታ

🖲 የድብርት በሽታ ካልታከመና ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ፣ ራስን ለማጥፋት ምክኒያት ይሆናል

🖲ይህ ችግር ያለበት ሰው። ሀዘን ከያዘው ሰው ጋር ሊመሳሰል ይችላል ግን በጣም የተለያዩ ናቸው።

🖲ሀዘን፣ ምክኒያት አለው፣ ሲያጋሩት ይቀላል፣ በግዜ ሂደት የሚከስም እና ጥንካሬን ወይ ትምህርት ሰቶ ጊዜን ጠብቆ የሚያልፍ ስሜት ነው።

🖲ድባቴ ያለበት ሰው ግን ለስሜቱ ምክኒያት መስጠት አይችልም

👉የቀኑን አብዛኛውን ግዜ በድብርት መኖር
👉በማናቸውም ድርጊቶች ላይ ደስታን ማጣት
👉የባዶነት እና ያላስፈላጊነት ስሜት መኖር
👉የምግብ ፍላጎትን እና አቅምን ማጣት፣ የእንቅልፍ መዛባት
👉በተደጋጋሚ ግዜ ራስን የማጥፋት ሀሳብን ማመላለስ የመሳሰሉ ስሜቶች ከ2 ሳምንት በላይ ሲቆዩ የድብርት በሽታን ያመላክታሉ።

🖲የድብርት በሽታ አመላካች ስሜቶች ሲኖሩ የስነአእምሮ ሀኪምን ማማከር ያስፈልጋል።

ዊ ኬር ላይ ከስነ አእምሮ ሀኪሞች የበለጠ መረጃና ህክምና ማግኘት ይቻላል።
👇👇

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
👍15422👏12
በርግዝና ወቅት የሚከሰት ማቅለሺለሺ ና ማስታወክ

🖲በርግዝና ወቅት ማቅለሺለሺ ና ማስታወክ የተለመደ ነዉ። አንዳንዴ ስሜቱ የተጋነነ ሊሆን ይችላል።
ذ
🖲Hyper emesis gravidarum ይባላል በህክምናዉ።

🖲ይህ በመጀመሪያወቹ የርግዝና ሳምንታት በብዛት በመከሰት ይታወቃል። ስሜቱም መንታ ርግዝና ሲኖርና የመጀመሪያ ርግዝና ላይ ጠንከር ብሎ ይስተዋላል።

🖲በርግዝና ወቅት ከሚፈጠረዉ HCG ተብሎ የሚጠራዉ ሆርሞን በምክንያትነት ይጠቀሳል

🖲ተደጋጋሚ ማስመለስ ስለሚኖር
👉የሰዉነት ፈሳሺ ማነስ (dehydration)
👉የክብደት መቀነስ
👉በሰዉነታችን የሚገኙ ንጥረ ነገሮች መዛባት (electrolyte embalance) እንዲሁም የኬቶን እና አሲድ መብዛት ያስከትላል።

🖲ማቅለሺለሺ ና ማስታወክ በሌላ ህመምም ሊመጣ ስለሚችል

🖲የደም፣የሺንት፣የሰገራ፣የአልትራሳዉንድ፣የጉበት
ኩላሊትና ስኳር ምርመራ ያስፈልጋል።

🚩ህክምናዉ

በትዉከት ብዙ ፈሳሺ ስለሚወጣ የወጣዉን ፈሳሺ በግሉኮስ መልክ መተካት

ትዉከቱን ና ማቅለሺለሹን በመድሀኒት ማስቆም።

በምርመራ የተገኙ ሌሎች ችግሮች ካሉ ማከም።

በተደጋጋሚ ትንሽ ትንሽ መመገብ

ደረቅ ና ቅባት ያልበዛባቸዉ ምግቦችን መመገብ

በቤት ውስጥ ደሞ የዝንጁብል ሻይ መጠቀም ስሜቱን ለማሰተካከል ይረዳል

ከዛ ባለፈ ታማሚዋ እንዳትጨነቅ ማገዝ አብሮ መሆን ማጫወት ተገቢ ነው
👍24675👏24🥰10
👍4710🥰2
ብርድ  የሚባል በሽታ አለ?

🖲 አንድ ጤናማ ሰው ለመለስተኛ የከባቢ አየር ቅዝቃዜ ሲጋለጥ ሰውነት የያዘውን ሙቀት ላለማጣት ተፈጥሮአዊ ምላሾች ይሰጣል፣ እነዚህም

👉የደም ስር መጥበብ
👉የፀጉር ስር ጡንቻ መኮማተርን ተከትሎ የሚታይ የፀጉር መቆም
👉የሰውነት ጥቃቅን ተህዋሶች በሚደርሳቸው የሆርሞን ትእዛዝ መሰረት ሙቀትን አና ህይልን ማመንጨት
👉እንዲሁም የጡንቻ መንቀጥቀጥ ፣የመሳሰሉ ሂደቶች ሙቀትን ለማመንጨት እና ሙቀት ከሰውነት እንዳይወጣ የሚደረጉ የሰውነት የተፈጥሮ ምላሾች ናቸው።

🖲 በረዷማ ቅዝቃዜ ውስጥ ያለ በቂ መከላከያ ረዘም ላለ ግዜ መቆየት፣ ሰውነት ከሚሰጠው የመከላከያ ምላሽ በላይ የሆነ ቅዝቃዜ፣ የደም ዝውውርን የመግታት ብሎም ለአካል ጉዳት እንዲሁም ለህልፈት የመዳረግ አቅም አለው።

🖲መጠነኛ የከባቢ አየር ቅዝቃዜ መኖር ለበሽታ አይዳርግም። ነገርግን የተለያዩ ከዚህ በፊት የነበሩ የውስጥ ደዌ ህመሞችን የማባባስ አቅም አለው።

👉 ከዚህ በፊት የነበሩ የመገጣጠሚያ ችግሮች፣ የጀርባና የትከሻ ህመሞች፣ በቅዝቃዜ ወቅት ይባባሳሉ፣

👉 የአስም እና የመተንፈሻ አካል ችግር ያለባቸው ሰዎች ሳል እና ለመተንፈስ መቸገር ያጋጥማቸዋል

👉 የደም ማነስ እና የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ (Hypothyroidism ) ያለባቸው ሰዎች ብርድን መቋቋም ያቅታቸዋል።

👉 በጣም አናሳ ቢሆንም፣ አንዳንድ የተጋነነ ወይም የተዛባ የበሽታ ተከላካይ ያላቸው ወይም (Cold agglutinin disease) ካለ በቅዝቃዜ ወቅት ደም የመሰለ ሽንት መሽናት እና ለደም ማነስ መጋለጥ ያጋጥማቸዋል።

👉ጉንፋን ከሞቃታማ ግዜ ይልቅ በቅዝቃዜ ወቅት በብዛት የመንሰራፋት ባህሪ ያሳያል እንጂ የቅዝቃዜ መኖር ብቻ ጉንፋንን አያመጣም።

👉 በቅዝቃዜ ወቅት የደምስር ጥበት መኖር ፣የደም ግፊትን በመጠኑ ስለሚጨምር የደም ግፊት እና የልብ ህመም ታካሚዎች ላይ ጫና ያሳድራል።

🖲 ከዚህ ውጪ መባንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት ላይ በማንኛውም የአየር ፀባይ ፣መስኮትን ከፍቶ በመቀመጥ የሚመጣ በሽታ የለም።

🖲 ከታፈነ ከባቢ አየር ይልቅ በቂ የሆነ የአየር ዝውውር መኖር በትንፋሽ ከሚተላለፉ በሽታዎች የመከላከል አቅም አለው።

አመሰግናለሁ

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/
YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
Instagram 👉 https://www.instagram.com/invites/contact/?i=yicuvnbbuipm&utm_content=g6o8ksk
👍26566👏19🤔5🥰2😱2
🖲 ቀዝቃዛና ጣፋጭ ነገር ስትበሉ ጥርሳችሁን የሚያማችሁ ከሆነ ፣እንዲህ አይነቱ ችግር Dentin Hypersensitivity ይባላል

👉 የድድ መሸሽ
👉የጥርስ ሽፋን መሳሳት እና መጎዳት
👉የጥርስ መሸረፍ እና መቦርቦር በመሳሰሉ ምክኒያቶች ይጀምራል።

🖲ህክምናው እንደምክኒያቱ በጥርስ ሀኪም ይወሰናል

🖲ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው በውስጣቸው argenine እንዲሁም የ potassium ጨው የሚይዙ የጥርስ ሳሙናዎች እና የጥርስ ማጠቢያ ፈሳሾች ናቸው።

🖲ከሌሎች የጥርስ ሳሙናዎች የሚለዩት ለዚህ ችግር ታስበው የተሰሩ ስለሆኑ እነዚህ ምርቶች ባብዛኛው መሸፈኛቸው ላይ senesetive የሚል ፅሁፍ ይፃፍባቸዋል።
👍27590🥰16
አባክዎ የጥያቄ ግሩፕ ላይ ስልክ ቁጥር አያስቀምጡ።

ቀርበው ለመታከም ቀጠሮ ለማስያዝ 👉@LEKETERO የሚለውን ተጭነው ስም እና ስልክ ያስቀምጡ።

እናመሰግናለን።
👍13936🥰11👏10
መስቲካ ለምትወዱ ሰዎች

🖲ማስቲካ ማኘክ ሳይሆን ማስቲካ ታኝኮ ከተተፋ በኋላ ከ 15 እስከ 20 ደቂቃ ያህል ብቻ የአይምሮ ንቃት የመጨመር ባህሪ ያሳያል።

🖲ማስቲካ በሚታኘክበት ሰአት ደሞ እንደማንኛውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለግዜው ትኩረትን ይቀንሳል።

🖲ማስቲካ ሲታኘክ የምራቅ መጠንን ስለሚጨምር ፣የጥርስ ንፅህና ይጠበቃል፣ የጥርስ መቦርቦርን ይከላከላል።

🖲የሆድ እቃ እና የማህፀን ቀዶ ጥገና ከተሰራ ከ ተወሰነ ሰአት በኋላ ማስቲካ ሲታኘክ ፣የአንጀት እንቅስቃሴ ወደነበረበት እንዲመለስ ያፋጥናል።

🖲 ለሚያቅር ህመም ፣ ለስቅታ ማስታገሻ እና እንዲሁም አንዳንድ መዳኒቶችን በማስቲካ ውስጥ በማካተት ጥቅም ላይ ይውላል።

🖲ማስቲካ በድንገት ከተዋጠ፣ በጨጓራ መፈጨት ስለማይችል፣ ከቀናቶች በኋላ ይዘቱን ሳይቀይር በሰገራ ላይ ይወጣል።

🖲አንዳንዴ በተለይ እድሜያቸው ከ 5 አመት እና በታች ያሉ ህፃናቶች የሆድ ድርቀት ካላቸው እና በተደጋጋሚ መስቲካ ከዋጡ፣ የአንጀት መዘጋት ሊፈጥርባቸው ስለሚችል፣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

👍 አመሰግናለሁ

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb

አባክዎ የጥያቄ ግሩፕ ላይ ስልክ ቁጥር አያስቀምጡ።

ቀርበው ለመታከም ቀጠሮ ለማስያዝ 👉@LEKETERO የሚለውን ተጭነው ስም እና ስልክ ያስቀምጡ።
👍428109🥰37👏36😱6😢2
የተረሳ እንክብል

🖲የሚዋጥ የወሊድ መቆጣጠሪያ ለምትወስዱ ሰዎች በመሀል መውሰድ ብትረሱ እንደ ወሊድ መቆጣጠሪያው አይነት ተጨማሪ ጥንቃቄ ያስፈልጋችሁዋል

🖲ባለ 1 ሆርሞን ወይም ለምታጠባ እናት የሚሆነውን እንክብል የምትጠቀሙ ከሆነ፣ አወሳሰድ ላይ በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

🖲በተመሳሳይ ሰአት ካልተወሰደ ማለትም፣ ከሚወሰድበት ሰአት ለ3 ሰአት እንኳን ከተዛነፈ እርግዝና የመፈጠር እድል ይኖራል

🖲በዚህን ግዜ፣ መዳኒቱን መውሰድ ሳታቋርጡ ለ 2 ተከታታይ ቀናት ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ ወይም ተጨማሪ የእርግዝና መከላከያ፣ እንደ ኮንዶም እና ፖስት ፒል መጠቀም አለባችሁ።

🖲ባለ ሁለት ሆርሞን መከላከያ የሚወሰድ ከሆነ ደሞ፣ አንድ  ቀን ብቻ ሳትወስዱ ከረሳችሁ በማግስቱ ሁለት እንክብል ወስዶ የተቀረውን መቀጠል።

👉አብዛኛውን ግዜ ተጨማሪ መከላከያ መውሰድ አያስፈልግም

👉ነገርግን የተዘለለው እንክብል የወር አበባ መቶ ከሄደ የመጀመሪያው ሳምንት አካባቢ ከሆነ ፣ በግንኙነት ግዜ ተጨማሪ መከላከያ ፣ ኮንዶም ወይም ፖስት ፒል መጠቀም ያስፈልጋል።

🖲ሁለት ቀን እና ከዛ በላይ ከረሳችሁ ደሞ፣ የረሳችሁትን እንክብል ትተውት እና ካስታወሳችሁበት ቀን ጀምሮ በቀን በቀን እየወሰዳችሁ። ለሚቀጥሉት 7 ቀናት ከግንኙነት መቆጠብ። ካልተቻለ ደሞ በግንኙነት ግዜ ተጨማሪ መከላከያ ያስፈልጋል።
👍28361🥰38👏17🙏1
👍364
ቫይታሚን ዲ

🖲የፀሀይ ብርሀን ቫይታሚን ዲ ኖሮት አያውቅም፣ የፀሀይ ብርሀን የሚይዘው እንደስሙ በአይን የሚታይ እና የማይታይ UVA, UVB, UVC, Infrared , etc እየተባሉ የሚጠሩ የብርሀን ሞገዶችን ነው።

🖲ቨይታሚን ዲ የሚሰራው በጉበታችን ውስጥ፣ ኮሌስትሮልን ወደ ቅድመ ቫይታሚን ዲ በመቀየር ነው።

🖲ነገር ግን ጉበታችን ውስጥ የተሰራው ቅድመ ቫይታሚን ዲ፣ ሙሉ ለሙሉ ቫይታሚን ዲ ሆኖ ስራላይ ለመዋል፣ ጤናማ የኩላሊት ስራ እና የፀሀይ ብርሀንን በዋነኝነት ይፈልጋል።

🖲ማለትም አንድ የምግብ እጥረት፣ ከፍተኛ የኩላሊት ወይም የጉበት ድክመት ያለበት ሰው፣ የፀሀይ ብርሀን ቢያገኝ እንኳን፣ ለቫይታሚን ዲ እጥረት ይጋለጣል ማለት ነው።

🖲የዚህ ቪታሚን ፣ዋነኛ ጥቅም ለአጥንት ጥንካሬ የሚጠቅሙትን ካልሲየም እና ፎስፈረስ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ፣ከአንጀት ወደሰውነት ማስገባት ነው።

🖲በደም ውስጥ ያለው መጠን ካነሰ፣ በህፃናት ላይ
👉 የአጥንት ልምሻ፣

🖲በትላልቆች ላይ ደሞ ፣

👉ስር ሰደድ የጡንቻ ህመም
👉የአጥንት ህመም እና መሳሳት እና
👉የፀጉር መሳሳትን ሊያስከትል ይችላል።

🖲የፀሀይ ብርሀን ማነስ እና የምግብ እጥረት ካለ፣
ከ6 ሳምንት በላይ ለረጅም ግዜ የሚቆይ ተቅማጥ መኖር፣
ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የኩላሊት እና የ ጉበት ድክመት መኖር፣ በሰውነት ላይ የ ቪታሚን ዲ እጥረት እንዲኖር የሚጋብዙ
ምክኒያቶች ናቸው።

🖲ህክምናው በጣም ቀላል ነው፣ ለተጓዳኝ ችግሮች ህክምና መስጠት እና፣ እንደየ እድሜ ክልሉ ፣ከ400 እስከ 50,000 iU የሚሆን መጠን ያለው ቪታሚን ዲ ከ 6 እስከ 8 ሳምንት በሀኪም ትእዛዝ ይሰጣል።

🖲ይህ ቫይታሚን ዲ ያለ ሀኪም ትእዛዝ ከልክ በላይ ከተወሰደ ግን

👉ከፍተኛ ራስ ምታት እና ድካም
👉ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
👉ውሀ ጥም እና ቶሎ ቶሎ መሽናት የመሳሰሉ ምልክቶች ይታያሉ።

መልካም ግዜ

Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍31662👏31🥰8😱2👌1
ኮፍያ ፀጉርን ይመልጣል እንዴ?

🖲ኮፍያ ማድረግ ፣ፀጉርን፣ የራስ ቅልን እና የፊት ቆዳን ካላስፈላጊ የፀሀይ ጨረር በመከላከል፣ የፀሀይ ጨረርን ተንተርሰው ከሚመጡ የቆዳ ላይ ችግሮች አንዱ መከላከያ  መንገድ።

🖲ኮፍያ በቀጥታ ፀጉርን እንደሚመልጥ የሚያመላክቱ በቂ ጥናቶች የሉም።

🛑🛑 ነገርግን ንፅህናው የማይጠበቅ፣ የራስ ቅልን አጥብቆ የሚይዝ እና አየር የማያስገባ ኮፍያ ለረጅም ግዜ ማዘውተር የፀጉር እና የራስቅል ቆዳ ላይ የጤና ተፅእኖ ያሳድራሉ። 🔴

🖲ሆኖም ግን፣ ራሰ በረሀነት እና የፀጉር መሳሳት፣ ኮፍያ ማድረግን ብቻ ተንተርሰው የሚመጡ ችግሮች ሳይሆኑ፣ በተጓዳኝ ችግሮች ማለትም።

👉በዘር ራሰ በርሀነት ካለ፣
👉የምግብ እጥረት መኖር
👉የደም ማነስ ፣
👉ራስ ቅል ላይ በበሽታ አምጪ ተህዋስና በተፈጥሮ የሚመጣ ቁጣ ካለ፣
👉እንዲሁም አንዳንድ የውስጥ ደዌ በሽታዎች እና፣
👉የራስ ቅል ላይ የሚደርስ የጨረር የኬሚካል እና የሳት አደጋ መኖር ፣ እና የመሳሰሉ ምክኒያቶች፣ ለፀጉር መሳሳት ፣ መበጣጠስ እና መመለጥ የሚዳርጉ የተወሰኑ ምክኒያቶች ናቸው።

🖲ታዲያ ወደ ፀሀይ ሲወጣ ብቻ ከፍያን እንዲሁም ጃንጥላን በመጠቀም፣ ወይም ደሞ ወደፀሀይ ከመወጣቱ  ከሠላሳ ደቂቃ በፊት ቀደም ብሎ ለቆዳ አይነት የተስማማውን የፀሀይ መከላከያ ክሬም ተቀብቶ መውጣት ቢዘወተር በ አንድ ወር ውስጥ የሚፈለውን የፊት ቆዳ ለውጥ ማየት ይቻላል።

Telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍20524🥰3
👍8223🤔20🥰6👏5
በመሳሳም የሚተላለፍ በሽታ አለ?

🖲 ከንፈር ለከንፈር በመሳሳም ግዜ የሚኖር የምራቅ ንክኪ፣ በምራቅ ውስጥ የሚገኙ እና የመተላለፍ አቅም ያላቸው ጥቃቅን ህዋሳትን ማስተላለፍ ይቻላል።

🖲በአንድ ሰው ምራቅ ውስጥ ብዙ አይነት ጥገኛ ህዋሶችን ማግኘት ይቻላል

🖲የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቁ እንዲሁም የውስጥ ደዌ የበሽታ አምጪ ቫይረሶችን ከተበከለ ሰው ምራቅ ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን

🖲ከዚህ ውስጥም ከ 40 በላይ አይነት ያላቸው በሽታ አምጪ ቫይረሶች ከተበከለና በሽታው ካለበት ሰው ምራቅ ውስጥ ይገኛሉ።

🖲በምራቅ እና በቆዳ ንክኪ የመተላለፍ አቅም ያላቸው በሽታ አምጪ ቫይረሶች የመተላለፍ አቅማቸው፣ በአይነታቸው፣ በአፍ እና በከንፈር ዙሪያ ቁስለት መኖር፣ ተጓዳኝ ስር ሰደድ የውስጥደዌ በሽታዎች መኖር እና በተፈጥሮ ሁኔታ ይወሰናል።

👉የኪንታሮት ቫይረሶች  (HPV እና MC)
👉የምቺ ቫይረስ (HSV 1 እና 2)
👉የመተንፈሻ አካል አጥቂ ቫይረሶች ( Corona, RSV, EBV Adeno virus, Influenza.. etc) የመሳሰሉት የቫይረስ አይነቶች፣ ከሰው ወደሰው በትንፋሽ ፣ መሳሳምን ተከትሎ የሚኖር የምራቅ እና የቆዳ ንክኪ ምክኒያት የመተላለፍ አቅም አላቸው።

🖲ከነዚህ ውስጥ በዋነኝነት ከንፈር ለከንፈር መሳሳምን ተንተርሶ በመተላለፍ የሚታቅ የቫይረስ አይነት አለ

🖲Epstein–Barr virus (EBV) ወይም የመሳሳም ቫይረስ በመባል ይታወቃል

🖲ይህም ቫይረስ በአፍ ቆዳ ውስጥ ስለሚራባ ፣ መሳሳምን ተንተርሶ የምራቅ ንክኪ ሲኖር በቀላሉ ይተላለፋል።

🖲ይህ ቫይረስ በየትኛውንም የእድሜ ክልል ያለ ሰውን የማጥቃት አቅም ያለው ሲሆን፣ ባብዛኛው ያለው ስርጭት በታዳጊ ወጣቶች ላይ ነው

🖲በዚህ ቫይረስ የተጠቃ ሰው ላይ አነስተኛ ትኩሳት ድካም እና የጡንቻ ህመምን ተከትሎ የሚመጣ የጉሮሮ እና የቶንሲል እብጠት እና ህመም ሊያጋጥም ይችላል።

🖲ይህ ቫይረስ ታዲያ ጤናማ የበሽታ መከላከል አቅም እስካለና ለተጓዳኝ ኢንፌክሽን እስካላጋለጠ ድረስ በራሱ የመዳን አቅም ያለው ቢሆንም

🖲በነጭ የደም ህዋስ ውስጥ የመደበቅ አቅም ስላለው የበሽታ መከላከል አቀም ባነሰ ግዜ በግዜ ሂደት ለካንሰር በሽታዎችም የመዳረግ አቅም አለው።

🖲ከዚህ ውጪ ያሉ በሽታ አምጪ ቫይረሶች፣ ማለትም፣

👉የ ጉበት ቫይረስ  (HepV B,C)
👉የ HIV ቫይረስ
👉የጉድፍ እና አልማዝ ባለጭራ ቫይረስ (VZV) የመሳሰሉት እና ሌሎችም ቫይረሶች ፣ ምንም እንኳን ከተበከለ ሰው ምራቅ ውስጥ የሚገኙ ቢሆንም፣ ነገርግን ከሰው ወደሰው የመተላለፍ አቅማቸውን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ የለም።

🖲የመለጠ መረጃ (Reference ) ካስፈለገ ከታች ያለውን ጥናታዊ ፅሁፍ ይመልከቱ 👇👇👇👇👇

"Viral Diseases Transmissible by Kissing" https://www.ncbi.nlm.nih.gov/pmc/articles/PMC7150091/

Telegram 👉https://t.me/seifemed

Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb

ዶ/ር ሰይፈጋ በአካል ቀርበው ለመታከም ቀጠሮ ለማስያዝ 👉@LEKETERO የሚለውን ተጭነው ስም እና ስልክ ያስቀምጡ።
👍36878😱39👏16🥰7🤔6😢3
የእርዳታ ጥሪ

🖲 ከላይ በምስሉ የምትመለከቷት ዶ/ር ሰገን ትባላለች፣ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ፣የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም። ያቀፈችው የ8አመት ልጇ ሚካኤል ዳንኤል ይባላል

ታሪኩ በጣም የሚያሳዝን ነው

🖲ልጇ በህክምናው( ALL, acute lymphoblastic leukemia )በሚባል የደም ካንሰር ተጠቂ ነው፣ ላለፉት 2 አመት ህክምናውን በሚገባ ሲከታተል  የማገገም ተስፋ ሁሉ እየታየበት ነበር።

🖲ከሁለት ሳምንት በፊት ነው አዲስ የካንሰር እብጠት በዘርፍሬው ላይ ተገኝቶ የካንሰር መጠኑ በአዲስ መልኩ እየተስፋፋ መሆኑ የተነገራት

🖲አሁን ያለው አማራጭ ፣ከጨረር እና ከፀረካንሰር  ህክምና ዉጪ፣ አስቸኳይ የአጥንት መቅኔ ነቀሎተከላ አስፈልጎታል (bonemarrow transplant ይባላል)

🖲ህይ ህክምና ታዲያ አይደለም በሀገር ውስጥ ሊሰራ ይቅርና በውጭ ሀገራት ራሱ በጣም ውድ የሆነ ህክምና ነው ፣በመንግስት ሰራተኛ አቅም የሚቻል አደለም

🖲የቻልነውን ያህል ለመርዳት እየተረባረብን ስለሆነ የተቻላችሁን እንድትረዱን በፈጣሪስም እንጠይቃለን

ፈጣሪ ያክብርልን።

0911862592 ዶ/ር ሰገን ዮሀንስ
Dr Segen Yohannes

1000155156965
CBE ንግድ ባንክ

Gofundme: https://gofund.me/eaaac63b
😢261👍17124👏18🤔3🙏2
ከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ

🖲 ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባሉ ልጆች የዚህ የአፈጣጠር ችግር ይዘዉ ይወለዳሉ። የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ(cleft lip and palat)

🖲ወንዶች ላይ ከሴቶች በበለጠ የሚከሰት ሲሆን በግራ በኩል በብዛት ይከሰታል
🖲ከንፈር ወይም ላንቃ ብቻ ላይ ሲከሰት( isolated ) ሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል።

🖲ምክንያቱ በትክክል ይህ ነዉ ባይባልም የሚከተሉት ነገሮች በአጋላጭነት ይጠቀሳሉ

👉በዘር የሚተላለፍ (ተፈጥሯዊ )
👉በርግዝና ጊዜ ለተለያዩ ቫዮረሶች እንደ Rubella virus መጋለጥ
👉በርግዝና ሰዓት አልኮል መጠጥ፣ሲጋራ ማጨስ
👉በርግዝና ጊዜ የሚከሰት የቫይታሚን ና ፎሊክ አሲድ እጥረት መጋለጥ
👉በርግዝና ወቅት የእናትዮዋ እድሜ መግፋት
👉በርግዝና ወቅት ከሀኪም ትዛዝ ዉጭ የሚወሰዱ መድሀኒቶች
👉ሌሎች አካባቢያዊ(enviromnenyal)ነገርች

🖲ከከንፈር ና ላንቃ መሰንጠቅ ጋር የሚከሰቱ ተጎዳኝ ችግሮች

✍️የአመጋገብ ችግር ።ጡት መጥባት መቸገር
✍️የጥርስ ችግር
👉የአፍንጫ ቅርፅ አለመስተካከል ና ተደጋጋሚ ለሆነ ላይኛዉ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሺንመጋለጥ
✍️ተደጋጋሚ የጆሮ ኢንፌክሺን
✍️አፍ መፍታትና የቋንቋ እድገት ችግር

🖲ይህ ችግር ያለባቸዉ ልጆች ጡት ለመጥባት ስለሚቸገሩ ለዚህ ተብለዉ የተዘጋጁ የጡጦ አይነቶች ስላሉ እነሱን መጠቀም
✍️ችግሩ በቀዶ ህክምና ስለሚስተካከከል ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ መዉሰድ ማስተካከል ይቻላል

🖲የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ የብዙ የህክምና ባለሙያወችን ጥምረት
👉 የህፃናት ስፔሻሊ
👉ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት
👉የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና
👉የአፍና የጥርስ ስፔሻሊስት
👉የስነምግብ ባለሙያ ይፈልጋል

🖲በርግዝና ወቅት በቂ ክትትል በማድረግ፣አጋላጭ ነገሮችን በመቀነስ እንዳይከሰት መከላከል ይቻላል።


ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ
👍23676👏8😱4🙏3
የመቀመጫ ኪንታሮት

🖲 የመቀመጫ ኪንታሮትን በተመለከተ ከ ዶ/ር ስዩም አንቶኒዮስ የተሰጠ ሰፊ ማብራሪያ ነው። ሊንኩን ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ።


https://youtu.be/3_8h78Ap3C8
👍21664👏17😢11🤩1🙏1