➕➕ ዉድ የቻናላችን ተከታታዮች ➕➕
🚩👍 እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
🖲የበዓል ዕለት ከቤተሰብ ወዳጂ ዘመድ ጋ ሁነዉእየበሉ ፣እየጠጡ፣ እየተጫወቱ ከመካከላችሁ አንዱ ጥሬ ስጋ/ወይም ሌላምግብ ቢያንቀዉ ምን ያደርጋሉ?
🖲እንዲህ አይነት ገጠመኞችን የበዓል ሰሞን መስማት ያልተለመደ ነገር አይደለም።
🖲በቀላሉ ሳይደናገጡ ይህን የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ ማድረግ ይችላሉ።
🖲Hemiliches maneuver ይባላል በህክምናዉ።
🖲 ከተጎዳዉ ሰዉ በጀርባ በኩል በመቆም ሁለት እጅወን ደራርቦ በመጨበጥ ከእምብርቱ ከፍ ብሎ በመያዝ ወደዉስጥና ወደላይ መግፋት ነዉ።
🖲ይሄንን ድርጊት ሰዉየዉ አየርና ያነቀዉን ነገር እስኪያወጣ ድረስ ደጋግመን በመሞከር የመጀመሪያ ህክምና ርዳታ ማድረግ እንችላለን።
🖲ለህፃናት ሲሆን ግን ወደታች በማድረግ ከጀርባቸዉ መታ መታ በማድረግ ና በፊት በኩል ከእንብርታቸዉ ከፍ ብለን ጫን ጫን እያደረግን መሞከር እንችላለን።
🖲ይህን የመጀመሪያ ህክምና ርዳታ በማድረግ ወደ ህክምና ቦታ እስክንደርስ በአየር መተላለፊያ ቧንቧ ላይ የሚደርሰዉን መዘጋት(air way obstruction) መከላከል ይቻላል።
🚩👍 መልካም በዓል ይሁንላችሁ👍🚩
ዶ/ር ዮርዳኖስ

👍274❤83🥰16👏5😱4🤔2
➕➕ ሊፕስቲክ ➕➕
🖲ሊፕስቲክ ከሌሎች ቀለሞች ይልቅ በብዛት በቀይ ቀለም ይመረታል፣ ይህም ደሞ የራሱ የሆነ ታሪካዊ አመጣጥ እና የማህበረሰብ ተፅእኖ ስላለው ነው።
🖲አንድ ሊፕስቲክ ሲሰራ በውስጡ ደረቅ እና ለስላሳ ሰም፣ ዘይት እና ቀለም የመሳሰሉ መደበኛ ገብአቶችን ይይዝና፣ የዘቱ ከውበት ባሻገር ልዩነት እና ጠቀሜታ እንዲኖረው ደሞ እንደ ፋብሪካው ቀመር፣
👉ጠረን የሚሰጡ ማኣዛዎች
👉አንቲኦክሲዳንት ቪታሚኖች ( Vitamin A, C, E) እና
👉የፀሀይ መከላከያዎች ይጨመርባቸዋል
🖲ታዲያ እነዚህ ውህዶች ለከንፈር ቆዳ ተስማሚ ቢሆኑም፣ በተለያዩ ጥናቶች እንደታየው፣ ሊፕስቲኮች ከፋብሪካ ሲወጡ ግን ፣ለጤና ጠንቅ በሆኑ ጥቃቅን ብረታማ ንጥረ ነገሮች ይበከላሉ።
🖲ከነዚህም ውስጥ lead, cadmium, nickle , aluminium እና ሌሎችም ይገኙበታል
🖲ታዲያ እነዚህ ብክለቶች መጠናቸው ያነሰና እንደ ሊፕስቲኩ የአመራረት ጥራት የተወሰነ ቢሆንም፣ አንድ ሊፕስቲክ የብክለት መጠኑ በጥራት ቁጥጥር ምርመራ ካልታወቀ በቀር፣ ተጠቃሚን የሚያሳውቅ መረጃ ምረቱ ላይ አይፃፍም።
🖲በቀን ውስጥ ሊፕስቲክን አብዝቶና በተደጋጋሚ ግዜ በመጠቀም እንዲሁም ከንፈር ላይ ያለ ሊፕስቲክ ከምራቅ ጋር ንክኪ ኖሮት በሚዋጥበት ግዜ፣ በነዚህ ለጤና ጠንቅ በሆኑ ጥቃቅን ብረታማ ንጥረነገሮች የመበከል እድልን ያሰፋል።
🖲ስለዚህ ሊፕስቲክን አዘውትሮ ከመጠቀም ይልቅ ሲያስፈልግ ብቻ ቢሆን መልካም ነው።
https://t.me/seifemed

👍306❤75🥰27😱19👏11🤔9
በስነ ምግብ ዙሪያ ከባለሞያ የተፃፈ መፅሀፍ ነው፣ ለበለጠ መረጃ 👉https://www.youtube.com/shorts/K-GUvHye01Q
❤64👍48🥰12🙏2
➕እርድን ለምትጠቀሙ ሰዎች ➕
🖲እርድ ለቆዳ ያለውን ጠቀሜታ የተለያዩ ጥናቶች ይደግፋሉ።
👉የቆዳ ቁጣን ፣ የብብት ፀጉርን እና ጥቁረትን መቀነስ
👉የቆዳ ውፍረትን እና የቆዳ የመሳሳብ አቅምን እንዲጨምር ማድረግ እና እንዲሁም ሌሎችም ተደራራቢ ጥቅሞች እንዳሉት የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ።
🖲ታዲያ ጥናቶቹ ሲሰሩ አብዛኛውን ግዜ እርዱ እንዴት እንደተዘጋጀ ብዙ ጥናቶች ላይ አይገልጽም ። ለተለያየ ሙከራም የሚጠቀሙት የእርድ ዝርያም አይነቱ የተለያየ ነው።
🖲ሆኖም የእርድ ዝርያ ተመሳሳይ ይዘት ስላለው ቤትውስጥ አዘጋጅቶ መጠቀም ይቻላል
🖲እርድን በቤት ውስጥ ስትጠቀሙ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እና እንዲሁም ሰፋ ያለ መረጃ youtube ላይ አስቀምጫለሁ፣ ከታች ባለው አድራሻ ማግኘት ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/jMU_bN8--1k
➕አመሰግናለሁ ➕

👍351❤116🥰39👏7😱4🙏1
➕➕ መጥፎ የአፍ ጠረን ➕➕
🖲በእለት ከእለት እንቅስቀሴያችን በትራንስፖርትና ፣በስራ ቦታ ከሚያጋጥሙ ና ከሚያስቸግሩን ነገሮች አንዱ ነው።መጥፎ የአፍ ጠረን።
🖲 ጥናቶች እንደሚያሳዩት 15% ሰወች በህይወታችው የሆነ ጊዜ ላይ መጥፎ የአፍ ጠረን ያጋጥማቸዋል።ለዚህም ብዙ ምክንያቶች አሉ
🖲በአፋችን ውስጥ ብዙ ባክቴሪያወች ይኖራሉ። ምግብ ከተመገብን በኋላ እነዚህ ባክቴሪያወች በአፍና ጥርስ ላይ የቀረውን ምግብ ለሀይል ምንጭነት ይጠቀማሉ።
🖲በዚህ ኬሚካላዊ አፀግብሮት ሂደት ውስጥ
የሚፈጠረው ተረፈ ምርት በአፍ ውስጥ ለሚፈጠረው መጥፎ የአፍ ጠረን አስተዋፅኦ ያደርጋል።
🖲ይህ ሁኔታ በተለይ በምላሳችን የኋለኛው ክፍል በብዛት ይከናወናል።
🖲የአፍ መድረቅ ።ምራቅፀረ ባክቴሪያ ሚና ስላለወ አጠቃላይ የአፍ ውስጥ ጤንነትን ይጠብቃል
🖲በምራቅ አመንጪ እጢወች ላይ በሚከሰት ችግር ወይም በሌላ ምክንያት የአፍ መድረቅ ለመጥፎ የአፍ ጠረን አስተዋፅኦ ያደርጋል
👉 የቆዩ ና ያልታከሙ የድድ፣ የጉሮሮ እና የቶንሲል በሽታዎች
👉የአፍንጫ ፣ የመተንፈሻ አካል እና የሳንባ በሽታዎች
👉 ሲጋራ ማጨስ
👉መጥፎ ሺታ ሊይዙ የሚችሉ እንደ ነጪ ሺንኩርት አይነት ምግብ ማዘውተር
👉 እንዲሁም ሰገራ እና ፈስን ለረጅም ግዜ ቋጥሮ መያዝ፣ ለአፍ ጠረን መቀየር ምክኒያት ናቸው
🖲ምን መደረግ አለበት?
👉ጠዋትና ማታ ምግብ ከተመገብን በኋላ የአፍና የጥርስ ንፅህና በጥርስ ሳሙና ማፅዳት
👉ምላሳችን በተለይም ኋለኛውን ክፍል በደንብ ማፅዳት ችግሩን በ70% ይቀንሳል።
👉በቂ ፈሳሺ መውሰድ ና የአፍ ድርቀትን መከላከል።
👉ሌሎች የአፍንጫ ሳይነስ፣የጨጎራ የሳንባ በሺታ ካለ መታከም።
👉ሰው ሰራሺ ና ተገጣጣሚ ጥርስ የሚጠቀሙ ማታ ማታ ቢያወልቁትና ንፅህና ው ተጠብቆ ቢጠቀሙ።መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል ይረዳል።

👍420❤119🥰50😢3
Forwarded from EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
#በተለያየ ጊዜ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በመንገደኛ ሻንጣ እና በሌሎች የመግቢያና መውጫ ኬላዎች አማካኝነት እና ወደ ሀገር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሊገቡ የነበሩ የተለያዩ መድኃኒቶች ማለትም #Titan gel ፣ #Mara Moja ፣ #Relief እና ሌሎችም መድኃኒቶች ከባለድረሻ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ መግለፃችን ይታወቃል፡፡
በአሁኑ ወቀት ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ማወቅ እንደተቻለው በፎቶ እንደሚታየው ከዚህ በላይ የተገለጹት መድኃኒቶች በኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ባለሥልጣን ያልተመዘገቡና በህጋዊ መንገድም ወደ አገር ዉስጥ ያልገቡ ስለሆነ እና እንደ Titan gel ያለው መድኃኒት በሐኪም ብቻ በመታዘዝ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ሲሆን ነገር ግን በድብቅና በህገወጥ መንገድ ገበያ ላይ አንደሚገኙ ለማውቅ ተችሏል፡፡
ስለሆነም በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ስለሆነ፤ ጥራታቸው ፣ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ እና በጤና ላይ ከቀላል እስከ ከፍተኛ #የጤና #ጉዳት #ስለሚያደርሱ #መድኃኒቶቹን #ህብረተሰቡ #እንዳይጠቀምባቸው #እያሳሰብን፤ማንኛውም ግለሰብ/አካል Titan gel ፣ Mara Moja ፣ Relief በህጋዊ ተቋማትም ሆነ በህገወጥ መንገድ ሲያገኛቸው በባለስልጣን መስሪያቤቱ ነጻ የስልክ መስመር 8482፣በአቅሪያባቸው ለሚገኙ የክልል ተቆጣጠሪዎች ወይም ለጸጥታ አካላት በመጠቆም አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ በትህትና እንጠይቃለን፡፡
ጤናዎን ይጠብቁ!ህገወጥ፤#ጥራታቸው፣#ደህንነታቸውና#ፈዋሽነታቸው #ያልተረጋገጡ #መድኃኒቶች #የጤና #ጉዳት #ስለሚያደርሱ #ይጠንቀቁ! መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሞት ለክልል ጤና ተቆጣጣሪዎች፣የጸጥታ ካላት / #በነፃ #የስልክ #በ8482 #በመደወል #ጥቆማ በመስጠት #ይተባበበሩ፡፡

👍246🥰39❤16👏15
➕➕ የፀጉር መነቃቀል ➕➕
🖲የአንድ ጤናማ ሰው ፀጉር እድሜውን ሲጨርስ በራሱ ግዜ ይነቃቀላል።
🖲 አንድ ጤናማ ሰው ላይ በቀን ከ 60 እስከ 90 የሚደርሱ የፀጉር ዘለላዎች እድሜያቸውን ጨርሰው በራሳቸው ይረግፋሉ።
🖲ከልክ ያለፈ የፀጉር መነቃቀል መኖሩን ለማወቅ አውራጣትን እና ጠቋሚ ጣትን ብቻ በመጠቀም፣ በግምት ከ 20 እስከ 60 የሚደርሱ የፀጉር ዘለላዎችን በመያዝ በመለስተኛ ጉልበት መሳብ
🖲ይህ በሚደረግበት ግዜ፣ በጣት ከተያዙት የፀጉር ዘለላዎች መሀል 10 በመቶ እና ከዛ በላይ የተነቀሉ ከሆነ ፣
🖲ማለትም 20 የፀጉር ዘለላ ይዛችሁ፣ ሁለት እና ከዛ በላይ ፀጉር ከተነቀለ፣ ጤናማ ያልሆነ የፀጉር መነቃቀል እንዳለ ያመላክታል
🖲ጤናማ ያልሆነ የፀጉር መነቃቀል ብዙ ምክኒያቶች አሉት። ለምሳሌ፣
👉የምግብ እጥረት፣ በተለይ የ Vitamin B7, Vitamin D, እና የ Zink እጥረት ካለ።
👉በበሽታ ምክኒያት የሚመጣ የሰውነት ጫና፣ ወይም የአልጋ ቁራኛ ከመሆን ጋር ተያይዞ።
👉የደም ማነስ
👉ከወሊድ በኋላ
👉ፀጉርን ያለልክ በመጎተት
👉የራስ ቅል ላይ የሚደርሱ የፈንገስ እና የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖች
👉ላሽ፣ ራሰ በርሀነት፣ እና የራስ ቅል ላይ የሚደርሱ የተለያዩ የቆዳ በሽታዎች ለፀጉር መነቃቀል እና መመለጥ ዋና ዋና ምክኒያቶች ናቸው።
🖲የፀጉር መነቃቀልን እና መመለጥን ለማከም መጀመሪያ ምክኒያቱን ማወቅ ግዴታ ነው።
🖲 ለምሳሌ፣ በደም ማነስ ምክኒያት የመጣ የፀጉር መነቃቀል ካለ፣ ለደም ማነስ ህክምና በማረግ ብቻ የፀጉር መነቃቀልን መመለስ ይቻላል።
🖲ታዲያ፣ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ፣ ፀጉርን ያሳድጋሉ ተብለው በቤት ውስጥ የሚሰሩ፣ የሮዝመሪ ዘይት፣ የዱባ ፍሬ ዘይት፣ የሽንኩርት እና የሩዝ ውሀ የመሳሰሉት፣ ምንያህል እውነተኛ ናቸው?
🖲ለየትኛው አይነት የፀጉር መሳሳት እና መነቃቀል ነው የሚጠቅሙት?
🔴ሰፋ ያለ መረጃ youtube ላይ አስቀምጫለው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/SUAFupItbmA

YouTube
ለተነቃቀለ ፀጉር ባህላዊ ወይስ ዘመናዊ | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
👍286❤93👏28🥰11🤔3😢2👌1
🔴🔴ለራሰ በርሀነት ሚኖክሲዲልን የምትጠቀሙ ሰዎች ማወቅ ያለባችሁ ነገር
🖲ሚኖክሲዲልን መጠቀም ስትጀምሩ ፣ ከ3 እስከ 6 ሳምንት የፀጉር መነቃቀል ሊያጋጥም ይችላል።
🖲ምክኒያቱም፣ ይህ መዳኒት፣ የቆዩ የፀጉር ዘለላዎችን በግዜያዊ ሁኔታ ፣እድሜያቸውን ቶሎ እንዲጨርሱ ስለሚያደርጋቸው ነው።
🖲ሚኖክሲዲል ማህንነትን እና ስንፈተ ወሲብን አያመጣም፣
የተወሰነ ሰው ላይ ስንፈተ ወሲብን የሚያመጣ የፀጉር ማብቀያ ግን አለ።
🖲ፊናስቴራይድ ይባላል፣ ከሚኖክሲዲል የተሻለ ለውጥ የሚያሳይ እና በሚዋጥ መልኩ በሀኪም ትእዛዝ ብቻ ይሰጣል።
🖲የፀጉር መብቀያ መዳኒቶች በቀን በቀን እየተጠቅማችሁ ለውጥ ለማየት ከ 4 እስከ 6 ወር ግዜ ይፈጃል። ሁሉም ሰው ደሞ ተመሳሳይ ለውጥ አያሳይም
🖲ሚኖክሲዲል ወደ 10 የሚጠጉ ብራንዶች አሉት፣ ከነዚህ ውስጥ የመጀመሪያው እና ለገበያ ፈቃድ ያገኘው rogain የሚባለው ምርት ሲሆን፣ በፈሳሽ እና በአረፋ መልክ የተዘጋጀ ነው።
🖲ከሌሎቹ ምርቶች ይልቅ፣ በአረፋ መልክ የተዘጋጀው ምርት፣ ለአጠቃቀም አመቺ እና አነስተኛ የጎንዩሽ ጉዳት ስላለው ከፈሳሹ ይልቅ አረፋው (foam) ተመራጭ ነው።
🖲የበለጠ ማብራሪያ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ፣ ለመመልከት ይሄንን ይጫኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/w1PYCfAlBbI

የፀጉር ማብቀያ መዳኒት በሚቀባ | Minoxidil | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
👍200❤82🥰19👏7
➕➕ ደርማሮለር ለምትጠቀሙ ሰዎች ➕➕
🔴 እባካችሁ ደርማ ሮለርን ከመጠቀማችሁ በፊት አንድ ግዜም ቢሆን የቆዳ ሀኪምን አማክሩ
🖲 ደርማ ሮለር ወይም በህክምና ስሙ (Microneedling) የሚሰራው ፣ ጥቃቅን መርፌዎችን በመጠቀም የስረኛው የቆዳ ክፍል ላይ በመጠኑ ጉዳት በማድረስ፣ የሰውነት ተፈጥሮአዊ እደሳ መንገድን በመጠቀም፣
👉 አነስተኛ ጠባሳዎችን ማስተካከል
👉የተጨማደደ ቆዳን በመጠኑ በመመለስ፣ እንዲሁም
👉በራሰ በርሀነት ምክኒያት የሚመጣ የፀጉር መሳሳትን ለመመለስ የሚያገለግል የቆዳ ህክምና መንገድ ነው።
🖲 ደርማ ሮለርን ለመጠቀም ፣ የመርፌውን ርዝመት እና ለምን እና እንዴት መጠቀም እንዳለባችሁ የማታውቁ ከሆነ፣ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት አይቻልም።
🖲 እንደውም ከአጠቃቀም ስህተት የተነሳ፣ ላልተፈለገ የቆዳ ኢንፌክሽን እና ጠባሳ ሊያጋልጥ ይችላል።
🖲 ደርማ ሮለር መጠቀም ከፈለጋችሁ ማድረግ ያለባችሁ ነገር
👉🚩 አነስተኛ ርዝመት ያለውን መርፌ መምረጥ ከ 1.5 mm በታች መሆን አለበት።
👉🚩ከመጠቀማችሁ በፊት ደርማሮለሩን በፈላ ውሀ ለ 15 ደቂቃ መቀቀል ወይም 70% አልኮል ውስጥ ለ 15 ደቂቃ መዘፍዘፍ።
👉🚩በደርማ ሮለር የሚታሽበትን የቆዳም ሆነ የራስ ቅል ክፍል በሳሙና እና በውሀ በደምብ ማጠብ፣ ወይም በ 70% አልኮል አስቀድሞ ማሸት እና እስኪደርቅ መጠበቅ።
👉🚩በመቀጠልም ደርማ ሮለሩን በቦታው ላይ ደም እስከሚታይ ድረስ ብቻ ማሸት
🖲የምትጠቀሙት ለመጀመሪያ ግዜ ከሆነ በወር 2 ግዜ ብቻ፣ ለ 1 ወር በዚህ መልኩ ተጠቅማችሁ፣ በመቀጠልም በሳምንት 1 ግዜ ብቻ መጠቀም ይቻላል።
🔴 ከሳምንት በታች ባነሰ ግዜ እንዳትጠቀሙት።
🔴እባካችሁ ይህንን ደርማ ሮለር መጠቀም የሌለባቸው ሰዎች ስላሉ በ YouTube ዝርዝር መረጃውን ከነ ጉዳቱ አስቀምጫለሁ።
🔴ደርማሮለር ከመጠቀማችሁ በፊት የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ ሙሉ መረጃውን ተመልከቱ
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/b0yciBZuj5w

ለተነቃቀለ ፀጉር ባህላዊ ወይስ ዘመናዊ ? : Dermaroler, ደርማሮለር እና finasteride | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
👍265❤73🥰26🤔15👏13😱13
➕Neo hair lotion ታውቁታላችሁ? ➕
🖲ፀጉር ማብቀያ ተብሎ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ሲተዋወቅ ያያችሁት ይመስለኛል።
🖲Neo hair lotion በመባል የሚታወቀው የ ታይላንድ ምርት ከዘመናዊ የፀጉር ማሳደጊያ መዳኒቶች የተሰራ ቅባት ሳይሆን፣ ፀጉርን ያሳድጋሉ ከሚባሉ ፣የእፅዋት ወጤቶች የተቀመመ ስለመሆኑ በምርቱ ላይ የተገለፀ ነው።
🖲ታዲያ በውስጡ የያዛቸው ንጥረነገሮች፣ ራሰ በርሀነት ሲጀምር፣ እየከሰመ ያለ ፀጉርን የመመለስ የተወሰነ አቅም እንዳላቸው ጥናቶች ይደግፋሉ።
🖲ነገር ግን፣ እነዚህን ምርቶች፣ ማለትም፣ በዘመናዊም ሆነ በባህላዊ የተቀመጡ የፀጉር ማብቀያዎችን ተጠቅማችሁ ለውጥ ለማየት በአማካይ ከ4 እስከ 6 ወር በቀን በቀን መጠቀም ያስፈልጋል ።
🖲ሁሉም ሰው ላይ ተመሳሳይ የሆነ እና የሚፈለገውን ያህል ለውጥ አያስገኝም። ለውጥ ከታየ ደሞ፣ መጠቀም ስታቆሙ ፣በግዜ ሂደት ፀጉር ወደቀድሞ ይዞታው ይመለሳል
🖲ለማንኛውም Neo hair lotion ለመጠቀም ከመወሰናችሁ በፊት፣ ማወቅ ያለባችሁን ነገር ዩቲዩብ ላይ በሰፊው አስቀምጫለሁ ።
🖲የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ በቀላሉ መመልከት ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/Tfe7OG2Ftg0

Neo የፀጉር ቅባት
👍266❤84🥰27🤔22👏20
➕➕ የወር አበባ በሄደ በሚቀጠለው ቀን ግንኙነት ባደርግ ርግዝና ይፈጠራል?➕➕
🖲አንድ ቋሚ የወር አበባ ያላት ሴት የወር አበባ በአማካይ በየ 28 ቀኑ ይመጣል ተብሎ ይታሰባል
🖲ነገር ግን ከ21 እሰከ 35 (ሲፈጥን በየ 21 ቢበዛ ደግሞ በየ 35 ቀን ሊመጣይችላል) ማለት ነው
🖲ስለዚህ ርግዝና የሚፈጠረው መቸ ነው የማይፈጠረውስ መቸ ነው ?
🖲በአማካይ መደበኛ የሚባለውን ወስደን ስናይ የወር አበባ በየ 28 ቀን ይመጣል::
🖲የወር አበባ በጀመረ የመጀመሪያወቹ 5 ቀናት በአማካይ የወር አበባ የሚፈሰባቸው ቀናት ናቸው።
🖲ከ 6ኛው እስከ 14 ኛው ቀን ያለው Follicular phase ይባላል።ይህም ኢስትሮጂን :FSH የሚባሉት ሆርሞኖች የሚጨምሩበትና የማህፀን ግድግዳ እየወፈረ የሚሄድበት ጊዜ ነው
🖲14 ኛው ቀን ውፃት(ovulation) ይባላል። እንቁላል ለፅንሰት ዝግጁ ሆኖ ይወጣል ማለት ነው።
🖲በዚህ ግዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ከተፈፀመ ርግዝና የመፈጠር እድሉ በጥም ከፍተኛ ነው፣ ከ 14 _28ኛው ያለው ቀን lutheal phase ይባላል።ርግዝና ከተፈጠረ ማህፀን ፅንሱን ለማሳደግ ዝግጁ የሚሆንበት ጊዜ ካልተፈጠረ ደሞ የዳበረው የማህፀን ወለል በመፈራረስ በወር አበባ መልክ የሚፈስበት ጊዜ ነው።
🖲ሰለዚህ 14 ኛው ቀን ላይ ርግዝና ይፈጠራል።ነገር ግን የወንድ ስፐርም የሴትብልት ላይ እስከ 5 ቀን ድረስ ሳይሞት ይጠብቃል እንቁላልም ከወጣ ጀምሮ እስከ 24 ሰዓት ይጠብቃል
🖲 ስለዚህ ከ 14 ኛው ቀን 5 ቀን ወደ ፊት ና 3 ቀን ወደ ሗላ ርግዝና የሚፈጠርባቸው ቀናት ናቸው።
🖲የወር አበባ በየ 28 ቀን የማይመጣ ከሆነ ና ቋሚ ከሆነ ከ14 ኛው ቀን እሰከ 28 lutheal phase ያልነው ቋሚ 14 ቀን ስለሆነ ተመሳሳይ ሰሌት በመጠቀም ማወቅ ይቻላል።

👍496❤128👏67😱6🎉2🙏2
➕➕ የፊት ክሬሞችን ከመምረጣችሁ በፊት ➕➕
🖲 መቼም ግዜ ቢሆን የፊት ቅባቶችን ከገበያ ስትገዙ: ለምን እንደምትገዙ እና የገዛችሁት ቅባት ከቆዳችሁ ጋር እንደሚሄድ እና እንደማይሄድ ካላወቃችሁ: እንዲሁም ደሞ የገዛችሁአቸው ቅባቶች: ጥራት የሌላቸው እና ይዘታቸው የማይታወቅ ከሆነ:
🖲 አንዳንዴ ሊመልስ ለማይችል የቆዳ ጠባሳ ከመጋለጥ ባሻገር: አንዳንድ ቅባቶች በድብቅ ከሚይዙት መዳኒት የጎንዮሽ ጉዳት የተነሳ: ለአንዳንድ የውስጥ ደዌ በሽታዎችም የመጋለጥ እድል አለ::
🖲እዚህ ቪዲዮ ላይ የቀረበው መረጃ አንዳንድ የፊት ቅባቶች ውስጥ ሊጨመሩ የሚችሉ መዳኒቶችን እና: ሊያስከትሉ የሚችሉትን የጎንዮሽ ጉዳት ማስተማሪያ ነው::
አመሰግናለሁ
እነዚህን የፊት ክሬሞች እባካችሁ አትጠቀሟቸው
https://youtu.be/kzdE58BkHiA

እነዚህን የፊት ክሬሞች ከመጠቀማችሁ በፊት... | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
🖲 መቼም ግዜ ቢሆን የፊት ቅባቶችን ከገበያ ስትገዙ: ለምን እንደምትገዙ እና የገዛችሁት ቅባት ከቆዳችሁ ጋር እንደሚሄድ እና እንደማይሄድ ካላወቃችሁ: እንዲሁም ደሞ የገዛችሁአቸው ቅባቶች: ጥራት የሌላቸው እና ይዘታቸው የማይታወቅ ከሆነ:
🖲አንዳንዴ ሊመልስ ለማይችል የቆዳ ጠባሳ ከመጋለጥ ባሻገር: አንዳንድ ቅባቶች በድብቅ ከሚይዙት መዳኒት የጎንዮሽ ጉዳት የተነሳ: ለአንዳንድ የውስጥ ደዌ በሽታዎችም…

👍331❤142🥰52👏51😢8🙏1
➕➕ የትኛው ሳሙና ይሻላል? ➕➕
🖲 በልብስ ሳሙና መታጠብ ቆዳን አመድ ያስመስላል።
🖲ከገላ ሳሙናዎች ውስጥ ለደረቅ እና ለሚቆጣ ቆዳ Dove የተሻለ ሳሙና ነው።
🖲 አንድ ሳሙና ሲሰራ ቁሻሻን የማስለቀቅ አቅሙ ከፍተኛ በሆነ መጠን፣ ቆዳን የማድረቅ መጠኑም በዛውልክ ይጨምራል፣
🖲አብዛኞቹ የገላ ሳሙናዎች ከ 9 እስከ 11 የሚደርስ የ ph ልኬት አላቸው።
🖲የገላ ሳሙናዎች እንደ ምርታቸው፣ አይነታቸው እና ጥቅማቸው ተጨማሪ መዳኒቶች፣ ቫይታሚኖች ፣ የቆዳ ማርጠቢያዎችን እና ማኣዛዎች ይጨመርባቸዋል።
🖲ታዲያ፣ በተለምዶ ሳሙና ተብለው ይጠሩ እንጂ፣ አንድአንድ ሳሙናዎች መደበኛ የሳሙና ይዘት የላቸውም
🖲ይዘታቸው (Synthetic Detergent) የሆነ፣ ወይም ስማቸው ሲያጥር ( Syndet ) በመባል የሚታወቁት መታጠቢያዎች፣ አብዛኛወን ግዜ ለቆዳ ተስማሚ ናቸው።
🖲ስለቆዳ አይነቶች እና ስለ ተስማሚ የሳሙና አይነቶች በሰፊው ዩቱዩብ ላይ አስቀምጫለሁ። አመሰግናለሁ።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/r1-mJhp-ahQ

ይሄኛው ይሻላል | የፊት ሳሙና እና የቆዳ አይነትን በተመለከተ
ይህ ቪዲዮ፣ አጠር ባለ መልኩ የተዘጋጀ፣ ስለ የፊት ቆዳ አይነቶች እና መሰረታዊ የቆዳ ጤና አጠባበቅን በተመለከተ የሚገልፅ እና፣ ለፊት ቆዳ መጠቀም የሚያስፈልገውን የሳሙና አይነቶች፣ ባጭሩ ለማስተማር የተዘጋጀ ነው።
ተመሳሳይ እና ተጨማሪ መረጃዎችን በቴሌግራም ቻናሌ ማግኘት ይችላሉ።
Telegram Chanel 👉 https://t.me/seifemed

👍292❤99🥰51👏27😱11🙏2