Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.7K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
#በተለያየ ጊዜ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በመንገደኛ ሻንጣ እና በሌሎች የመግቢያና መውጫ ኬላዎች አማካኝነት እና ወደ ሀገር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሊገቡ የነበሩ የተለያዩ መድኃኒቶች ማለትም #Titan gel ፣ #Mara Moja ፣ #Relief እና ሌሎችም መድኃኒቶች ከባለድረሻ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ መግለፃችን ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ወቀት ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ማወቅ እንደተቻለው በፎቶ እንደሚታየው ከዚህ በላይ የተገለጹት መድኃኒቶች በኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ባለሥልጣን ያልተመዘገቡና በህጋዊ መንገድም ወደ አገር ዉስጥ ያልገቡ ስለሆነ እና እንደ Titan gel ያለው መድኃኒት በሐኪም ብቻ በመታዘዝ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ሲሆን ነገር ግን በድብቅና በህገወጥ መንገድ ገበያ ላይ አንደሚገኙ ለማውቅ ተችሏል፡፡

ስለሆነም በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ስለሆነ፤ ጥራታቸው ፣ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ እና በጤና ላይ ከቀላል እስከ ከፍተኛ #የጤና #ጉዳት #ስለሚያደርሱ #መድኃኒቶቹን #ህብረተሰቡ #እንዳይጠቀምባቸው #እያሳሰብን፤ማንኛውም ግለሰብ/አካል Titan gel ፣ Mara Moja ፣ Relief በህጋዊ ተቋማትም ሆነ በህገወጥ መንገድ ሲያገኛቸው በባለስልጣን መስሪያቤቱ ነጻ የስልክ መስመር 8482፣በአቅሪያባቸው ለሚገኙ የክልል ተቆጣጠሪዎች ወይም ለጸጥታ አካላት በመጠቆም አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ በትህትና እንጠይቃለን፡፡

ጤናዎን ይጠብቁ!ህገወጥ፤#ጥራታቸው፣#ደህንነታቸውና#ፈዋሽነታቸው #ያልተረጋገጡ #መድኃኒቶች #የጤና #ጉዳት #ስለሚያደርሱ #ይጠንቀቁ! መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሞት ለክልል ጤና ተቆጣጣሪዎች፣የጸጥታ ካላት / #በነፃ #የስልክ #በ8482 #በመደወል #ጥቆማ በመስጠት #ይተባበበሩ፡፡
👍246🥰3916👏15