Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.7K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
#ሰው #ሰራሽ #እርግዝና

🖲ሰው ሰራሽ እርግዝና መሰለኝ የሚባለው፣ ምናልባት ከተሳሳትኩ አርሙኝ፣ በህክምናው IVF ይባላል

🖲Assisted Reproductive technology ከሚባሉት ውስጥ ይመደባል

🖲እንቁላልና ሀብለዘርን ወስዶ በላብራቶሪ ውስጥ ፅንስን መፍጠርና እርግዝና እንዲይዝ መልሶ በመሀፀን ውስጥ ማስቀመጥ ማለት ነው በቀላሉ ሲተረጎም

🖲ይህ ህክምና በሀገራችን ውስጥ መሰራት ከተጀመረ 4 አልፎታል። ከዚህም በበለጠ መልኩ ICSI የተባለ መንገድም በሀገራችን ውስጥ እየተጀመረ ነው።

🖲ውጤታማነቱ በእድሜ እና በእርግዝና ታሪክ ይወሰናል፣ ማለትም ከዚህ በፊት አርግዘው የሚያውቁ ሴቶች እና እድሜያቸው ከ 35 አመት በታች ከሆነ፣ በዚህ መንገድ የማርገዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው

🖲ይህ ህክምና ለሁሉም እርግዝና ላልተሳካላቸው ሴቶች የሚሰጥ አይደለም። ያለመፀነስ ችግር በብዙ ምክኒያቶች ከሁለቱም ፆታዎች ሊመጣ ይችላል።

🖲የመሀንነት ህክምና መጀመር ያለበት ሁኔታ

👉እድሜያቸው ከ 35 በታች ለሆኑ ሴቶች፣ ያለምንም የእርግዝና መከላከያ በሳምንት 2 ግዜ ግንኙነት እየተደረገ ለ 1 አመት ያህል እርግዝና ካልተፈጠረ

👉እድሜያቸው ከ 35 አመት በላይ ከሆነ ደሞ በዚሁ ሁኔታ ለ6 ወር ቆይተው እርግዝና ካልተፈጠረ፣  ሁለቱም ፆታዎች የመካንነት ምርመራ ማረግ ይጠበቅባቸዋል።

🖲መካንነት እንደ አመጣጡ የሚታከም የመራቢያ አካል ችግር ነው።


Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
Tiktok 👉https://vm.tiktok.com/
YouTube 👉https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
👍213👏1