ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
497 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
አመሰገኑ

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት የኮሪደር ልማት ስራዎቻችን የእያንዳንዱ ቀን እና ምሽት ስራ እየተገመገመ የሚስራ ስራ መሆኑን ገልጸው ፤ ልማቱ ለመረጠን እና ቃል ለገባንለት የከተማችን ነዋሪ የኢኰኖሚ ፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ፤ከዘመናዊነት ጋር የተቃኘ አሰራርን በመዘርጋት እና በማሳለጥ ለከተማችን የኢኮኖሚ እድገት ወሳኙን ሚና እንድንወጣ ያስቻለን ነዉ ብለዋል፡፡

በሂደቱም በምታደርጉት ተሳትፎ በአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ታሪካዊ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ መሆናችሁን ተረድታችሁ ስራውን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በጥራት እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ ብለዋል።

በታሪክ ሂደት የከተማዋን የሥራ ባህል በቀየርንበት ፤ ቀንና ለሊት በስራችሁበት ጎን ለሥራ ጥራት የምትሰጡት ትኩረት እንዲሁ ባህል ሆኖ መቀጠል እንዲችል መስራት አለብን ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ ሳይት በየምሽቱ በሥራ ላይ ለነበሩ ሰራተኞችን የእራት ግብዣ እያደረጉ ያሉትን የአካባቢውን ነዋሪዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66911af7891c8163b27b4eec

Purchase Requisition Coffee & Tea Refreshment
Catering Service at Ministry of Tourism Head Office, Addis Abeba
- Published by Ministry of Tourism

💵 ፕሮፎርማ Sun Jul 14th, 2024 - Fri Jul 12th, 2024

ምንጭ
#Ethiopia

በነዳጅ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መከልከሉ ይታወቃል።

ይኸው ክልከላ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችን እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።

ምንም ዓይነት የሕግ ድንጋጌ ሳይኖር ወይም ግልጽ የሆነ ሕግ ሳይወጣ እና ሕግን የተከተለ ክልከላ ሳይኖር ' ከላይ በወረደ ወይም ተሰጠ ' በተባለ አቅጣጫ ላይ ብቻ በመመሥረት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ መከልከሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችን እያተጓጎለ እንደሆነ ጠቁሟል ኮሚሽኑ።

ኮሚሽኑ ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ እንድሂህ ብሏል ፦

- በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል፣ በሕግ አግባብ ወይም ድንጋጌ የታገዘ አይደለም፡፡

- ለማንኛውም አይነት አገልግሎት የሚውሉ ከባድ የጭነት ተሽከርኮሪዎች፣ የእርሻ ትራክተሮችና ለቱሪስት ማስጎብኛ የሚያገለግሉ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ነው፡፡

- በግብርና ፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ፣ በሆልቲካልቸር ፣በቱሪዝም ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በግንባታ እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው።

- በተለይ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ልዩ ባህሪ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እንዲቻል ሚኒስቴሩ ፈቃድ ሊሰጥ ይገባል።

#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66925022e468e54e5443f544

አይብ እና ቅመማቅመም ግዥ
- Published by Ethiopian Civil Service University

💵 ፕሮፎርማ Sat Jul 13th, 2024 - Sat Jul 13th, 2024

ምንጭ
🔈 #ተጠንቀቁ

ወደ ተለያዩ ውጭ ሀገራት " ስራ ነው " በሚል ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ ወጣቶቻችን የትም ሀገር ይሁን የምትሄዱት ስራው ምን እንደሆነ እና ለደህንነታችሁም አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጡ።

" ለስራ ውጭ እንላካችሁ " የሚሉትን ደላሎችንም ሆነ ኤጀንሲዎች ፦
- ስራው ምንድነው ?
- በትክክል ድርጅቱ ያለበት ሀገር የት ነው ?
- የድርጅቱን ህጋዊነት የሚያሳይ ማስረጃ አሳዩን !
- ባለበት ሀገር ሕጋዊ ስርዓት የተመዘገበበትን ፋይል አሳዩን ! ብላችሁ ጠይቋቸው።

ከዚህ ውጭ በተድበሰበሰ ሁኔታ " ጠቀም ያለ ገንዘብ ነው የምታገኙት " በሚል ብቻ መረጃ ፤ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ የሚደረግ የውጭ ሂደት ብታቋርጡ መልካም ነው።

አንዳንድ ስለ ገንዘብ እንጂ ፍጹም ስለ ሰው ህይወት የማያሳስባቸው ደላሎች እና ኤጀንሲዎች በርካታ ወጣቶችን እያታለሉ መጀመሪያ ወዳሉት ሳይሆን ወደ ሌላ ምንም ደህንነቱ ወዳልተረጋገጠ ሀገር እየላኩ ሰዎችን በማጭበርበር ላይ ወደ ተሰማሩ ድርጅቶች እያስገቧቸው ነው።

በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በሚቆዩበት ወቅት በርካታ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ይፈጸምባቸዋል።

የወጣትነት ጊዜያችሁ ሳያልፍ ህይወታችሁን ለማሻሻል ብላችሁ እጅግ ተቸግራችሁ ፤ ቤተሰብም አስቸግራችሁ ብዙ ብር ከፍላችሁ ወደ ውጭ ሀገር የምትሄዱ ልጆች ስለምትሄዱበት ሀገር እና ስራ በደንብ አጣሩ አንብቡ

ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነውና በስልካችሁ ላይ ገብታችሁ የምትሄዱበት ሀገር ስላለው ደህነት፣ ስላለው የስራ ሁኔታ ፣ እናተም ትስሩታላችሁ ስለሚባለው ስራ በደንብ አረጋግጡ።

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
📷

ዛሬ መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ይጓዝ የነበረ  ተሳቢ መኪና ጌዴኦ ዞን፣ ወናጎ ወረዳ ውስጥ ተንሸራቶ ሲወድቅ ከመብራት ሽቦ ጋር ተገናኝቶ እሳት በመነቱ መኪናውን በእሳት ተቀጣጥሎ ወድሟል።

መኪናው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ ተርፈዋል።

ሌላኛው የሰሌዳ ቁጥር '  ኦ.ሮ 27555 ' የህዝብ ማመላለሻ መንገድ ስቶ ተገልብጦ በደረሰ አደጋ ሶስት ሰዎች ተጎድተው ዲላ ሆስፒታል ገብተው ህክምና ላይ ናቸው።

ፖሊስ አደጋ የደረሰው በነበረው ዝናብ ምክንያት በመንሸራተት እንደሆነ ጠቁሞ የክረምት ወቅቱ በመግባቱ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

#ጌዴኦዞንኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66951d557c0ca4bafb80cd88

የሙቀት መከላከያ ኮሮላ መኪና /double face/++
የሙቀት መከላከያ ኮሮላ መኪና /double face/++
- Published by Ethiopia Pharmaceutical Supplies Service

💵 ፕሮፎርማ Mon Jul 15th, 2024 - Mon Jul 15th, 2024

ምንጭ
ትኩረት- ለወባ- በሽታ!!!

#Ethiopia | የወባ ወረርሽኝ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል !

የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸው ተግባራት እንደሚከተለው ቀርቧል

👉አጎበርን በአግባቡ መወጠርና ሁሌም
በአግባቡ መጠቀም

👉በፀረ-ወባ ኬሚካል በተነከረ አጎበር
ውስጥ መተኛት

👉የአጎበር አጠቃቀም ላይ ለነፍሰጡር.
እናቶችና ለህጻናት ቅድሚያ መስጠት

👉አጎበርን ለታለመለት አላማ በማዋልና
መጠቀም

👉የቤት ውስጥ የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል
ቤትዎን ማስረጨት
👉በጸረ-ወባ ኬሚካል የተረጨ ግድግዳ ላይ
እስከ 6 ወር ቀለም አለመቀባት፣ እበት
ባለመለቅለቅ፣ በወረቀት አለመሸፈን

👉በግቢዎና በአካባቢዎ ያሉ ዉሃ የሚያቆሩ
ቦታዎችንና ቁሳቁሶችን እንደ መኪና ጎማ፣
የሸክላ ስባሪዎች፣ የወዳደቁ ጣሳዎች
ማስወገድ፣ ማፋሰስ፣ መደልደል

👉ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማላብ፣ ራስ
ምታት፣ የሰውነት መጓጎል፣ ማቅለሽለሽና
ማስመለስ የወባ በሽታ ምልክቶች ሊሆኑ
ስለሚችሉ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና
ተቋም በመሄድ ምርመራ ያድርጉ።

👉በምርመራ የወባ በሽታ መሆኑ ከተረጋግጠ
በጤና ባላሙያ በታዘዘሎት መሰረት
መድኃኒቱን ጨርሶ መውሰድ

👉በወባማ አካባቢዎች ከአንድ ወር በላይ
ቆይተው ሲመለሱ የወባ በሽታ ምርመራ
በማድረግ ራስዎን ቤተሰቦን እና
ማህበረሰቡን ከወባ በሽታ ይከላከሉ:


Via ጌጡ ተመስገን

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66962883fe3d907205e10d16

procurement of labour works 11
- Published by Amanuel Mental Specialized Hospital

💵 ፕሮፎርማ Tue Jul 16th, 2024 - Tue Jul 16th, 2024

ምንጭ
በአዲስ አበባ ከተማ ኮድ 2 በፈረቃ ሊሆን ነው

#Ethiopia | በአዲስ አበባ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት፤ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው፡፡

በከተማዋ ጠዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል ያሉት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ሁነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው እቴሳ ናቸው፡፡

እቅዱ በ2 እና በ3 ወር ጊዜ ውስጥ፤ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካራች በፈረቃ አንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የኦሮሚያንና የፌዴራልን ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755 ሺ በላይ ናቸው ያሉት አቶ አያሌው ከእነዚህ ውስጥ የበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጠዋትና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ሲሉም ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Via ሸገር ኤፍኤም

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth