ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
495 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
🔈 #ተጠንቀቁ

ወደ ተለያዩ ውጭ ሀገራት " ስራ ነው " በሚል ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ ወጣቶቻችን የትም ሀገር ይሁን የምትሄዱት ስራው ምን እንደሆነ እና ለደህንነታችሁም አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጡ።

" ለስራ ውጭ እንላካችሁ " የሚሉትን ደላሎችንም ሆነ ኤጀንሲዎች ፦
- ስራው ምንድነው ?
- በትክክል ድርጅቱ ያለበት ሀገር የት ነው ?
- የድርጅቱን ህጋዊነት የሚያሳይ ማስረጃ አሳዩን !
- ባለበት ሀገር ሕጋዊ ስርዓት የተመዘገበበትን ፋይል አሳዩን ! ብላችሁ ጠይቋቸው።

ከዚህ ውጭ በተድበሰበሰ ሁኔታ " ጠቀም ያለ ገንዘብ ነው የምታገኙት " በሚል ብቻ መረጃ ፤ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ የሚደረግ የውጭ ሂደት ብታቋርጡ መልካም ነው።

አንዳንድ ስለ ገንዘብ እንጂ ፍጹም ስለ ሰው ህይወት የማያሳስባቸው ደላሎች እና ኤጀንሲዎች በርካታ ወጣቶችን እያታለሉ መጀመሪያ ወዳሉት ሳይሆን ወደ ሌላ ምንም ደህንነቱ ወዳልተረጋገጠ ሀገር እየላኩ ሰዎችን በማጭበርበር ላይ ወደ ተሰማሩ ድርጅቶች እያስገቧቸው ነው።

በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በሚቆዩበት ወቅት በርካታ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ይፈጸምባቸዋል።

የወጣትነት ጊዜያችሁ ሳያልፍ ህይወታችሁን ለማሻሻል ብላችሁ እጅግ ተቸግራችሁ ፤ ቤተሰብም አስቸግራችሁ ብዙ ብር ከፍላችሁ ወደ ውጭ ሀገር የምትሄዱ ልጆች ስለምትሄዱበት ሀገር እና ስራ በደንብ አጣሩ አንብቡ

ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነውና በስልካችሁ ላይ ገብታችሁ የምትሄዱበት ሀገር ስላለው ደህነት፣ ስላለው የስራ ሁኔታ ፣ እናተም ትስሩታላችሁ ስለሚባለው ስራ በደንብ አረጋግጡ።

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth