ምጽዋት ብዛት ወይስ ጥራት?
የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ። የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው ። የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፤ ታድያ ለወንድምህስ የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነውን? መሆን የለበትም። ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው። ከምትለብሳቸው ሁለቱ ልብሶች አንዱን ስጠው። የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው። ለአንተ የምትመኝውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ። "እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40 ያለውን ቃል መለስ ብለህ አስብና የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋእት እንዴት እንደነበረ አሰብ። "አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋእቱ ተመለከተ።"ዘፍ 4፥4 ለምን መረጠለት? ብትል አቤል ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጎ ስላቀረበ ነው። በሐዋርያት ሥራ 4፥34-35 ላይ ሰፍሮ የሚገኝውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40
#ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር

October 23, 2018