የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
“እያንዳንዱ ስለ ክርስቶስ የሚነገረው ነገር ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከፍ ከፍ የሚያደርጋት ነው፡፡ ከክብሯ ሁሉ ከፍ ያለው ክብር ግን በመስቀሉ የተደረገው ድንቅ ነገር ነው፡፡ ሐዋርያው ይህን ቢያውቅ “ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክሕት ከእኔ ይራቅ” አለ ገላ.6፡14፡፡
ሲወለድ ጀምሮ ዕውር የነበረው ሰው በሰሊሆም ውኃ ታጥቦ እያየ መምጣቱ ድንቅ ነው፡፡ ሆኖም ዓለም ከታወረበት ዕውርነት አውጥቶ ብርሃን እንዲያይ ካደረገው ከመስቀሉ ጋር ሲነጻጸር ይህ ምንድነው? ከሞተ አራት ቀን የሆነው በመቃብርም ያደረው አልዓዛር እንደገና መነሣቱ ታላቅ ነገር ነው፡፡ ሆኖም በኃጢአት የሞተውን ዓለም ነፍስ ዘርቶ እንዲነሣ ካደረገው ከመስቀሉ ኃይል ጋር ሲነጻጸር ይህ ምንድነው? አምስቱ እንጀራዎች አምስት ሺሕ አባዎራዎችን ማጥገባቸው ድንቅ ነው፡፡ ሆኖም ዓለም ሁሉ ነግሦበት ከነበረው ረኀብ በዕውቀት ብርሃን እንዲጠግቡ ካደረገው ከክርስቶስ ኃይል ጋር ሲነጻጸር ይህ ምንድነው? ሰይጣን ለዓመታት ሲያሰቃያት የነበረችው ሴት ከእስራት መፈታትዋ ታላቅ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ሁላችንን በኃጢአታችን ምክንያት ተጠላልፈን እንድንታሰር የሆንበትን የኃጢአት ሰንሰለት ከበጣጠሰው ኃይል ጋር ሲነጻጸር ምንድነው?
ዓለም ስለዳነ የምታደንቁ አትሁኑ! ይልቁን የሞተው ዕሩቅ ብእሲ ሳይሆን የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ በመሆኑ ይህንን አድንቁ እንጂ፡፡”
ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
መምህር ምህረተ አብ አሰፋ
ከ መናፍቁ ፓስተር ዳዊት ጋ
ያደረገው ቃለ መጠይቅ
እንድታነቡ "ጥቅስ ብቻ ስጠኝ"ታለቅ ፍጥጫ!!!!!!!
ይህን ጥያቄና መልስ ለሌሎች በማድረስ ብዙዋችን ከጥፍት
እንመልስቸው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት።
አብረን ኣንከታተል!
ጴንጠው-- ቆይ ግን ታቦት ምንድ ነው? ጥቅስ ብቻ ስጠኝ
ለእያንዳንዱ
መልስህ?
ኦርቶዶክሱ-- ታቦት ማለት ቤተ ሀገሬ ከምለው ከግዕዝ ቃል
የወጣ ስሆን
"ማደርያ" ማለት ነው። የምን ማደርያ? ካልከኝ የቃሉ ማደርያ
ኦ.ዘፀ
25፥22
ጴንጠው--እና ድሮ ለቃሉ ማደርያ ነው በአድስ ኪዳን ለምን
አስፈለገ?
ኦርቶዶክሱ--- በአዲስ ኪዳን የጌታችን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር
ደሞ
ይፈተትበታክ(በዮሐ .ወ 6፥54) የምታገኘው ይህ ሥጋውና ደሙ
የምከብርበት ዙፋን ነው።
ጴንጠው - ታቦት ጣኦት ነው እግዚአብሔር ከእኔ ባቀር የተቀረፀ
ምስል
ለራስህ አታድርግ አላለም ወይ?
ኦርቶዶክሱ - ታቦት ጣኦት ነው ካልክ ታቦትን ቀርፆ ለሙሴ
የሰጠው
እግዚአብሔር ነውኮ ኦ.ዘፀ 32፥16 እና እግዚአብሔር ከእኔ
በቀር ለላ
የተቀረፀ ምስል ለራስህ አታድርግ እያለ ለምን ቀርፆ ሰጠ?
ጴንጠው -- ለሙሴ የሰጠው ታቦት ወድቆ ተሰብሯል።
ኦርቶዶክሱ -- አው እውነት ነው ነገር ግን እግዚአብሔር እንደገና
ሙሴ
እንድቀርፅ አዞታል። ኦ.ዘፀ 34፥1 ።
ጴንጠው -- እሽ ይሁንና ሙሴ የቀረፀው ሁለት ብቻ ነው ይህ
ሁሉ ከየት
መጣ??
ኦርቶዶክሱ -- ከሙሴ ከጥሎ ያሉት ቅዱሳን አባቶች እንድቀርፁ
ስልጣን
ተሰጣቸው ኦ.ዘፀ 31፥1-6 እንዲሁም ባሰልኤም ታቦትን ቀርጿል
ኤ.ዘፀ
37፥1።
ጴንጠው -- እሽ ይሁንና ለምን በቅዱሳን ስም ይቀረፃል?
ኦርቶዶክሱ -- የመታሰብያ ስም እስከተሰጣቸው ድረስ ት.ኢሳ
56፥4
ይቀረፅላቸዋል ነገር ግን በታቦቱ ላይ የምከብረው የጌታችን
ሥጋውና ደሙ
ነው።
ጴንጠው -- እኔ አሁንም ያልገባኝ ታድያ ለምን በየሀገሩ
በየአህጉሩ ታቦት
በዛ ከቅዱሳኑ ቁጥርምኮ ይበዛል?
ኦርቶዶክሱ -- መልስ ሳልሰጥህ በፊት ጥያቀ አለኝ? መጽሐፍ
ቅዱስ
ስታተም 1 ነበር አይደል? ታድያ አሁን በእያንዳንዳችን እጅ ላይ
የምገኘው
ከየት መቶ ነው?
ጴንጠው -- ያው ተባዝተው ስለታተመ ነዋ
ኦርቶዶክሱ -- ታቦቱም እንድሁ ለአገልግሎት እንድመች
በየስፍራው አለ!
ይህ ለምን ይሆናል ካልከኝ ት.ሚልክ 1፥11 ተመልከት።
ደግሞም በአድስ
ኪዳን እግዚአብሔር ለሰዎች ቅርብ አምላክ ነውና ነው ት.ኤር
23፥23።
ጴንጠው -- ለምን በታቦቱ ላይ የቅዱሳን ስም ይፃፋል?
ኦርቶዶክሱ -- በታቦቱ ላይ ብቻ አይደለም በሰማይ ቤትም
ተፅፎላቸዋል
ሉቃስ 10፥20።
ጴንጠው -- ታቦት በአድስ ኪዳንኮ ተሽሯል አያስፈልግም
ኦርቶዶክሱ -- ማነው የሻረው? ጌታ በማቴ 5፥17 ላይ ምን ነበር
ያለው?
ህግንና ነብያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈፅማቸው ነው እንጅ
አላለም
ወይ?
ጴንጠው - እናንተ ኦርቶዶክሶች ብቻ አከረራችሁት እንጅ ታቦት
የምባል
ነገር መኖር የለበትም።
ኦርቶዶክሱ - አይደለም በምድር ላይ አይደለም በኦርቶዶክሶች
መቅደስ
ውስጥ በሰማይምኮ አለ ታቦት። ነገ እዛ ስትሄድም ይጠብቅሃል
ራእይ
11፥19 ይህንንም ስያመለክት ነው ቅዱስ ጳውሎስ ሀገራችን
በሰማይ ነው
እያለ 2ኛ ቆሮ 5፥1-5 የተናገረው።
ጴንጠው -- እሽ ሁሉም እንዳለ ሆኖ ለምንድ ነው እሽ ታቦት
ስሰረቅ ዝም
የምለው ሃይል የለውምኮ ሌባ ሰረቀው ምናምን ስባል
እሰማለው
የሰረቀው ሌባም ስሸጠው ታቦቱ ታምራትን እንኳን አያደርግም።
ኦርቶዶክሱ -- ምርጥ ጥያቀ ጠየከኝ ገና አሁን!! ለመሆኑ ታቦት
ይበልጣል ወይስ ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጣል ?? ታቦት ማለት
የቃሉ
ማደርያ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ደሞ እራሱ የታቦቱ ባለቤት ነው።
እስት
ንገረኝ?
ጴንጠው -- መብለጡንማ ኢየሱስ ነው የምበልጠው
ኦርቶዶክሱ -- ታድያ ይሁዳ በ30 ብር አሳልፎ ስሸጠው ለምን
ኢየሱስ
ዝም አለ?? ሀይል ስለለለው? አቅም ስለለለው? ወይስ
ይሁዳንም
አይሁዶችንም በአንዴ ማጥፋት ስለማይችል ነውን??
ጴንጠው -- ዝምምምምምም
ኦርቶዶክሱ -- አየህ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁዳ አሳልፎ ስሸጠው
ዝም
ያለው በኃላ እነርሱንና ጠላት ዲያብሎስንም ድል ልነሳው
ስለፈለገና
አዳምንም ነፃ ልያወጣው ስለወደደ ነው እራሱን አሳልፎ
የሰጠው። ዛሬ
ታቦታትም ስሰረቁ ዝም የምሉት በኃላ ላይ የእግዚአብሔርን
ኃይልና
የታቦትን ክብር ለማሳየት ብቻ ነው ለዚህ ደሞ 1ኛ ሳሙ 4,, 5,,
6
እነዚህን 3ምዕራፎችን ካየህ ይበቃሃል።
ጴንጠው---በኦርት ጊዜኮ ኦዛ ታቦቱን ስነካ ተቀስፏል?
ኦርቶዶክሱ---አው ተቀስፏል። በኦርት ጊዜ ሰው ሁሉ በመርገም
ነውና
ያለው እግዚአብሔር ለቁጣው አይዘገይም። በአድስ ኪዳን ግን
ዘመኑም
"አመተ ምህረት" ይባላልና የምህረት ዘመን ነው አምላክ ቶሎ
አይፈርድም
ምሳሌ እንድሆንልህ ማቴ 13፥24-30 .....ማቴ
5፥45...አንብብ....
ጴንጠው---ስግደት ለምን አስፈለገ ከእኔ በቀር ለሌላ አምላክ
አትስገድ
አላለም ወይ?
ኦርቶዶክሱ---እሽ መልካም ኢያሱ ማለት በመ.ኢያሱ 24፥15
ላይ "እኔና
ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ"
ያለ ቅዱስ
ነብይ ነው አይደል? ታድያ ለምን በመ.ኢያሱ 7፥6 ላይ ለታቦቱ
ሰገደ???????? ስለዚህ እኛ ደሞ ዕብ 13፥7 ላይ ቅዱስ
ጳውሎስ
እንዳለን ሁሉ ይህንኑ እንፈፅማለን።
ጴንጠው----እኛ የምሸከመንን እንጅ የምንሸከመውን
አናመልክም
እናንተኮ ታቦትን ትሸከሙታላችሁ?
ኦርቶዶክሱ---አሁንም መልሼ ልጠይቅህ ከታቦት ኢየሱስ
ይበልጣል
ተባብለናል አይደል? ታቦት ዙፋኑ ነው እርሱ ደሞ የዙፋኑ ባለቤት
ነው።
ጴንጠው----አዎ
ኦርቶዶክሱ---እሽ የሰው ልጅ ይበልጣል ወይስ አህያ?
ጴንጠው---የሰው ልጅ ነዋ
ኦርቶዶክሱ---ታድያ የሰው ልጅ ታቦትን ከተሸከመ ምን
ይገርምሃል?
አህያ የታቦቱን ባሌበት ሰማይና ምድርን በቃሉ ያፀናቸውን
አምላክ
ጌታችንን በጀርባዋ አልተሸከመችውምን?????
ጴንጠው----- ለካ እሱም አለ!!!.........
ኦርቶዶክሱ----ገና ብዙ አለ!!!! እርሱን የተሸከመችው አህያ
በብቃቷ
በጉልበቷ ሳይሆን በእርሱ ፈቃድና ሃይል ነው። ካህናትም ታቦቱን
የምሸከሙት በራሳቸው ጥበብና በስልጣናቸው አይደለም፤
የሾማቸው
አምላክ ፈቅዶላቸው በቸርነቱ እንደፈቃዱ ነው እንጅ።
ሃይማኖቴ ተዋህዶ ማለት ይህችው ናት። ኦርቶዶክስ መልስ
አላት!!
ደግሜ እላለሁ ኦርቶዶክስ መልስ አላት!! እውነተኛይቱና
ቀጥተኛዋ
ሃይማኖቴ ተዋህዶ ናት!!!
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ማንም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ
(በቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ)

ከመጀመርያ ጀምሮ መልካም ነገርን መምረጥ ክፉ አይደለም፤ በመልካምነት አለመቀጠል ግን ብዙ ወቀሳን ያመጣል፡፡ የብዙ ሰዎች ክፉ መሆን በዚሁ የሚመደብ ነው፤ ብዙዎች ሕይወታቸውን በመልካም ጀምረው በኋላ ግን በክፋት መርዝ ተጠምቀው ሲሰክሩ ተመልክቻለሁና፡፡
እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ፡፡ ምንም እንኳን አሁን ወደ ክፋት ጥልቅ ወርዳችሁ ቢሆንም “ከዚሁ ተመልሰን መነሣት አይቻለንም፤ መለወጥም አይሆንልንም” በማለት ተስፋ የምትቈርጡ አትሁኑ፡፡እናንተ ስትፈቅዱ እግዚአብሔርም ሲረዳችሁ ከክፋት ዐዘቅት መውጣት በእጅጉ ቀላል ነውና፡፡ ከሁሉም በላይ አመንዝራ ተብላ በከተማው ዘንድ ትታወቅ የነበረችውን ሴት በመልካምነቷ እንዴት እንደምትወደስ አልሰማችሁምን? እየነገርኳችሁ ያለሁት በዮሐንስ ወንጌል ላይ ስለተጠቀሰችው ሴት አይደለም፡፡ በእኛ ዘመን ስላለችውና ፍኒሳ ከተባለችው ጋጠ ወጥ ከተማ ስለተገኘችው ሴት እንጂ፡፡ ይህች ሴት አስቀድማ በመካከላችን በአመንዝራነቷ ትታወቅ ነበር፡፡
በክብር ቦታ ሁሉ የመጀመርያን ስፍራ የምትይዝ ሴት ነበረች፤ ስሟ በሀገሩ ሁሉ የገነነ ነበር፤ በእኛ ከተማ ብቻ ሳይሆን በሲልስያ እና በቀጰዶቅያም ጭምር እንጂ፡፡ ይህች ሴት ብዙ ከተሞችን አፍርሳለች፤ የብዙ ወላጅ አልባ ሕፃናትን ንብረት በልታለች፡፡ ብዙዎችም “መተተኛ ናት” ይሏታል፤ ውበቷን ብቻ ሳይሆን መድኃኒትም ጭምር ትጠቀም ነበርና፡፡ ከዚሁ የተነሣ በአንዱ ቀን የንግሥቲቱን ልጅ እስከ ማማለል ደርሳለች፡፡ ጭካኔዋ የክፉ ክፉ ነበር፡፡
ከዕለታት በአንዲቱ ቀን ግን ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ሆኖም ግን በዓይኔ ፍጹም ተለውጣ ራሷን በእግዚአብሔር የጸጋው ዙፋን ፊት ድፍት አድርጋ ስታለቅስ አየኋት፡፡ አሁን የቀድሞ ክፉ ሥራዎቿን ሁሉ እርግፍ አድርጋ ትታለች፤ በእርሷ ላይ ከነበሩት
የአጋንንት ጭፍራ ተፋትታ አሁን የክርስቶስ ሙሽሪት ሆናለች፡፡
በእውነት ከእርሷ የሚከፋ ሰው በዐይኔ አላየሁም፡፡ በኋላ ግን ራሷን ከእንደዚህ ዓይነቱ ክፉ ሥራ ከለከለች፡፡ ከዚህ በፊት ስትለብሳቸው የነበሩት የምንዝር ጌጦች ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ አሁን ግን እነዚህ ሁሉ በእርሷ ዘንድ ቦታ የላቸውም፡፡ እነዚህን ሁሉ አወላልቃ ጥላ ለእግዚአብሔር በሚገባ የማቅ ልብስ ለብሳ ራሷን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር አድርጋለች፡፡ ይህችን ሴት ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ለመመለስ የሀገሪቱ መኳንንት ከዙፋናቸው ወርደው ለምነዋት ነበር፤ ወታደሮች ትጥቃቸውን ታጥቀው በመምጣት አስፈራርተው ሊወስዷት ሞክረው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ሊመልሷት አልተቻላቸውም፤ ከተቀበሏት ደናግላን በዓት ሊያስወጧት አልተቻላቸውም፡፡ ይህች ሴት ከዚያ አስነዋሪ ሕይወቷ ተመልሳ ለቅዱስ ቁርባን በቅታለች፤ ለእግዚአብሔር ጸጋ የተገባ ሆና ተገኝታለች፤ ኃጢአቷን ሁሉ በጸጋው አጥባለች፤ ከተጠመቀች በኋላ ራሷን መግዛት ችላለች፡፡ ይህች ሴት የቀድሞ ሕይወቷን፣ ገላዋን ለብዙ ወዳጆቿ ያሳየችበትን ሕይወት “የእስር ቤት ሕይወት” ብላ ትጠራዋለች፡፡ በእውነት “ኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ” የሚለው የከበረው የጌታ ቃል በእርሷ ሲፈጸም አየነው፤ መለወጥ ከፈለግን እኛን ማሰናከል የሚቻለው ኃይል እንደሌለ አወቅን ተረዳን፡፡
እንግዲያስ ተወዳጆች ሆይ! ተስፋ በመቁረጥ በኃጢአት ዐዘቅት ሰምጠን የምንቀር አንሁን፡፡ ከእኛ መካከል በጽድቅ በረሀነት የሚኖር ማንም አይገኝ፡፡ ፊተኛ ነኝ የሚልም ከቶ አይኑር፤ ብዙ አመንዝሮች እርሱን አልፈዉት ሊሄዱ ይችላሉና፡፡ ማንምም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ፤ ከልቡ ከተጸጸተና ከተመለሰ ፊተኛ መሆን ይቻለዋልና፡፡
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- “ይህም ሁሉ ካደረገች በኋላ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፡፡ ነገር ግን አልተመለሰችም፡፡ አታላይ እኅትዋም ይሁዳ አየች” /ኤር.3፡7/፡፡
ወደ እግዚአብሔር ስንመለስ የቀድሞ ኃጢአታችንን
አያስበውም፤ እግዚአብሔር እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለምና፡፡ በእውነት እርሱ በቀድሞ ኃጢአታችን የሚወቅሰን አይደለም፡፡ እርሱ እንደ ሰው አይደለምና፡- “እስከ አሁኑ ሰዓት ወዴት ነበርክ?” የሚለን አይደለም፡፡ ብቻ እኛ እንመለስ እንጂ እርሱ እንዲህ ያለ አምላክ አይደለም፡፡
ይህን እንደናደርግ ሰውን በመውደድ ሰው የሆነው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
"ባሎች ለሚስቶቻቸው ሊያሳዩአቸው የሚገባ ፍቅር"
(በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሚስትህ ለአንተ ትገዛልህ ዘንድ ትሻለህን? ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት አንተም እንዲሁ ለሚስትህ አድርግላት፡፡ ሕይወትህን ስለ ርሷ አሳልፈህ መስጠት ካለብህ ስለርሷ ሕይወትህን አሳልፈህ ስጥ፤ መከራም መቀበል ካለብህ መከራን ለመቀበል አትሰቀቅ፡፡

አንተ ይህን ብትፈጽመው ስንኳ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ካደረገላት ጋር ሲነጻጸር የሚወዳደር አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንተ ይህን ያደረግኸው ከአንተ ጋር ፈጽማ ለተዛመደችህ ለአንዲት ሴት ነው፡፡ “እርሱ ግን ከእርሱ ለተመለሰችውና ለጠላቸው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡” ርሱ ከርሱ የተመለሰችውንና የጠላችውን እንዲሁም ያቃለለችውን ገንዘቡ ሲያደርጋት በማስፈራራት፣ በማስገደድ ወይም ይህን በመሳሰሉ ነገሮች አልነበረም፤ ነገር ግን ኀዘን ባልተቀላቀለበት ፍጹም በሆነ ፍቅር በመሆን ነበር፡፡ አንተም ለሚስትህ እንዲሁ አድርግላት አዎን! ምናልባት ሚስትህ አንተን ልታመናጭቅህ፣ ልትንቅህ፣ ልታፌዝብህም ትችላለች፤ ቢሆንም ግን አንተ ለርሷ ካለህ አርቆ አሳቢነት ንጹሕ ፍቅርና ኀዘኔታ የተነሣ ልትታገሣት ይገባሃል፡፡

ከሰው ሁሉ ጋር ተስማምቶ ለመኖርም ከእነዚህ የተሻሉ ነገሮች ፈጽሞ አናገኝም፡፡ በተለይም ለባልና ለሚስት፡፡ አንድ ሰው አገልጋይ ባሪያውን በማስፈራራት ለመግዛት ቢሞክር ለጥቂት ጊዜአት ሊገዛለት ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ ባሪያ እንዲህ ዓይነት አገዛዝ ስለማይመቸው ከእርሱ ፈጥኖ ይሸሻል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው የሕይወቱን አጋር፣ የልጆቹን እናት፣ የደስታው ሁሉ ምንጭ የሆነችውን ሚስቱን በፍቅርና በፍጹም አክብሮት እንጂ ልክ እንደ ባሪያ በፍርሃት ሰንሰለት በማሰር ወይም በማስጨነቅ ርሷን ሊገዛት መሞከር አይገባውም፤ ሚስት በባልዋ ምክንያት የምትሸበር ከሆነ አንድነታቸው ምን ዓይነት አንድነት ነው? ከባሪያ ጋር እንደ መኖር ከሚስት ጋር መቀመጥ ለባል የሚፈጥርለት ምን ዓይነት ደስታ ነው? አዎን ይልቁኑ አንተ ስለ ርሷ ስትል ብዙ መከራዎችን መቀበል ሲገባህ በተቃራኒው በቁጣ ርሷን በማስጨነቅና በማሸበር ታስፈራራታለህን? ክርስቶስ እንዲህ አላደረገም፡፡

“በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ አንዲቀድሳት ስለ ርሷ (ስለ ቤተ ክርስቲያን) ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ቤተ ክርስቲያን (እኛ) አስቀድማ ንጽሕት አልነበረችም፤ ጉድፍ ነበረባት፤ መልከ ጥፉም ነበረች፡፡ ስለዚህም ለእርሱ የተገባች አልነበረችም፡፡ አንተ እንደ ቤተ ክርስቲያን የሆነችውን ሴት ሚስትህ ትሆን ዘንድ አትመርጥም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ የተለየችውን ያህል ከአንተ ፈጽማ የማትስማማውን ሴት ሚስትህ ትሆን ዘንድ ወደ አንተ አታቀርባትም፡፡ እርሱ ግን እጅግ መልከ ጥፉ ብትሆንም አልጠላትም፣ አልተጸየፋትም፣ ስለ መልከ ጥፉነቷ የተጻፈውን መስማት ትፈልጋለህን? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ርሷ ምን እንደሚል ስማ “ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁ” (ኤፌ.፭፡፰) አላት፤ የገጽታዋን መጥቆር ትመለከታለህን? ከጨለማስ የበረታ ጥቁረት ምን አለ? የአመሏን መክፋት ደግሞ ስማ “በክፋትና በምቀኝነት” ይልና “የምንኖር” ይላል፤ ስለ ነውሮቿ ደግሞ “የማንታዘዝና የምንስት ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ” ይላታል (ቲቶ.፫፡፫)፡፡

ነገር ግን ለርሷ ስለተደረገላት በጎነት ምን ማለት ይቻለኛል? ርሷ ስንፍናን የተሞላችና ክፉ አንደበት የነበራት እንዲሁም በነውሮቿ ሁሉ ያደፈች ብትሆንም እነዚህ ሁሉ ጠባዮቿ ከርሷ አላራቀውም፡፡ ነገር ግን ልክ የደስ ደስ እንዳላት ልጃገረድ በአፍቀሪም ዘንድ ለምትወደድ ውብ ሴት እንደሚደረገው ርሱ ስለ ርሷ ራሱን አሳልፎ የሰጠ አይደለምን? ይህንንም በማድነቅ ቅዱስ ጳውሎስ “ስለጽድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት ስንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኛል” ይልና “ነገር ግን ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና”(ሮሜ.፭፡፯-፰) ብሎአል፡፡ በዚህ መልክ ርሷ ለርሱ ትሆን ዘንድ አቀረባት፤ በመንፈሳዊ ውበትም አስጌጣት፤ ንጽሕት አደረጋት፤ ስለ ርሷም ራሱን አሳልፎ ለመስጠት ስንኳ የጨከነ ሆነ፡፡

(የትዳር አንድምታ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ ገጽ 17-19 - በመምህር ሽመልስ መርጊያ)
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ
ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ ለማግኘት ሲፈልጉ ቻናላችንን ይጎብኙ::

ለመቀላቀል ከስር ሰማያዊውን ይጫኑ

JOIN OUR CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
Forward this to your friends and family
" እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።"
(የማቴዎስ ወንጌል 6:2)
To join our channel click the one in blue
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
የተወደደ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-

እግዚአብሔርን የምትወዱት፥ ይልቁንም እግዚአብሔር አብልጦ የሚወዳችሁ ሆይ!

ሕፃናት የእናታቸውን ጡት ለመጥባት ምን ያህል እንደሚጓጉ አስተውላችኋልን? እኛም ወደ ቅዱሱ ማዕድ መቅረብ ያለብን፣ ከመንፈሳዊው ጽዋ ጡትም ለመጠጣት መጓጓት ያለብን እንደዚህ ነው፡፡

ሕፃናቱ የእናታቸውን ጡት ሲያዩ እንዴት ደስ እንደሚሰኙም ተመልክታችኋል! እኛም የመንፈስ ቅዱስን ፍቅር ስንመለከት ደስ ሊለን የሚገባው እንደዚህ ነው፡፡

ሕፃናቱ የእናታቸው ጡት ሲከለከሉ ምርር ብለው እንደሚያለቅሱ ኹሉ፥ እኛም ከዚህ ማዕድ (ከቅዱስ ቁርባን) ስንርቅ ምርር ብለን ልናለቅስ ይገባናል፡፡
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ጊዜው ጋብቻ የሚበዛበት በመሆኑ እንማርበት ዘንድ፡-

ትዳር ምንድን ነው?

ትዕይንት (ቲያትር) ነውን? አይደለም፡፡ ምንም እንኳ እናንተ ለትዳርና ለምሳሌው አክብሮት ባይኖራችሁም ትዳር ግን ግሩም ምሥጢርና የታላቅ መንፈሳዊ ምሥጢር ምሳሌ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ሲያስተምር “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው” ይልና ጨምሮ “እኔ ግን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ” ይላል (ኤፌ.5፥23)፡፡

ጋብቻ የቤተ ክርስቲያንና የክርስቶስ ምሳሌ ነው። እንዲህ በከበረ ምሥጢር ላይ ዳንኪረኞችን በመጋበዝ ዝሙትን ታስተዋውቁበታላችሁን? ነገር ግን ከእናንተ መኻከል አንዱ እኔን፡- "እንዲህ ስትል ደናግል ወይም ያገቡት አይጨፍሩ እያልክ ነው? እንግዲያ እነርሱ በዚህ ሰርግ ላይ ካልጨፈሩ ማን ሊጨፍር ነው?" ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ፡፡ ማንም አይጨፍር ነው መልሴ፡፡

በአሕዛብ ዘንድ ይህን በመሰሉ ሥርዓቶቻቸው ዳንኪረኞች ዳንኪራቸውን ያቀርባሉ፡፡ በእኛ ግን ማንኛውም ምሥጢራት ሲከናወኑ በጸጥታ፣ በትሕትናና በጥሩ ሥነ ምግባር እንዲሁም በመልካም ሥርዐት ነው፡፡

ይህ የጋብቻ ሥርዐት አመንዝሮች ከተጠሩበት እግዚብሔርን የማይፈሩ ከተጋበዙበት መንፈሳዊ ጋብቻ ብለን ልንጠራው የምንችለው እንዴት ብለን ነው? እንዲህ ከሆነ ሁለቱ አካላት አንድ ሆነዋል ልንል የምንችለው እንዴት ተብሎ ነው?

ክርስቶስ በተገኘበት ጋብቻ ግን ዳንኪራ የለም፤ የእምቢልታም ድምፅ አይሰማበትም፡፡ ነገር ግን ግሩም የሆነ ጸጥታ የሰፈነበት፣ በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዐት የሚከናወን ነው፡፡ በዚህ ሥርዐት አንድ አካል ወደ መኾን ሲመጡ አንድነታቸው ሕይወት አልባ ፍጥረታት እንደሚኖራቸው አንድነት ወይም በዚህ ምድር የሚታየውን ዓይነት አንድነት አይደለም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ኾነው አንድ ይኾናሉ፡፡ ይህ ታላቅ የኾነ ምሥጢር በሚከናወንበት ሥፍራ እንደ አራዊት ታላቅ ሁካታና ረብሻ እንዲሁም ነፍስን የሚያሳድፉ ታላቅ የኾነ በደል ይፈጸማልን?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ facebook page)

To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ገላትያ ሰዎች አጭር ዳሰሳ!

ይህች ገላትያ የተባለች ሀገር በታናሿ እስያ አጋርዮስና አሊያስ በተባሉ ሁለት ወንዞች መካከል የምትገኝ አውራጃ ስትሆን ዛሬ የቱርክ መናገሻ ከተማ ናት፡፡ይህች የገላትያ ሰዎች መልእክት የተጻፈላቸው በ48 ዓ.ም ሲሆን የተላከላቸውም በቲቶ እጅ ነው፡፡መልክቲቱም ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ የመጀመሪያዋ እንደሆነች ይነገራል፡፡ክርስትያኖች በእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ያገኘነውን ጸጋና ክብር ከኃጢአት ባርነት ነጻ እንዴት እንደወጣን የምትናገር የምታስረዳ በመሆኗ ‹‹የነጻነት መልእክት›› በመባል ትጠራለች፡፡
ይህን መልእክት የጻፈበት ምክንያት
የአይሁድ መምህራን የሐሰት ትምህርት ወጋቸውን ሥርዓታቸውን የገላትያ ሰዎች እንዳይቀበሉ የተማሩትን የሐዋርያት ትምህርት እንዲጠብቁ እንዲጸኑ
የአይሁድ መምህራን እንደ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን አላየም ከቅዱሳን ሐዋርያትም እኩል አይቆጠርም ይሉት ስለነበር ይህንን የእርሱን ሐዋርያነትና ሥልጣኑን ያውቁ ዘንድ
ከሐዋርያት እንጂ ከጌታ ስላልተማረ ክብሩ ያነሰ ሰው እያሉ አይሁድ ካህናት የገላትያን ሰዎች ያወናብዱ ያስጨንቁ ስለነበር ይህን ለማስረዳት
መገረዝ ጽድቅን ያስገኛል ጳውሎስ ራሱ ተገርዟል እናንተን ግን ጽድቅ እንዳታገኙ ‹‹መገረዝ አይጠቅምም››ይለችኋል እያሉ በዚህ ምክንያት ከእውነተኛዋ ሃይማኖት ሕግና ሥርዓት ያስወጧቸው ስለነበር ይህን ለማስረዳት ሐዋርያት ከአይሁድ ተፉቅረው ሕገ ኦሪትን ጠብቀው ሥርዓተ አይሁድን አክብረው በኢየሩሳሌም እየኖሩ እርሱ ግን እናንተን አላዋቂ አድርጎ የሐሰት ትምህርትን ያስተምራችኋል በማለት የሚናገሩትን ለማስተማር ጽፎላቸዋል፡፡
ዲያቆን ሸዋፈራው አለነ
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
የምጽዋት ብዛት የሚመዘነው በሚሰ’ጠው ገንዘብ ቁጥር ሳይኾን ስጦታውን በሚሰጥ የልብ ስፋት ነው፡፡ አንዲት ድኻ ሴት ያላትን ጥቂት እንጀራ ምንም ከሌላት ከሌላ ሴት ጋር ተካፍላ የምትበላ ከኾነ፥ ወርቅን በሙዳዬ ምጽዋት ከሚጨምር ባለጸጋ ሰው እጅግ ትበልጣለች፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳን ይህ እውነት እንደ ኾነ ብዙ ክርስቲያኖች ቢያውቁም፥ ምስጋና የሚሰጡት ወርቅ ለሰጠው ነው፡፡
አንድ ባለጸጋ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ቢሰጥ እጅግ ያመሰግኑታል፤ ካለው የሀብት ብዛት የተነሣ ያንን በመስጠቱ ምንም ባይጎድልበትም እንኳ፥ በሰዎች ዘንድ እጅግ ቸር እንደ ኾነ ተደርጎ ይንቆለጳጰሳል፡፡ ድኻው ጥቂት ገንዘብ ቢሰጥ ግን ሰዎች ስለ እርሱ ምንም ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምናልባት ያቺ የሰጣት ገንዘብ’ኮ በኋላ እርስዋን በማጣቱ ምክንያት ተርቦ እንዲያድር ልታደርገው የምትችል ትኾን ይኾናል፤ ነገር ግን ይህን በማድረጉ የሚያመሰግነው አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም ሳይጎድልበት የሰጠውን ባለጸጋውን አመስግኖ ያለውን ኹሉ የሰጠውን ድኻ ሳያመሰግኑ ከሚቀሩ ከእነ ጭራሹ ምስጋና ባይኖር ይሻል ነበር፡፡
ስለዚህ እውነተኛ ምጽዋት የሚባለው የባለጸጋውም ይኹን የድኻው በአግባቡና በሥርዓቱ ልናውቀው ይገባናል፡፡ ማመስገን የሚገባንም ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የምስጋናችን ስጦታም ሰዎች ከልባቸው ከሚሰጡት ገንዘብ ብዛት አንጻር ሊኾን ይገባል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
"የሚወደውን ሰው እያየ የሚጠጣ ሰው ከወይኑ ጋር ፍቅርን ይጠጣል ፣ ጠላቱን እያየ የሚጠጣ ግን ከመጠጡ ጋር ቁጣን ይጎነጫል። እኛ ግን ወይናችንን ባልንጀራን ከመውደድ ጋር እንቀላቅል። ወይኑ በደም ሥራችን ሲወርድ ፍቅር በኅሊናችን ይፍሰስ። ምግቡ ወደ ሆዳችን ሲወርድ ጸሎት በኅሊናችን ይቆይ"

በልተን ስንጨርስም "ስብሐት" ብለን እናመስግን። እስራኤል በልተው ባለማመስገናቸው እንደተቀሠፉ አስታውሱ (ዘኁ 21:6) ፈጣሪ ሥጋን ሠጣቸው ሳያመሰግኑ ሲበሉ ሳያኝኩት የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ። ምግቡም በአፍንጫቸው ወጣ። (ዘኁ 11:20) ቅዱስ ኤፍሬም በአፍንጫቸው ወጣ የሚለውን ሲያብራራ "ከአፍ በላይ ያለው አፍንጫ አፍን ባለማመስገኑ ኮነነው። ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ ምግቡ በአፍንጫ በኩል ወጣ" ይላል።

መቼም በልቶ ስለማመስገን የሚያብራራውን ይህን ጽሑፍ ሲያነብ "አሁን ስንት ሚልዮን ሕዝብ እየተራበ በልቶ ስለማመስገን ለመጻፍ ጊዜው ነውን? ይሄ ሕዝብ ምን በልቶ ነው የሚያመሰግነው?" የሚል ሰው አይጠፋም። (ጽሑፉንም ላይጨርሰው ይችላል)

ቅዱስ ኤፍሬም ግን ለማመስገን መጥገብ ብቻ ምክንያት አይደለም ባይ ነው። የሉቃስ ወንጌሉን ታሪክ በመጥቀስ "ባለጠጋው ነዌ ጠግቦ አላመሰገነም ፣ ደኃው አልዓዛር ግን ተርቦ ያመሰግን ነበር" ይላል።

እውነቱን ነው! ሳይበላ ያመሰገነ ሰው በሰማይ ገበታ በአብርሃም እቅፍ ይስተናገዳል። ከመንግሥተ ሰማያት ራት ይጋበዛል። ከአብርሃም ከይስሐቅ ከያዕቆብ ጋር ይቀመጣል። የሕይወት እንጀራን ከቶ ከማያስጠማው የሕይወት ውኃ ጋር ይጠጣል። ለዘላለም አይራብም አይጠማም።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
henoktsehafi@gmail.com
ሰኔ 2 2008 ዓ ም
ሮተርዳም ፣ ኔዘርላንድስ የተጻፈ
ቤተ ክርስቲያን Vs ሆስፒታል

(በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ልጆቼ! ተጠራርታችሁ ወደ አባታችሁ ቤት ለመምጣት ያደረጋችሁትን ቅንአት ተመልክቼ ደስ ተሰኝቼባችኋለሁ፡፡ እኔም ይህን ቅንአታችሁን አይቼ ስለ ነፍሳችሁ ጤና ይበልጥ እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቀዶ ጥገና የሚደረግባት ሐኪም ቤት ናት፡፡ የሥጋ ቀዶ ጥገና ግን አይደለም፤ የነፍስ ቀዶ ጥገና ነው እንጂ፡፡ የምናክመው የሥጋን ቁስል አይደለም፤ መንፈሳዊ ቁስልን እንጂ፡፡ መድኃኒቱም ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ መድኃኒት በምድር ላይ ከሚበቅሉት ዕፅዋት የተቀመመ አይደለም፤ ከሰማያት ከሚመጣው ቃል እንጂ፡፡ ይህን መድኃኒት በቁስል ላይ ለመጨመር ሐኪሞች አያስፈልጉም፤ የሰባክያነ ወንጌል አንደበት እንጂ፡፡ ቀዶ ጥገናውን ለማከናወን ብዙ ሰዓታትን አይፈጅም፡፡ ቀዶ ጥገናው ላይሳካ ይችላል ተብሎ የሚጠረጠር አይደለም፡፡ ከጊዜ በኋላ ወይም በሌላ ሕመም ምክንያት የተደረገው ቀዶ ጥገና ሊከሽፍ ይችላል ተብሎም አይገመትም፡፡ ሐኪሞች የሚሰጡን መድኃኒት እንዲህ ዓይነት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ሐኪሞች የሚሰጡን መድኃኒተ ሥጋ ለጊዜው ብርቱ ነው፤ ሰውነታችን እያረጀ እንደሚሔደው ኹሉ መድኃኒቱም በጊዜ ሒደት ብርታቱን እያጣ ይሔዳል፡፡ ሌላ ደዌ ዘሥጋ ሲገጥመንም መቋቋም የሚችል አይደለም፡፡ ምክንያቱም መድኃኒቱን የቀመሙት ሰዎች ስለኾኑ፡፡ ከእግዚአብሔር የሚሰጠን መድኃኒት ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ምንም ያህል ጊዜ ቢቆይም አይበላሽም፤ ጊዜው አያልፍበትም፤ ኃይሉም ብርታቱም ያው ነው አይቀንስም፡፡

ሙሴ የተቀበለው ቃለ እግዚአብሔር በጊዜው የነበሩትን ሰዎች ፈውሷቸዋል፤ አሁንም ያ ቃል ይፈውሳል፡፡ የመፈወስ ኃይሉ ብርታቱ እስከ አሁን ድረስ አላጣም፤ ሌላ ምንም ዓይነት በሽታም አላሸነፈውም፡፡ ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብር አይበቃውም፤ ቅን ልቡና ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ በዚህ መድኃኒት ባለጸጋውም ድኻውም እኩል ይታከማሉ፡፡ ወደ ምድራዊው ሆስፒታል ሲኬድ ባለጸጋው ብር ስላለው ያሻውን ሕክምና አግኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ድኻው ግን ብር ስለሌለው መድኃኒቱንም መግዛት ስለማይችል ሳይታከም ከነሕመሙ ወደ ቤቱ ይመለሳል፡፡ ይህ ከቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው መድኃኒት ግን በብር የሚገዛ አይደለም፡፡ ይህን መድኃኒት ለማግኘት የሚያስፈልገውም ብር ሳይኾን እምነትና ምግባር ነው፡፡ እምነትና ምግባር የከፈለ ሰው ይህን መድኃኒት ማግኘት ይቻሏል፡፡ እነዚህን የከፈለ ጤናውን አግኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፡፡ በመኾኑም ድኻውም ባለጸጋውም እኩል ታክመውበት ይሔዳሉ፡፡ እንደዉም ከባለጸጋው ይልቅ ድኻው በመድኃኒቱ ይበልጥ ተጠቅሞ ይሔዳል፡፡ ለዚህስ ምክንያቱ ምንድነው? ምክንያቱም ባለጸጋው ብር ስላለው በብዙ ሐሳብ የተያዘ ነው፡፡ ሀብታም ነኝ ብሎ ስለሚያስብ ትዕቢተኛ ነው፡፡ ሕይወቱን የሚመራው በቸልተኝነት ነው፡፡ በስንፍና ስለሚያዝ መድኃኒት የኾነውን ቃሉን ለማድመጥ ስልቹ ነው፡፡ ድኻው ግን በቅንጦትና በስንፍና ኑሮ ስለማይኖር፣ ጊዜውን በእንተ ፈንቶ ነገሮች ስለማያሳልፍ መድኃኒተ ነፍሱን ለማግኘት ንቁ ነው፡፡ ቃሉን ለማድመጥ ፈጣን ነው፡፡ ቸልተኝነት አይጠጋውም፡፡ የተባለውን ለማድመጥ ልቡናው ዘወትር ዝግጁ ነው፡፡ የሚከፍለው ክፍያ ብዙ ነው ማለት ነው፤ የሚያገኘውም መድኃኒት እንደዚያ ብዙ ነው፡፡

ይህን ኹሉ ዘርዝሬ መናገሬ ግን ባለጸጋውን ኹሉ በደፈናው መኰነኔ አይደለም፡፡ ድኻውንም ኹሉ እንደሁ ማመስገኔ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሀብት በራሱ መጥፎ አይደለም፤ መጥፎ የሚያደርገው የእኛ አጠቃቀም ነው፡፡ ድኽነቱም በራሱ በጎ አይደለም፤ በጎ የሚያደርገው የኛ አጠቃቀም ነው፡፡ ባለጸጋው ነዌ ወደ ሲዖል የተወረወረው ሀብታም ስለነበረ አይደለም፤ ጨካኝና ሰብአዊነት የማይሰማው ክፉ ስለነበረ ነው እንጂ፡፡ አልዓዛርም በአብርሃም ዕቅፍ የተቀመተው እንዲሁ ድኻ ስለነበረ አይደለም፤ ድኻም ቢኾን አመስጋኝ ስለነበረ እንጂ፡፡

ስለዚህ ባለጸጎችን እንዲሁ በደፈናው አንውቀሳቸው፤ ድኽነትንም እንዲሁ አንጥላው፡፡ መውቀስ ካለብን እነዚህን ኹለቱንም በአግባቡ የማይጠቀሙባቸው ሰዎችን ነው፡፡ አስቀድሜ እንደተናገርኩት ድኽነት ወይም ሀብት በራሳቸው መጥፎ ወይም በጎ አይደሉምና፡፡ ስለዚህ በቤተክርስቲያን የሚሰጠው መድኃኒት ድኻውም ባለጸጋውም እኩል ታክመውበት ይሔዳሉ፡፡ ከባለጸጋው ይበልጥ ደግሞ ድኻው፡፡ የቃለ እግዚአብሔር ጥቅሙ መድኃኒተ ነፍስ መኾኑ ብቻ አይደለም፤ ጥራቱ በጊዜ ብዛትም አይበላሽም፡፡ በሌላ በሽታ ተጨማሪ ጉዳትን አያመጣም፡፡ በነጻ የሚታደል ነው፡፡ የድኻውም የባለ ጸጋውም ዓቅም ያገናዘበ ነው፡፡ ከዚህ ባልተናነሰ መልኩ ሌላም ጥቅምም አለው፡፡ እርሱስ ምንድነው? አንድ ታካሚ ለቀዶ ጥገና ወደዚህ በመጣ ጊዜ ቁስሉ ሌላ ሰው እንዲያየው አይደረግም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ወደኾነው ሆስፒታል ብትሔዱ ግን አንድ የቀዶ ጥገና ልዩ ባለ ሙያ (Specialist) አስቀድሞ የታካሚውን ቁስል ሳያይ የቁስል ፋሻን ማድረግ አይችልም፡፡

በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ አንደኛ በአንድ ጊዜ ብዙ ሕሙማን ይታያሉ፡፡ ኹለተኛ ሕክምናው የሚሰጠው በምሥጢር ነው፡፡ የእያንዳንዱን ኃጢአተኛ ኃጢአትን በአደባባይ አንናገርም፡፡ ከዚያ ይልቅ መጀመሪያ ኹሉንም አንድ ላይ እናስተምራለን፡፡ ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ሕሊናውን እንዲያደምጥ እናደርጋለን፡፡ ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ካስተማርነው ትምህርት እንደ በሽታው ዓይነት የሚስማማውን መድኃኒት እያነሣ ይወስዳል፡፡ ሰባኬ ወንጌሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማንና ቀኖናን ያስተምራል፡፡ በዚያም አብሮ ክፉ ምግባርን ይገሥፃል፤ በጎ ምግባርን ያወድሳል፡፡ ዋልጌነትን ይነቅፋል፤ ንጽህናን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡ ትዕቢትን ይገሥጻል፤ ትሕትናን ያመሰግናል፡፡ መድኃኒተ ሥጋ በውስጡ ሕመሙን ማከም የሚችሉ ብዙ ንጥረ ነገርን እንደያዘ ኹሉ ከሰባኪው የሚወጣው ቃለ እግዚአብሔርም እንደዚሁ ለእያንዳንዱ ሰው የሚኾን ፈውስን ይዟል፡፡ ቃሉ ኹሉም እየሰማ ይነገራል፤ ወደ እያንዳንዱ ሕሊና እንዲገባ ይደ ረጋል፡፡ በምሥጢርም ሕክምናውን ያከናውናል፡፡ የታማሚው ቁስል ሳይገለጥ በስውር ጤናውን ይመልስለታል፡፡

ታዲያ መድኒተ ሥጋን ለማግኘት የምንፋጠነውን ያህል ቃለ እግዚአብሔርን ለመማር፥ ተምረንም ከመስማት ባለፈ (አጋንንትም ይሰማሉና) በተግባር መድኃኒትነቱን ተጠቅመንበታልን?

#መቅረዝ_ዘተዋሕዶ_ፌስቡክ_ገጽ
ውርጃ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምሮ
ምድሪቱ (የሴቲቱ ማኅፀን) ዘር ከዘራንባት በኃላ ፍሬ እንዳታፈራ የምናደርገው ስለ
ምንድን ነው? ውርጃን የምናካሒደው ስለ ምንድን ነው? እናንተ ዘማውያን ሆይ! ዝሙት
መፈጸማችሁ ሳይበቃ ሰውን መግደል ትጨምሩበታላችሁን? እንግዲህ ስካር እንደ ምን ሴተኛ
አዳሪን እንደሚያደርግ፣ ሴተኛ አዳሪነትም ዘማዊ፣ ዝሙትም እንደ ምን ነፍሰ ገዳይ
እንደሚያደርግ ታስተውላላችሁን?
ይህን ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ምክንያቱም ይህን ሕፃን ከተወለደ በኃላ ከቤት
አስወጥተን አይደለም ያባረርነው፤ እንዳይወለድ ከለከልነው እንጂ ወዮ! ስለምን
የእግዚአብሔርን ስጦታ ታቃልላላችሁ? ስለምን ሕጉን ትተላለፋላችሁ? ስለምን ርጉም የሆነን
ግብር እንደ በረከት ትቆጥሩታላችሁ? ስለምን እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያዘጋጀውን
መንገድ መግደያ ታደርጉታላችሁ? ስለምን ልጅን አቅፋ እንድትስም የተፈጠረችውን ሴት ነፍሰ
ገዳይ እንድትሆን ታደርጓታላችሁ? እህቴ ሆይ! ፍቅረ ንዋይ ዐይንሽን አሳውሮት፣ ዳግመኛም
በፍትወት ከሚመስሉሽ ጋር ዝሙትን ለመሥራት ስትዪ ፍምን በራስሽ ላይ አታከማቺ ወንድሜ
ሆይ! ምንም እንኳን ይህን አሰቃቂ ግድያ የምትፈጽመው እርሷ ብትሆንም አንተም ከእርሷ ጋር ተባባሪ ነህ። ✞
"እውነተኛ ክርስቲያን አባቱ ክርስቶስን ይመስላል፡፡ ይሰደዳል
እንጂ አያሳድድም፡፡ ይሰደባል እንጂ አይሳደብም፡፡ የጠፉትን
ፍለጋ ይደክማል እንጂ ይባስ ብሎ አይገፈትርም፡፡ በወንድሙ
ውድቀት ያለቅሳል እንጂ አይደሰትም፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን
አባቱ ሌላ ነው፡፡
ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና በጊዜውም ያለ ጊዜውም
ሊሆን ይገባል፡፡ ባገኘን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ባጣንም ጊዜ፤ ባለጤና
በሆንን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በታመምንም ጊዜ፤ ሲሳካልን ብቻ
ሳይሆን ባልተሳካልንም ጊዜ ማመስገን መለማመድ አለብን፡፡
የምስጋናችን ምንጭ የሁኔታዎች መለዋወጥ ሳይሆን ስለ
አምላካችን ብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ ስንለማመድ
በክብር ላይ ክብር ይጨመርልናል፤ እንደ አባታችን ኢዮብ
የዲያብሎስን አፍ እንዘጋለን፡፡
ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን?” እንኪያስ "በዘፈን
የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት
የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ
እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ
ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ
አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም
ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ
ተአምር ይሄ ነው፡፡"
ቅዱሥ ዮሐንስ አፈወርቅ
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ደብረ ምጥማቅ (ግንቦት 21)

ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መላእክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር፤ እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ፤ ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር፤ ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል፤ እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር፤ አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው። ወይ ግሩም ታዲያ ይህ በዚያ ደጉ ዘመን ነበር፤ አሁን ግን ኃጢያታችን ሲበዛ በረድኤት ካልሆነ በገሃድስ ተገልጻ አትታይም ለበቁ ካልሆነ።

ከእመቤታችን ረድዔት በረከት ይክፈለን
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
የሚፈውስ እንባ
/በቅዱስ ኤፍሬም /

ሰውን የምታድን ክርስቶስ ሆይ! ከአንተ በቀር ማን ያድነኛል? የድኅነት ምንጭ ከኾንከው ከአንተ በቀር የታመመችውን ነፍሴን ማን ይፈውሳታል? አቤቱ ሆይ! እንኪያስ የታመመችውን ችግረኛ ሴት እንደፈወስካት እኔንም ከጥፋት ከምረረ ገሃነም አድነኝ፡፡ ምሕረት ቸርነትኅ በእኔ ላይ ትኹን፡፡ ጠላቴን ድል አደርገው ዘንድ እርዳኝ፡፡ ብርቱ በምትኾን ክንድኅ ደካማ የምኾን እኔን አበርታኝ፡፡ አበርታኝና ለተጋድሎ የተዘጋጀኹ እንደኾንኩ ዐይቶ ጠላቴ ይራድ፤ ይንቀጥቀጥ፤ ይፈርም፡፡ አበርታኝና ጠላቴ የተዋረደ ይኹን፡፡ አበርታኝና ጠላቴ (ዲያብሎስ) በሐፍሬት ከፊቴ ይመለስ፡፡ አበርታኝና እኔም ስምኽን ከፍ ከፍ ላድርገው፡፡

አቤቱ ሆይ! ጐስቋላ የምኾን እንባዬን ተቀበልልኝ፤ ዕዳዬንም ፋቅልኝ፡፡ ፍቅርኅ የእኔን የበደለኛውን የክፉ ምግባሬ ፍሬ ይደምስስልኝ፤ ምረረ ገሃነምም አያግኘኝ፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ ሆይ! ዕዳዬን ደምስስልኝና ጠላቴ ይፈር፡፡ ፈተናውን ድል አደርግ ዘንድ፥ ድል አድርጌም ዘወትር ከአንተ ጋር እኖር ዘንድ ምሕረት ቸርነትኅ ከእኔ ጋር ትኹን፡፡

አቤቱ ሆይ! አልቅሳ ሰምታኻታልና፥ በሚፈውስ እንባ አጥባኻታልና፥ ፍጥረትን ኹሉ ለፈጠርከው ለአንተም ቤተ መቅደስህ አድርጋኻታልና በደለኛ የምትኾን ሰውነቴ፥ ከባሕርይ አባትኅ ከአብ ከባሕርይ ሕይወትኅ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ታከብርኻለች፡፡ አሜን!!!

#ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ
To join our channel click the one in blue

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
አንድ 60 ሰው የገደለ ወንበዴ ወደ አንድ አባት መጥቶ ንስሐ
ስጡኝ 60 ሰው ገድያለሁ አላቸው እሳቸው አንተማ ሰይጣን ነህ
ከኔ ራቅ ቢሉት እሳቸውንም ገደላቸውና ሄደ።
ሌላ ቄስ አገኘ "አባቴ ንስሐ ይስጡኝ 60 ሰው ገድያለሁ
ይህንንም ብዬ የጠየኳቸው ካህን ሰይጣን ብለውኝ እሳቸውንም
ገድያለሁ " ካህኑም አንተ አረመኔ እኔንም ልትገለኝ ነውን?
ቢሉት እሳቸውንም ገደላቸው በዚህ ሁኔታ ሌላ ሁለት ካህናትንም
ገድሎ ወደ ለመደው ውንብዳናው እየሄደ ሳለ አንድ ሽማግሌ
መነኩሴ ውኃ ሊቀዱ አገኘና አንቱ ሽማግሌ ይቁሙ አላቸው።
"አቤት ልጄ" 60 ሰዎችን ገድዬ ንስሐ ልገባ ብጠይቅ
አልፈቅድም ብለውኝ 4 ካህናት ገድያለው እርሶንም እርሶንም
ንስሐ የማይሰጡኝ ከሆነ እገድሎታለሁ አላቸው። እሳቸውም
ሥቅሰቅ ብለው አለቀሱለት " በእውነት # እግዚአብሔርን
በድለሃል አስከፍተሃል ግን መሃሪ አምላክ ነው። "አሉት ከዛም
ወደ ጉድጓድ ወሰዱትና " ላንተ እፀልይልህ ዘንድ የፀሎት
መጽሐፌ እዚህ ወድቋልና አውጣልኝ " አሉት ከዛም ወደ ጥልቁ
በገመድ አንጠልጥለው አስገቡት መግባቱን ሲያረጋግጡ
ገመዱን ቆረጡ። አንተ ሽማግሌ እገድልሀለሁ እያለ መዛት
ጀመረ ትተውት ሄዱ። ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ቂጣና ውኃ ይዘው
መጥተው "ልጄ እንዴት ነህ አሉት" እገድልሀለው አለ።
"ምግቡን ሰጥተውት ሄዱ።
ከ12ሰዓት በኋላ ተመለሱ" ልጄ እንደምን አለህ " ደከም ባለ
ድምጽ እገድልሃለሁ አለቅህም " ምግብ ሰጥተውት ሄዱ ።
1 ቀን ቆይተው መጡ " ልጄ እንደምን አለህ "
እ..ገ..ድል..ሀለው" አለ እጅግ በደከመ ድምጽ ምግቡን
ሰጥተውት ሄዱ አንድ ቀን ቆይተው ተመለሱና " ልጄ እንደምን
ዋልክ ሲሉት"""እግዚአብሔር ይመስገን ""አለ ትዕቢቱ በጾም
ተሸነፈ ነፍስ ስጋን አሸነፈች እሳቸውም በገመድ አውጥተው
ንሰሃን ሰጡት የአምላክ ባሪያ ሆነ ኖረ።
ለሁላችንም ፈርሃ እግዚአብሔር ትዕግስትን ማስተዋልን ይስጠን
አሜን።
ትልቁ ነገር ደግሞ ለንስሐ ሞት ያብቃን ማለት ነው አሜን
ያብቃን!!
መልካም ቀን
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ንስሐ ምንድን ነው?

ንስሐ ማለት አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መቆርቆሩ፣ መፀፀቱ፣ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው። በአጭሩ ንስሐ ማለት ትርጉሙ ይህ ሲሆን፤ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስገነዝበን ቀጥሎ የተጠቀሱትን ፍችዎች ያጠቃለለ ሆኖ እናገኘዋለን።
•ንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። ሚልኪያስ 3፡7
•ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ነው። 2 ቆሮንቶስ 6፡19
•ንስሐ ከኃጢአት እንቅልፍ መንቃት ነው። ሮሜ 13፡11
•ንስሐ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው። ኤፌሶን 5፡14
•ንስሐ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔርን የሚያስወድድ ከንጹህ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ነው። ሕዝቅኤል 36፡25-27
•ንስሐ ከኃጢአትና ከዲያቢሎስ ባርነት ነጻ መውጣት ነው። ዮሐንስ 8፡34-36
•ንስሐ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ቅድስና ብሎ ኃጢአትን መተው ነው። ምሳሌ 28 13
•ንስሐ ኃጢአትን ከተዉ በኋላ በፍጹም መልሶ አለመስራት ነው።
•ንስሐ ስለ አለፈው ስህተት አብዝቶ ማልቀስ፤ ያለፈውን የኃጢአት ኑሮ ማውገዝና መኮነን ነው። ኢዩኤል 2፡12
•ንስሐ ፍጹም የሆነ የሕይወት ለውጥ እንጂ ጊዜያዊ ስሜት አይደለም፤ ሮሜ 12፡2
•ንስሐ ኃጢአትን ሲሠሩ ከመኖር ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር መኖርን መሻት ነው። መዝሙር 73፡28
•ንስሐ የአዕምሮ መታደስ ነው። ሮሜ 12፡2
•ንስሐ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የሚያስችል ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር የሚያስገባ ቁልፍ ነው። ማቴዎስ 25፡1-13
•ንስሐ በቀራንዮ መስቀል ላይ እኛን ለማዳንና ከኃጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት የፈሰሰልንን የክርስቶስን ደም እንድናስብ የሚያደርግ መንፈሳዊ ሃብት ነው።
•ንስሐ ከኃጢአት የሚያነጻ ሱራፌል ከመንበረ ሥላሴ የወሰዱት የእሳት ፍም ነው። ኢሳያስ 6፡4
•ንስሐ ከሚመጣው የመጨረሻ መከራና ሃዘን መዳኛ ወይም ማምለጫ መንገድ ነው። ዮናስ 3፡10
•ንስሐ እግዚአብሔር የሰውን ኃጢአት ይቅር የሚልበትና ከኃጢአት ውጤት የሚያድንበት መሳርያ ነው።
•ንስሐ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ የተዘረጋ የእግዚአብሔር እጅ ነው። መዝሙር 50/51
•ንስሐ እግዚአብሔር ወደ ሰው የሚጣራውን ጥሪ ሰምቶ ወደ እርሱ መመለስ ነው። ዮሐንስ 7፡51። ኤፈሶን 4፡30
•ንስሐ ስለ አለፈው ኃጢአት ከመፀፀት የተነሳ የተሰበረ ልብ ነው። መዝሙር 50/51፡17
•ንስሐ ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው ተፀፅተው ከእግዚአብሔር ጋር እንዳይታረቁ በብርቱ በሚጥረው ሰይጣን ላይ የተገኘ ድል ነው። መዝሙር123/124፡ 6-7::
ወስባት ለእግዚ አብሔር
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
♥️ዝሙትን የሚፈፅም በገዛ ስጋው ላይ ሀጢያትን ይሰራል፡(1ኛ ቆሮ 6÷18)
♥️ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው፡ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት! (1ኛ ቆሮ 7÷2)
👉በዚህ በአለንበት ዘመን ሰውን ያንበረከከ ትልቁ ሀጢያት "ዝሙት" ነው፡
♥️ዝሙት ሰውን ከእግዚአብሔር ይለየዋል፡
ዝሙትን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን ህግ ይጥሳልና፡(ዘዳ 5÷18)
♥️ዝሙት ሀጢያት ነው! የሀጢያት ደሞዝ ደግሞ ሞት ነውና፡(ሮሜ 6÷18)
♥️እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው! ከሀጢያት መራቅ ማስተዋል ነው። አስተዋይ የሆነ ሰው ከእግዚአብሔር መንግስት እንዳይለይ ራሱን ከአመንዝራ ሊጠብቅ ይገባዋል።
♥️ዝሙት ከክፉ ልብ የሚወጣ፡(ማቴ 15÷19)
የክርስትያኖችን ህብረት የሚረብሽ፡(1ኛ ቆሮ 5÷9-11 )
♥️ዝሙት ከእግዚአብሔር የሚለይ ለሰው ልጅ ️መንፈሳዊ እድገት እንቅፋት የሆነ ሀጢያት ነው፡(1ኛ ቆሮ 6÷9)
♥️ስለዚህ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስትያኖች ሀጢያትን በመስራት ከእግዚአብሔር ቤተ መንግስት እንዳንለይና ርስቱን እንዳናጣ ራሳችን ከዝሙት ልንጠብቅ ይገባል።
እግዚአብሔር ከዝሙትና ከርኩሰት ነፃ የሆነ ህይወትን ያድለን፡አሜን
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር