የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
የወፏ__ምክር
🦆🦆🦆🦆

አንድ ሰው አንዲት በጣም ቆንጆ ወፍ በመዳፉ ውስጥ ይዞ ጨምቆ ሊገድላት ሲል ከመሞቷ በፊት አንድ ወይም ሁለት ቃላት ትናገር ዘንድ እንዲፈቅድላት ጠየቀችው፡፡

እንዲህም አለች “እባክህ አትግደለኝ፡፡ ሶስት ጠቃሚ ምክሮችን እሰጥሃለሁ፡፡ የመጀመሪያው ምክር፤ በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ፡፡ ሁለተኛው ምክር፤ ስለሆነው ነገር ሁሉ አትቆጭ፡፡” ካለችው በኋላ ዝም አለች፡፡

ሶስተኛውንም ምክር ትነግረው ዘንድ ሲጠይቃት “ሶስተኛው ምክር ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ካለቀከኝ አልነግርህም፡፡” አለችው፡፡

በዚህ ጊዜ ሰውየው ሶስተኛውን ምክር ለመስማት በጣም ጓጉቶ ስለነበረ ወፏን ሲለቃት ከአንድ ዛፍ ላይ በርራ ወጥታ “ምንድን ነበር ያልኩህ? ታስታውሳለህ?” ብላ ጠየቀችው፡፡ እርሱም “በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ ነው ያልሺኝ፡፡” አላት፡፡ “ሁለተኛውስ?” “ስላለፈው ነገር ሁሉ አትቆጭ፡፡”“አዎ፡፡ ነገር ግን የነገርኩህን ነገር አልተቀበልክም፡፡ ባትለቀኝ ኖሮ ከሆዴ ውስጥ ለልጅ ልጆችህ የሚሆን ወርቅ ታገኝ ነበር፡፡ ይኸው ነው፡፡” አለችው፡፡
ሰውየው “ሶስተኛውስ ታዲያ?” አላት፡፡

እሷም “ሶስተኛው የሁለተኛው ምክር ድጋሚ ነው፡፡ ስላጣኸው ነገር አትቆጭ፡፡ ይኸው
ነው፡፡ ደህና ሁን፡፡ ብላው በራ ሄደች።

🐦🐤🐦🐤🐦🐤🐦🐤🐦🐤🐦🐤

ክርስቲያን በህይወት ዘመኑ ጠቢብ፣ ብልህ፣አስተዋይ መሆን አለበት ለሂወቱ የሚጠቅመውን ነገር አጥብቆ ሊይዝ ይገባዋል።

ያለፈውን ነገር እያሰበ አይቆጭም ለወደፊቱ ይማራል እንጂ

" እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 10:16)

🍇መልካም ሰንበት🍇

Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
“ልጆቼ! ሓኪሞች ብትሆኑ፣ መሀንዲሶች ብትሆኑ፣ የሽመና ሠራተኞች ብትሆኑ፣ መርከበኞችም ብትሆኑ መልካም ነው፡፡ ይህን ጥበብ መማራችሁም ጥሩ ነው፡፡ እኔ ግን ከዚህ የበለጠ ጥበብ አሳያችኋለሁ፡፡ በዚህ (በተማራችሁት ምድራዊ) ጥበባችሁም ሌላ ጥበብ ትማሩበት ዘንድ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሰማያዊን ጥበብ! ከላይ በገልጽኩላችሁና እናንተ በተማራችሁት ጥበብ ተጠቅማችሁ ገንዘብ ማግኘታችሁ አይቀርም፡፡ በዚህ ገንዘባችሁ ግን ድሆችን መርዳት ልመዱበት፡፡ ይህ የምነግራችሁን ጥበብ እንደ ቀላል የምታዩት አትሁኑ፡፡ መሀንዲሶች ብትሆኑ በምህንድስና ጥበባችሁና እውቀታችሁ በዚህ ምድር የሚያማምሩ ቪላ ቤቶችን ልትሠሩ ትችላላችሁ፡፡ በምነግራችሁ ጥበብ ግን
በመንግሥተ ሰማያት ውስጥ የዘላለም ቤታችሁን ትሠራላችሁ፡፡ በዚህ ምድር ለምትሠሩት ቤታችሁ በጣም ብዙ ወጪ ብዙም ድካም ይጠይቃችኋል፡፡ በምነግራችሁ ጥበብ ግን ብዙ ልፋት የለውም፡፡ ወጪአችሁ መልካምና ፈቃደኛ መሆን ብቻ ነው፡፡ በዚህ ምድር ለምትሠሩት ቤት የተለያዩ ዓይነት ብረቶችና ማቅለጫዎች እንዲሁም የከበሩ ድንጋዮችን ትጠቀማላችሁ፡፡ በምነግራችሁ ጥበብ ግን ይህ ሁሉ አያስፈልጋችሁም፡፡ የሚያስፈልጋችሁ ብሎን ወይንም ብረት ወይንም የከበረ ድንጋይ ሳይሆን መልካም ምግባራችሁና በጎ ፈቃዳችሁ ብቻ ነው፡፡

እንደውም እኔ እነዚህ የተማራችኋቸው ጥበቦች ጥበብ ብዬ ለመጥራት በጣም እቸገራለሁ፡፡ ለምን ብትሉኝ ከምነግራችሁ ጥበብ ጋር ሳወዳድራቸው በጣም ስለሚያንሱብኝ አያያዛቸው ላላወቀበት ሰውም ብዙ ጉዳት ስለሚያመጡ፡፡ እስኪ አስተውሉት! አንድ ሰው በዚህ ምድር ባገኘው ጥበብና ገንዘብ ተጠቅሞ ድሆችን መርዳት ሲገባው አላግባብ ሲበላ ሲጠጣ በኋላ ግን በስኳር፣ በሪህ፣ በቁርጥማት፣ በራስ ምታት፣ በልብና በኩላሊት በሽታ የሚሰቃይ ከሆነ ይህ ጥበብ እለው ዘንድ እንዴት እደፍራለሁ? እንግዲያውስ ጥበባችሁ ጥበብ ይሁንላችሁ፡፡ ጥበባችሁ ለሥጋችሁም ለነፍሳችሁም የሚጠቅም እንጂ በዚህ ዓለምም ይሁን በሚመጣው ዓለም የሚጎዳችሁ አይሁን፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ታቦተ ጽዮን የአምላክ እናት
[በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ የኾነቺው በወርቅ የተለበጠችው ይቺ የእግዚአብሔር ታቦት፤ በንጽሕና በቅድስና የተጌጠችው የእግዚአብሔር ወልድ እናት የኾነቺው የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡

በመጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፪ ቊጥር ፲፪ትን እንደምናነበው፤ ታቦተ ጽዮንን ያገለግሉ የነበሩት የካህኑ የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በሠሩት ታላቅ ኀጢአት ምክንያት እግዚአብሔር ዐዝኖባቸው የክብሩ መገለጫ የኾነችው ታቦት በፍልስጤማውያን እጅ እንድትማረክ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቤንኤዘር ወደ አዛጦን በመውሰድ በድፍረት ከዳጎን አጠገብ አኖሯት፤ ነገር ግን ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ወድቆ ተገኘ፤ እነሱም እንደገና ዳጎንን ወደ ስፍራው መልሰው ኼዱ፤ በነጋታው ለማየት ሲመጡ የዳጎን እጅ እግሩ ተቆራርጠው ደረቱ ለብቻው ወድቆ ተገኘ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይኽነን ታሪክ ይዞ ‹‹የእግዚአብሔር ታቦትንስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው?›› (፪ቆሮ ፮፥፲፮) በማለት የታቦትን ክብር አስተምሮበታል፡፡

ኢትዮጵያዊዉ ሊቅም በሰቈቃወ ድንግል መጽሐፉ ላይ የአምላክ ማደሪያ የኾነችው ታቦት ወደ ፍልስጤም ሀገር ኼዳ ዳጎንን ሰባብራ እንዳጠፋች ኹሉ፤ አማናዊት የጌታ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን ይዛ ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ የግብጽ ጣዖታት ኹሉ እየተሰባበሩ መውደቃቸውን ሲገልጹ፡-

"ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ
አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ
ወድቁ አማልክተ ግብጽ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ
ወተኀፍሩ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ"
(ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የኼደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦት ታቦተ ጽዮን፤ የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፤ በዚች ታቦት የተመሰለች ድንግል ማርያምም ኹሉን ማድረግ ከሚችል ከልጇ ጋር ግብጽ ወደሚባል አገር በኼደች ጊዜ፤የሐሰተኛ ሰይጣን ዘፋኖች የኾኑ የግብጽ ጣዖታት ፈረሱ፤ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ኹሉ ዐፈሩ) በማለት አነጻጽሯል፡፡

በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ስለሠሩት ታላቅ የድፍረት ኀጢአት እግዚአብሔር ቀጣቸው ብዙዎቹ ሞቱ፤ ያልሞቱትም በእባጭ ተመቱ፤ የአይጥ መንጋም ምድራቸውን አጠፋባቸው፤ ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራው በምን እንስደደው? ብለው በመማከር፤ የሚያጠቡ ቀንበር ያልተጫነባቸው ኹለት ላሞችን በመውሰድ፤ በዐዲስ ሠረገላ ጠምደው እንቦሶቻቸውን (ጥጆቻቸውን) ከቤት ዘግተው በማስቀረት፤ ታቦተ ጽዮንን እጅ መንሻውን በሠረገላው ላይ ጫኑ፤ ያን ጊዜ እነዚኽ ላሞች ጥጆቻቸውን ሳይናፍቁ ወደቀኝ ወደግራ ሳይሉ እምቧ እያሉ ወደ ቤተ ሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ገሠገሡ፤ ሠረገላውም ወደ ቤትሳሚሳዊው ወደ ኢያሱ እርሻ ሲደርስ ያን ጊዜ ሌዋውያን ታቦት ጽዮንና ዐብሮ የነበረውን የወርቅ ዕቃ አውርደው በታላቅ ደንጊያ ላይ በማኖር፤ ሠረገላውን ፈልጠው ጊደሮቹን ሠውተዋቸዋል፡፡

ይኽም ለጊዜው ቢደረግም ለኋላው ግን ምሳሌ ነበር፤ ላሞቹ የሰማዕታት፤ ልጆች የልጆቻቸው፤ ሠረገላ የመስቀል፤ ልጆቻቸውን ከወደኋላ እንዳስቀሩ፤ ሰማዕታትም የልጅ የገንዘብ ፍቅር አያስቀራቸውምና፣ ሠረገላውን ፈልጠው እንደሠዋቸው ራሳቸውን በመስቀል ይሠዋሉና በማለት የብሉይ ኪዳን መተርጒማን ያመሰጥሩታል፡፡

የመልክአ ማርያም ደራሲ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችውን የኻያ መንፈቅ ማለት ዐሥሩ ቃላት የተጻፉባቸው ጽላት የተቀመጡባትን የእግዚአብሔርን ታቦት ጊደሮቹ ከልጆቻቸው ይልቅ በማስበለጥና በመውደድ ይዘዋት ወደፊት እንደነጎዱ፤ ርሱም የልዑል ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ጥልቅ ፍቅር በድርሰቱ ላይ፡-

"ማርያም ጽዮን ታቦት ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ
ዕጐላት እምዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ
አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እምይእዜ ለግሙራ"
(የኻያ እኩሌታ የሚኾን የእውነት ቃል ማደሪያ ጽዮን ማርያም ሆይ፤ ጊደሮች ከጥጆቻቸው ይልቅ አንቺን እንደአፈቀሩ፤ ወድጄሻለኹና ከዛሬ ዠምሮ ፈጽሞ ውደጅኝ) በማለት ገልጦታል፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በምስጢር በመራቀቅ "አንቲ ውእቱ ጽዮን ታቦተ አምላከ እስራኤል እንተ ነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤ ወበህየ አውደቀቶ ለዳጎን..." (ወደ ኢሎፍሊ ምድር የኼደች የእስራኤል አምላክ ታቦት (ማደሪያ) ጽዮን አንቺ ነሽ፤ በዚያም ዳጎንን የጣለችው ጣዖት አምላኪዎቹንም የቀሠፈቻቸው፤ በአመጣጧም ከአዛጦን ሰዎች ካሳን የተቀበለች፤ ከካሳዋም ጋር እንቦሳ ባላቸው ላሞች አስጭነው የሸኟት፤ ከርሷም ጋር የወርቅ ሳጥኖችን በጐኗም፤ የበድን ሣጥን ሥርዐትን አልሠሩም፤ ነገር ግን በርሷ ዘንድ ካለ ከወርቅ መሣሪያና ከሣጥን ጋራ ላኳት፤ በእንግድነቷ ወቅትም በአሳደራት ጊዜ ወደ ቤቱ በመግባቷ እግዚአብሔር የአቢዳራን ቤት ባረከ) በማለት የምሳሌዋን እሙንነት በሰፊው ገልጧል፡፡

ይኽቺም የእግዚአብሔር ታቦት በቤተ ዐሚናዳብ ኻያ ዓመት ተቀምጣለች፤ ከዚያም የሳኦል ዘመን ዐልፎ የእግዚአብሔር ወዳጅ ዳዊት በነገሠ ጊዜ በዐዲስ ሠረገላ አድርገው ከቤተ ዐሚናዳብ አውጥተው በበገና፣ በመሰንቆ፣ በከበሮ፣ በነጋሪት፣ በጸናጽል እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይዘዋት ሲመጡ፤ የእግዚአብሔርን ታቦት ኦዛ በድፍረት በመያዙ እግዚአብሔር ቀሥፎት ወዲያውኑ በታቦቷ አጠገብ ሕይወቱ አልፏል፤ ያን ጊዜ ነቢዩ ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት ያደረገችውን ተአምራት ተመልክቶ፤ እግዚአብሔር በርሷ እንዳደረ በማመን በፍርሃት ተውጦ "የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ይመጣል?" በማለት ለታቦቷ ያለውን ታላቅ ክብር ገልጧል (፪ ሳሙ ፮፥፱-፲)።

በዘመነ ሐዲስም በተመሳሳይ መልኩ ጌታን በማሕፀኗ የተሸከመች የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ አማናዊት ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ኤልሳቤጥ ልክ እንደ ዳዊት መንፈስ ቅዱስ መልቶባት፤ የጌታ ታቦት (ማደሪያው) መኾኗን ተረድታ፤ ድምፅዋን አሰምታ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል?" በማለት ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላትን ታላቅ አክብሮት እንደ ዳዊት ገልጣለች (ሉቃ ፩፥፵፫-፵፮) ፡፡

ከዚያም ዳዊት ይኽነን ታላቅ ቃል ከተናገረ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት በአቢዳራ ቤት ለሦስት ወር ያኽል እንደተቀመጠች (፪ ሳሙ ፮፥፲፩)፤ በተመሳሳይ መልኩ የአምላክ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያምም በካህኑ በዘካርያስ ቤት ለሦስት ወር ተቀምጣለች (ሉቃ ፩፥፶፮)፡፡ ኦዛ ተቀሥፎ ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቢዳራ ቤት ገብታ ቤቱ ለሦስት ወር በበረከት እንደተመላ ኹሉ፤ በተመሳሳይ መልኩ ዘካርያስም የመልአኩን ቃል ባለመቀበሉ ከተረገመ በኋላ (ሉቃ ፩፥፳)፤ እውነተኛዪቱ የአምላክ ታቦት ድንግል ማርያም ቤቱ ለሦስት ወር ተቀምጣለች፡፡

እግዚአብሔር በታቦቷ ምክንያት የአቢዳራን ቤት እንደባረከ ኹሉ የዘካርያስንም ቤት በእመቤታችን ምክንያት የባረከው መኾኑን ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በመጽሐፉ ሲገልጽ ‹‹ድንግል በምስጢር የተመላ ታቦትን ኾና ትኖራለች፣ የካህናት ወገኖችም ደስ ይላቸዋል፣ ያከብሯታልም›› በማለት ታቦትነቷን አጒልቶ አስተ ❖ በተጨማሪም የእግዚአብሔር ታቦት ከቤተ አቢዳራ ወደ ዳዊት ከተማ ስትገባ፤ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ከደስታው ብዛት የተነሣ የጌታ የክብሩ መገለጫ በኾነችው በታቦቷ ፊት እየዘለ
ለ እንዳመሰገነ ኹሉ (፪ሳሙ ፮፥፲፪-፲፭)፤ አካላዊ ቃልን በማሕፀኗ የተሸከመች የአምላክ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም ወደ ተራራማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ታላቁ ነቢይ መጥምቁ ዮሐንስ በእናቱ ማሕፀን ኾኖ ከደስታው ብዛት የተነሣ እየዘለለ አመስግኗል (ሉቃ ፩፥፵፩-፵፭)፡፡

ይኽነን ምስጢር ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሲያብራራ፦ "ንጉሡ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ይዘል ነበር፤ ከልቡ ደስታ የተነሣ ለንጉሣውያኑ ደንብ አልታዘዘም፤ እንዲኹ ዮሐንስ ደግሞ ገና ፅንስ ሣለ ከደስታው የተነሣ ከዳዊትም በላቀ ኹኔታ ዘለለ፤ ፅንስ ቢኾንም የእርሱ ባልኾነው በዚኽ ዕድሜ አልተገታም፤ ድንግል እና ቡርክት የኾነችው እናት የእግዚአብሔር ቤት ምስጢራት ከመሉባት ታቦትም በላይ ውብ ነበረች፤ ዳዊትም በአክብሮት በታቦቱ ፊት ዘለለ፤ ይኽም ዮሐንስ በማርያም ፊት ሊዘል እንዳለ አስቀድሞ ያሳይ ነበርና፤ ከዳዊት በቀር ንጉሥ መዝለሉ ተሰምቶ አይታወቅም፤ ሕፃን መዝለሉም እንዲኹ፤ ነቢያት ካህናት የእግዚአብሔርን ልጅ መንገድ አስቀድመው አመለከቱ፤ ርሱም በመጣ ጊዜ ይሹት የነበሩትን ምልክቶች ፈጸማቸው፤ የጌታውን የንጉሡን ምልክት ይጠቁም ዘንድ፤ ዳዊት በደስታ በታቦቱ ፊት ዘለለ፤ዮሐንስ በማርያም ፊት የሚያደርገውን ነገር ምሳሌ በመኾን አሳየ፤ ያቺም ብላቴና እንዲኹ የእግዚአብሔር ታቦት ነበረችና፤ የምስጢራት ጌታ በርሷ ዐደረ፤ ከዚኽም የተነሣ ልክ እንደዚያ ጀግና ንጉሥ ሕፃኑ በርሷ ፊት በደስታ ዘለለ፤ ርሷ በቅዱስ ቃል እንደተመላ ታቦት የተሸከሟት ነበረች፤ የትንቢት ምስጢራት ፍቺ በርሷ ዐደረ) በማለት ይኽ ምሁር ቅድስት ድንግል ማርያምን በምስጢር የተመላች የአምላክ ታቦት መኾኗን በማብራራት ገልጦታል፡፡

ዳግመኛም ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በደስታ ሲያመሰግን አይታ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ብትንቀው እግዚአብሔር ተቈጥቷት በሕይወቷ ዘመን ኹሉ የልጅ ጸጋ እንዳታገኝ በምክነት ቀጥቷታል (፪ሳሙ ፮፥፳-፳፫)፡፡ ይኸውም ማደሪያው የኾነች ታቦቷን በድፍረት ሊነካት የሞከረውን ኦዛን የቀሠፈ፤ ዳግመኛ የጌትነቱ መገለጫ በኾነች በታቦቷ ፊት ያመሰገነ ዳዊትን የናቀች ሜልኮልን በምክነት የቀጣ አምላክ፤ ዛሬም ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን፤ የድንግልና ጡቶቿን የመገበችውን፤ በዠርባዋ ያዘለችውና በደረቷ የታቀፈችውን ቅድስት እናቱን በድፍረት የሚነቅፉ፤ ሔዋንን ያሳተ እባብ መርዝ ክሕደቱን በአፋቸው የረጨባቸው በልቡናቸው ያሳደረባቸው፤ ነቢያት ሐዋርያት ያስተማሩትን የሚያጣምሙ ፀረ ማርያሞች ለዚኽ ድፍረታቸው ንስሓ ካልገቡ የዘላለም ቅጣትና፤ በዚኽ ዓለምም ከድንግል ማርያም አማላጅነት የሚገኘውን ታላቅ በረከት በማጣት እንደ ሜልኮል የበረከትና የጸጋ ምክነት ያጋጥማቸዋል፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ስለሚደርስባቸው ዘላለማዊ ምክነት በመዝ ፻፳፰፥፭-፰ ላይ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ይፈሩ፤ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ፤ በሰገነት ላይ እንደበቀለ ሣር ሳይነቀል እንደሚደርቅ ለሚያጭደው እጁን፤ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ ዕቅፉን እንደማይመላ ይኹኑ፤ በመንገድም የሚያልፉ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይኹን በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም›› በማለት እንደተናገረ ጽዮን የተባለች የድንግል ማርያም አማላጅነት የሚቀዋወሙ የዲያብሎስ የግብር ልጆች መናፍቃን እንደ ሜልኮል ከእግዚአብሔር ጸጋ የራቁ ናቸው።

ከሊቃውንትም አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ፡-
"እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦት ሕግ ከመ ዘፈነ
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ሥነ
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ
ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቊርባነ
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ ››
(አንቺን ያስገኘ የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት ሜልኮል እስከናቀችው ድረስ በእግዚአብሔር የሕግ ታቦት ፊት እንዳመሰገነ፤ ድንግል ሆይ እኔም በሥዕልሽ ፊት እዘምራለኍ፤ ድንቅ ታምርሽንና የቀረበ መንፈሳዊ ምስጋናሽን የሚንቅ በመላእክትና በሰው አንደበት የተረገመ ይኹን) በማለት ገልጿል፨

በተጨማሪም ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በምስጢር በመራቀቅ ቅድስት ድንግል ማርያምን “በምስጢር የተመላች ታቦት፣ የቃል ኪዳን ታቦት፣ እሳትን የተመላች ታቦት፣ የቅዱስ ቃል ታቦት” በማለት እያብራራ ያስተማረው የነገረ መለኮት ትምህርት እጅግ ጥልቅ ነው ፡፡
[የአምላክ ታቦት እመቤታችን ሆይ እንወድሻለን]


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉@ethiopianorthodoxbooks 👈
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
👉@ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
✦ እውነተኛ ታሪክ✦
የተወሰኑ መነኮሳት ወደ ታላቁ መቃርስ በመሄድ ከገዳማውያኑ መካከል አንዱ ወደ ባዕቱ እየመጣች የምትጎበኘው ሴት እንዳለችና ከእርሷም ጋር በኃጢአት መውደቁን ገልጸው ነገሩት። ቅዱስ መቃርስም ጊዜ በመውሰድ ወደ ባዕታቸው በመመለስ መነኩሴውን በጸሎት እንድያስቡ ነገራቸው።
ገዳማውያኑም ዳግመኛ በመመለስ ሴቲቱ በመነኩሴው ባዕት በዚህ ምሽት ሰዓት እንደምትገኝና ከነርሱም ጋር ወደ መነኩሴው ባዕት በመሄድ ይህንኑ እንዲመለከት ነገሩት።
ታላቁ መቃርስም ከገዳማውያኑ ጋር ወደ መነኩሴው ባዕት በመሄድ በሩን በማንኳኳት በስሙ ጠሩት። መነኩሴውም የሆነውን ነገር ስለተረዳ ሴቲቱን በጠረጴዛ
/ቅርጫት/ ውስጥ ደበቃት።
ቅዱስ መቃርስም ሰላምታ ሰጥቶ በጸጥታ ወደ ባዕቱ በመግባት በቅርጫቱ ላይ በመቀመጥ መነኩሴውን ወዳጄ ሆይ ሌሎቹ ሳይፈርዱብህ አስቀድመህ በራስ ላይ ፍረድ አሉት። ቅዱስ መቃርስ ከመነኩሴው ባዕት ሲወጣም የሰዎችን ኃጢአት በመሰወር ጌታህን አምላክህን ኢየሱስ ክርስቶስን መስለኽዋልና ሰላምታ ይገባሃል የሚል ድምጽ ሰማ።
📌መልዕክቱ
በዚህ ታሪክ ቅዱስ መቃርስ መነኩሴውን ሳያስቆጣው ሳያበሳጨውም ፈጽሞ በጽንአት በመታገስ አሸንፎት በንስሐ ወደ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመለስ የረዳው መሆኑን እንመለከታለን።
በትዕግሥት ሕይወት ቢገኝ ወደ ፍጹምነት ተፈጽሞ የማያደርስ እንደሆነ ነገር ግን የትዕግስት ሕይወት አስፈላጊነት በጥልቀት እየተረዳን በሄድን ቁጥር ብዙ የሚቀረው መሆኑን እየተረዳን እንደሚሄድ ነው።


Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
አንድ ትንሽ ወንድ ልጅና ሴት ልጅ አብረዉ እየተጫወቱ ነበር። ልጁ ደሳስ የሚሉ ብዮች ነበሩት። ልጅቷ ደግሞ ጣፋጭ ከረሜላዎች ነበሯት።

“የኔን ብዮች ልስጥሽና ያንቺን ከረሜላዎች ስጪኝ” አላት። ልጅቷ በመቀያየሩ ሃሳብ ተስማማች። ልጁ ካሉት ብዮች ውስጥ ትልቅና ቆንጆ የሆነዉን ደብቆ አስቀርቶ ሌሎቹን ሰጣት።

ልጅቷ ግን ቃል እንደገባችዉ ያሏትን ሁሉ ከረሜላዎች ሰጠችዉ። ያን ቀን ማታ ልጅቷ ሰላማዊ እንቅልፏን ተኛች። ልጁ ግን “እኔ ደብቄ ቆንጆዉን ብይ እንዳስቀረሁት እሷም የሚጣፍጠዉን ከረሜላ መርጣ አስቀርታ ይሆን እንዴ?” የሚል ሃሳብ ይዞት እንዲሁ ሲገላበጥ አደረ።
💖💝💖💝💖💝💖💝💖💝💖💝

ህሊናችንን በመጥፎ ሥራ ስንሞላው ሰዎችም እንደኛ ይመስሉናል። በእኛ ልክ እንመዝናቸዋለን፣ መጥፎና ክፉ ስንሆን ሰው ሁሉ መጥፎና ክፉ የሆኑ ይመስለናል። ስለዚህም መጀመርያ እራሳችንን እናጥራ።

Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
አንድ እምነት የነበረው እረኛ ነበረ ይባላል፡፡ ምሳ ለመብላት ሲፈልግ ያሰማራቸውን በጎች ለቅዱሳን፣ ለመላእክት አደራ ሰጥቶ ይሔዳል፡፡ "ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! እነዚህን በጎቼ ከተኩላ ጠብቅልኝ" ብሎት ይሔዳል፡፡ እንደ እምነቱም በጎቹ ተጠብቀዉለት ያገኛቸዋል፡፡ ሌላ ቀን ደግሞ "ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! አንተ ጠብቅልኝ" ይሏል፡፡ እንዲህ በቅዱሳን እያስጠበቀ ምሳውን በልቶ ይመጣል፡፡ አንድ ቀን፦ "እመበቴ ሆይ! ዛሬ አንቺ ጠብቂልኝ" ብሎ ወደ ቤቱ ይሔዳል፡፡ አባቱ አገኙትና፦ "ዛሬ ለማን አስጠብቀህ መጣህ?" አሉት፡፡ "ለእመቤታችን አስጠብቄ መጣሁ" አላቸው፡፡ እርሳቸውም፦ "አዪ! እርሷ'ማ ታስበላብሃለች" አሉት፡፡ "ለምን? ቅዱሳን፣ ጻድቃን፣ መላእክት የጠበቁትን እርሷ አትጠብቅምን? ይላቸዋል፡፡ "አይ ልጄ! የተጠማን ውሻ በወርቅ ጫማዋ ያጠጣች፡ የተራበ አውሬ መጥቶ ቢበላ ትከለክለዋለችን? ታስበላብሃለች" ሲሉት "እውነትም" ብሎ ወደ መንጎቹ ሮጠ ይባላል፡፡
ርህርህተ ሕሊና ሆይ! ዘወትር በምልጃሽ በቃል ኪዳንሽ ጠብቂን፡፡ አሜን!!!

#Samuel_Ayalneh.

🙏🙏🙏🙏መልካም ሰንበት 🙏🙏🙏🙏

Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
እንኳዕ ን ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል አብፀሓኩም አብፀሐና ::
ዛሬ በዳዊት ከተማ ኅፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና:አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም÷ኃያል:ድንቅ: መካር:የሰላም አለቃ የዘላአለም አባት ተብሎ ይጠራል፡፡
ማቴ ፪÷፩
መልካም በዓል
ጥር 7 - ቅድስት ሥላሴ

በዚህች ቀን ቅድስት ሥላሴ በኃጢያት የተገነባውን የሰናኦር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሶስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ቀን ነው፤ (ዘፍጥረት 11÷1) እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም አለ። "ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።" እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ። ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ ይላል።

“እግዚአብሔርም አለ” አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ኑ እንውረድ ሶስትነታቸውን፤ ሥላሴ በስም አአካል በግብር ሶስት ናቸው፤ የስም ሶስትነታቸው እንደምን ነው ቢሉ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፤ የግብር ሶስትነታቸውስ እንደምን ነው ቢሉ አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ፤ የአካል ሶስትነታቸውስ እንዴት ነው ቢሉ ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመሆኑ የሥላሴ ገጽ አካል ፊት እንደ ሰው ነውን ቢሉ አዎን እንደ ሰው ነው ነገር ግን የሰው ውሱን ጠባብ ፈራሽና በስባሽ ነው የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም በሰማይና በምድር በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ህያው ባህርይ ነው ኢሳ 66÷1። የሥላሴ አንድነታቸው በመለኮት በፈቃድ በስልጣን በምክር ወዘተ በመሳሰሉት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል
ጌታችን ለምን በውሃ ተጠመቀ?

እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)

አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
+ ኢየሱስ እናቱን ተቆጥቷት ይሆንን? +

የቃና ሰርግ ቤት ታሪክ ለጊዜው እናቆየውና አንድ ልጅ በአደባባይ በሰዎች ፊት እናቱን በምንም ምክንያት ቢቆጣ እንኳን ከሃይማኖት አንጻር ከሥነ ምግባርም አንጻር የሚደገፍ ሥራ አይደለም፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችን ‹እናቱን በቁጣ ተናገራት› የሚለው አስተሳሰብም እንዲሁ ብዙ የሚያመጣው ጣጣ አለ፡፡ ‹‹እናትና አባትህን አክብር›› ‹‹እናቱን የሰደበ ይሙት›› የሚለውን ሕግ የሠራ አምላክ ‹እኔን ምሰሉ› እያለ ለሰው ልጆች አርኣያ ሊሆን በመጣበት በዚህ ዓለም ራሱ እናቱን በአደባባይ በሰው ፊት ያቃልላታል ብሎ ማሰብ እጅግ ከባድና ለብዙ ሰዎች የኃጢአትን በር ወለል አድርጎ ከፍቶ መረን የሚለቅ ነው፡፡ (ዘጸ. ፳፥፲፪ ፣ ፳፩፥ )

እመቤታችንን የጎዱ መስሏቸው ‹ጌታ እናቱን ተቆጣ› ብለው የሚሰብኩ ሰዎችም ሳያውቁት እየተናገሩ ያሉት በእመቤታችን ላይ ሳይሆን በራሱ በጌታችን ላይ ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው?›› ብሎ የተናገረ ንጹሐ ባሕርይ ነው፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፮) ‹የሚጤስን የጧፍ ክር የማያጠፋ ፣ የተቀጠቀጠ ሸንበቆን የማይሰብር› በአነጋገሩ ጭምት ነው፡፡ ስንክሳሩም ‹‹ወንድሜ ምእመን ሆይ ጌታችን ለንጽሕት እናቱ ለድንግል ማርያም ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ጊዜዬ ገና አልደረሰም በማለቱ የክብርት እናቱን ቃል እንዳቃለለ አታስብ›› ይላል፡፡ (ስንክ. ጥር ፲፪ ቁ. ፵)

በማስከተልም ‹‹ጌታችን የሰማያዊውና የመለኮታዊ አባቱን ክብር እንደጠበቀ ይታወቅ ዘንድ እንዲሁ ከእርስዋ ፍጹም ሥጋንና ፍጽምት ነፍስን ነሥቶ ከመለኮቱ ጋር ያዋሐደውን የእናቱን ክብር ጠበቀ፡፡ በወንጌል ይታዘዛትና ይላላካት ነበር ተብሎ እንደተጻፈ›› ይላል፡፡ (ስንክ.ጥር ፲፪ ቁ. ፵፪)

በእርግጥም ጌታችን የባሕርይ አባቱን አብን ክብር እንደጠበቀ በራሱ አንደበት ‹‹አባቴን አከብራለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፱) ለእመቤታችንና ለአሳዳጊው ዮሴፍም እንዲሁ ‹‹ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ሉቃ. ፪፥፶፩) እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ስለ ወይኑ የነገረችውም የልጅዋን መታዘዝ በልብዋ ትጠብቀው ስለነበር እና እንደሚታዘዛት ታስብ ስለነበር ነው፡፡

እስቲ ነገሩን ሌሎች ከሚያዩበት ማዕዘን ለመመልከት እንሞክር፡፡ እውነት ግን ጌታችን እናቱን ሊቆጣ የሚችልበት ምን ምክንያት ነበረው? ከላይ እንደተመለከትነው የለመነችው ስለ ራስዋ ጥቅም አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ልመናዋ ከሚያስፈልግ ነገር ውጪ ይደረግ የተባለ አላስፈላጊ የቅንጦት ልመና አይደለም፡፡ በሰርግ ቤት ሙሽሮችን ለዕድሜ ልክ ውርደት ሊዳርግ የሚችል የወይን ጠጅ እጥረት በተከሰተበት ሰዓት ‹ወይን እኮ የላቸውም› ብሎ ማመልከት እንኳን በሩኅሩኁ አምላክ ፊት ይቅርና በእኛ በጨካኞቹ የሰው ልጆች ፊት እንኳን ሊያስቆጣ የሚችል ነገር አይደለም፡፡

የለመነችው እንደ አይሁድ ምልክት ለማየት ጓጉታ አይደለም፡፡ እንደ ፈሪሳዊያንና ሰዱቃውያን ‹አይተን እንድናምንህ ምን ምልክት ትሠራለህ?› ‹ከሰማይ ምልክት ልናይ እንወዳለን› የሚል የፈተና ጥያቄ አልጠየቀችም፡፡ (ማቴ. ፲፮፥፩ ፤ዮሐ. ፮፥፳) ተአምር የማየት ምኞት አድሮበት እንደጠየቀው እንደ ሄሮድስም በአጋጣሚው ልጠቀምና ተአምር ልይ ብላም አይደለም፡፡ (ሉቃ. ፳፫፥፰) ደግሞስ ያለ ወንድ ዘር በማኅጸንዋ አድሮ በታተመ ድንግልና ሲወለድ ያየች እናት ሌላ ምን ተአምር ሊያስደንቃት ይችላል?

የሰርጋቸው ቀን የኀዘናቸው ቀን ሊሆን ስለተቃረበ ሙሽሮች ተጨንቃ መለመንዋ እንዴት የሚያስቆጣ ሊሆን ይችላል? ያለጊዜው ስለለመነችውና ስለቸኮለች ተቆጣት እንዳንል ልመናዋን ትንሽ ብታዘገየው ኖሮ ነገሩ ይፋ እየሆነ ፣ ሙሽሮቹ መዋረዳቸው ነው፡፡ ስለዚህ የደረሰችው በሰዓቱ ነው፡፡

የጌታችን አሠራር እንዲህ አልነበረም፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስ አማት በንዳድ በታመመች ጊዜ እንዲፈውሳት ሲለምኑት እሺ ብሎ ንዳዱን ገሥፆ አላቀቃት፡፡ (ሉቃ.፬፥፴፱) የአንድ መቶ አለቃ ልጅ በታመመ ጊዜ የአይሁድ ሽማግሌዎች ሊያማልዱ በመቶ አለቃው ተልከው መጡ፡፡ ጌታችን ከይሁዳ ነገድ መሆኑን በማሰብም ‹‹ይህን ልታደርግለት ይገባዋል፤ ሕዝባችንን ይወዳልና ምኵራብም ራሱ ሠርቶልናል ብለው አጽንተው ለመኑት። ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ።›› የመቶ አለቃውንም ልጅ በመጨረሻ ፈወሰው፡፡ (ሉቃ. ፯፥፪-፮) እነዚህ ሰዎች ተአምር እንዲያደርግ ሲጠይቁት እሺ ያለ ጌታ እናቱ ስትለምነው ይቆጣል ብለን እንዴት እንቀበል? የአይሁድን ሽማግሌዎች እንኳን ያልተቆጣውን ጌታ በምን አንደበታችን እናቱን ተቆጣ ልንለው ይቻለናል?

ከሁሉ በላይ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን›› እንዳለው በረከሰ አንደበታችን ፣ በሚወላውል ልባችን ፣ በሚባክን ሃሳባችን ወደ እርሱ የምንጸልየውን የእኛን የኃጢአተኞቹን ጸሎት ለምን ጸለያችሁ ብሎ ያልከለከለ አምላክ ንጽሕት እናቱ በፍጹም ትሕትና ለለመነችው ልመና የቁጣ ምላሽ ሠጠ ማለት እንዴት እንደፍራለን? ዳዊት ‹‹በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ›› ብሏል፡፡ እርሱ በልቡ በደል ስለሌለ ጌታ ከሰማው በሃሳብዋ ድንግል የሆነች እናቱን እንዴት አልሰማትም እንላለን? (መዝ. ፷፮፥፲፱-፳)

እመቤታችን የጠየቀችው ይህን ያህል የማይጠየቅ ነገር ነው እንዴ? የመንግሥትህን እኩሌታ ፣ የሥልጣንህን ፈንታ ሥጠኝ አላለችውም፡፡ የጠየቀችው ስለ ድሆቹ ሙሽሮች ነው፡፡ እኛ በረባ ባልረባው ስንዘበዝበው የምንውለውና የምናድረው ታጋሽ አምላክ ለእናቱ ለእኛ የሠጠውን ነገር ይነሣል ማለት ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ ‹አብን አሳየንና ይበቃናል› ፤ ‹እሳት ከሰማይ ወርዶ ሕዝቡን ያጥፋቸው› ፤ ‹በግራ ቀኝህ አስቀምጠን› የሚሉ ደቀ መዛሙርትን ታግሶ ለሦስት ዓመት ከሦስት ወራት ያስከተለ ጌታ ቅድስት እናቱ ተገቢ ልመና በተገቢ ሰዓት ስትለምነው ሊቆጣ አይችልም፡፡

እንደ ወንጌሉ ብቻ ከሔድን ደግሞ እመቤታችን ከዚህ በፊትና በኋላ ምንም ነገር ስትለምነው አልተጻፈም፡፡ በወንጌል ለተጻፈው ለዚህ ብቸኛ ልመናዋም መልሱ ቁጣ ነው ብለን አምነን መቀመጥ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ፈጽሞ የሚዋጥልን ሃሳብ አይደለም፡፡ በልጅነትዋ ወልዳው ለተሰደደችው ፣ በነፍስዋ የኀዘን ሰይፍ ላለፈባት እናቱ አንዴ ብትለምነው ተቆጣ ብለን እንዴት እንናገራለን?

ጌታችን በዚህ ሰርግ ቤት እንኳንስ እንዲህ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የሚተረጉመው ‹ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ› የሚል የአክብሮት ንግግር ተናግሮ ቀርቶ ፤ ለእናቱ የተናገረው በቀጥታና በግልፅ የቁጣ ንግግር ቢሆን ኖሮ እንኳን ጾመን ጸልየን ፣ ወድቀን ተነሥተን ምሥጢራዊ ትርጉሙን እንፈልጋለን እንጂ ሰማይና ምድር ቢነዋወጥ ‹ጌታ እናቱን ተቆጣ› ብለን አናምንም!!!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ቃና ዘገሊላ ገጽ 81
" ሰው ብቻ አትሁኑ"

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ

" ሰው ብቻ አትሁኑ...ሰው ብቻ ማለት ምንድን ማለት ነው? ብዬ ሳስብ፤ የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ በሚለብሰው ልብስ፣ በሚነዳው መኪና የኑሮን ስኬት የሚለካ ማለት ነው? እስከ ሞት የሚኖር ማለት ነው? እንደ እንስሳ። "...ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል "ሰው እግዚአብሔር ሲለየው" ይላል። ሰው እግዚአብሔር ሲለየው፤ ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሔር ሆኖ ይቀራል። በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ ሲምካርዱ የወጣ ሞባይል(mobile ) ማለት ነው ። ጥሪ የማይቀበል፤ ለጉትቻ ማንጠልጠያ ብቻ የተሰራም ጆሮ አለ።"...እኔ በዕውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ ዐይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት የሰዉ አስተሳሰብ ነው።... የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል። ጃፓንና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን አልምተው ነው። አስተሳሰቡ ያልለማ ሕዝብ የለማውን ያወድማል።"
"ቤታችሁ ገብታችሁ እንድታጤኑት ነው። እነዛ. (ምንትስ) የምንላቸው ክርስቲያኖችን አርደዋል... ምዕራባውያኑ ደግሞ ክርስትናን እራሱን አርደውታል።....ወንድ ለወንድ፣ ሴት ለሴት፣ በቤተክርስቲያናቸው እያጋቡ፤ ክርስትናን አጋድመው ያረዱ ምዕራባውያን ናቸው። (ይህን ሁሉ ያመጣውም) የምዕራባውያን ልክ ያጣ ነጻነትና ገደብ ያለፈ ዝርክርክነት ነው።" "እንደምታዩት እኔ ዐይነ ስውር ነኝ። ቀላል አይደለም.... እንክዋን ዘውትር ዓይን አጥቶ አንድ ቀን መብራት ሲሄድ ስንት እንደምታማርሩ ታውቅታላችሁ። አንድ ቀን ግን አልቅሼ አላውቅም። ከሞት ወዲያ መብራት አለ። ከመቃብር በላይመብራት አለ። ... ወደ መቃብር ሲወርድ ማንም ዓይነ ስውር ነው። ማንም ዐይኑ እያየ የተቀበረ የለም። ተስፋችን ግን ምንድን ነው? ከሞት ወዲያ ሕይወት አለ። ከሞት ወዲያ ብርሃን አለ።"
"...አንድ አንድ ጊዜ እመኛለሁ። የማይረባ ነገር ስናይ (ዓይናችንን) የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር... መልካም ነገር እስክናይ ድረስ ለጊዜው የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር። "አሁን እንደው ጆሮ በካርድ የሚሰራ ቢሆን ሐሜት እንሰማ ነበር?(ከፍተኛ ሳቅ)... የምንፈልገውን (ብቻ) አውርተን ስዊች ኦፍ እናደርገው ነበር። ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደ አለ። "ጀርመን ሀገር ሄጄ ሲነግሩኝ፤ ባለ አምስት ኮከብ የውሻ ሆቴል አለ ተባለ። እኛ ሀገር አምስት ኮከብ ሆቴል ገብተው የበሉ ትንሽ ዝና (ሀብት) እና ትንሽ ሥልጣን ያላቸው ናቸው። ማን ይገባል ከነሱ ውጪ። ግን ሰዋች ነን። የጀርመን ውሻ ዛሬም ውሻ ነው ለዘላለምም ውሻ ነው። እኛ ግን ሰው ነን። እንደ ሰው አስቡ (ምዕመናን) በማርያም።" "...የንጉሠ ነገሥቱ የክርስቶስ አልጋ ወራሾች ነን... የደስታችሁ ልኬት የደስታችሁ ሚዛን ምግብና መጠጥ አይሁን፤ መኪናና ቤት ዝናንም አታርጉ። እኛ መለኪያችን
ጽድቅ ነው። መለኪያችን መንግሥተ ሰማያት ነው። ያ የምንገባበት ቤት ደግም የተዋበ፣ የደመቀ፣ መብራት ውሀ የማይሄድበት፤ 24 ሰዓት ክርስቶስ የሚያበራበት፤ 24 ሰዓት የሕይወት ውሀ የሚጠጣበት፤ ሀብታም፤ ደሀ፣ ተራ ሰው የማይባልበት፣ እገሌ ግባ እገሌ ውጣ የማይባልበት ቦታ ነው።
ሁላችንንም የመንግስቱ ወራሽ ያድርገን።
ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ ክርስቶስ የሰጠህን ስጦታ ላልተፈረገ ግብር አታውለው፡፡ እጅን የሰጠህ እንድትሰርቅበት ሳይሆን ትእዛዛቱን እንድትፈጽምበት፣ በጎ ምግባርን እንድትሠራበት፣ ለጸሎት እንድትነሣበት፣ የወደቁትን እንድታነሣበት ነው፡፡ ጆሮን የሰጠህ ተርታ ወሬን እንድትሰማበት ሳይሆን ቃሉን እንድታደምጥበት ነው፡፡ አንደበትን የሰጠህ እንድትሰድብበትና እንድትረግምበት ሳይሆን እንድትዘምርበት፣ እንድታመሰግንበት፣ እንድትመክርበት ነው፡፡ እግርን የሰጠህ ወደ ክፋት ሳይሆን ወደ በጎ ስፍራ እንድትፋጠንበት ነው፡፡ ሆድን የሰጠህ ለመብል ሳይሆን ጥበብን እንድትማርበት ነው፡፡ ፈቲውን የሰጠህ እንድታመነዝርበትና እንድትዳራበት ሳይሆን ልጆችን ትወልድበት ዘንድ ነው፡፡ ልቡናን የሰጠህ ሰዎችን እንድትወቅስበት ሳይሆን እውነትን ታውቅበት ዘንድ ነው፡፡ ገንዘብንና ጉልበትን የሚሰጠን ሰማያዊ ቤታችንን እንድንሠራበት ነው፡፡ ...እንኪያስ የክርስቶስን ስጦታ በአግባቡ ተጠቀምበት፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ