የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
ት ማስመስከሪያ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከዚያ በኋላ ወደ አከሱም ተመልሶ በመደባይ ታብር በተባለ ቦታ ቅዳሴያትን በዜማ አዘጋጅቷል፡፡ ይህ ቦታ ከአከሱም 15 ኪ.ሜትር ርቆ ይገኛል፡፡ ከዚህ በኋላ
ለመጨረሻ ጊዜ አኩስምን ተሰናብቶ ለመሄድ ወደ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገባና «ቅድስት ወብጽዕት ስብሕት ወቡርክት
ክብርት ወልዕልት አንቀጸ ብርሃን ማዕርገ ሕይወት» እያለ አንቀጸ ብርሃን የተባለውን ድርሰቱን ሰተት አድርጎ አዘጋጀው፡፡
ይህንን ድርሰት ሲያዜም አንድ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ብሎ ይታይ ነበር ይባላል፡፡
ቅዱስ ያሬድ በሰሜንና ወገራ፣ አገውና በጌምድር እየተዘዋወረ አስተምሮ ከሰሜን ተራራዎች ውስጥ እየጾመና
እየ[ለየ በብሕትውና ለብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ በሰሜናዊ ምሥራቅ በኩል ባለው በጸለምት ዋሻ ውስጥ በ571 ዓ.ም
ግንቦት 11 ቀን ተሠውሯል፡፡ ይህ ቦታ በተለምዶ የሰሜን ተራሮች በሚባለው ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛና ብርዳማ ቦታ
ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊ ዜማን ከማበርከቱም ሌላ በትምህርት ሂደትም አስተዋጽዖ
አድርጓል፡፡ የድጓን፣ የጾመ ድጓን የዝማሬ መዋሥዕትንና የቅዳሴን ትምህርት ከማስተማሩም በላይ ለቅኔ ትምህርትም
መሠረት ጥሏል፡፡ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
መናፍቃን

መናፍቅ የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን ,,ናፈቀ,, ተጠራጠረ አጠራጠረ ከፍሎ አመነ ማለት ነው
መናፍቅ የሚለውን ቃል ኪዳነ ወልድ ክፍሌ እንድህ ይተረጉሙታል
በግሪክ ኤፌቲክ
በእንግሊዘኛ ሄሬቲክ
በግዕዝ ደግሞ ሐራ ጥቃ =
መናፍቃን በየዘመናቱ የተለያዪ ስያሜዎች ተሰቷቸዋል
#በዘመነ ነቢያተት=ነቢያተ ( 1ኛ ነገ 13:11)
#በዘመነ ክርስቶስ
ጠላት የጠላት ልጅ (ማቴ 13:39)
#በዘመነ ሐዋርያት
ቢጸ ሐሳዊያን (የውሸት ወንድሞች)
#በዘመነ ሊቃውንት
መናፍቃን ተብለዋል::

፠መንፍቅና እንደት ተጀመረ ?
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
መናፍቅና የተጀመረው በሁለት መንገድ ነው
1ኛ/በጥንቆላ
ጥንቆላ ፈጣሪን የሚአሳዝን እጅግ አጸያፊ ተግባር ሲሆን ምንፍቅና ለመጀመሪያ የመጣውም በዚሁ ሥራ ነው
በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው መናፍቅ Simon ሲሞን ይባላል::
በሐዋሥ 8:9 ላይ ታሪኩን እናገኘዋለን
ይህ ሰው ሐዋርያት ተአምር ሲሰሩ ሲያይ አመንኩ ብሎ ተጠመቀ
ከዚያም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በገንዘብ ለመግዛት የሞከረ ሰው ነበረ::
በመጨረሻም በመተቱ ምልክት እያሳየ
በብሉይ ኪዳን እንደ አብ
በሐድስ ኪዳን እንደ ወልድ
በባአለ ሃምሳ እንደ መንፈስ ቅዱስ ሆኜ የተገለጥኩ እኔ ነኝ ይል ነበር
ከዚያም የእርሱ ተከታዮች በቤተ ክርስቲያን ላይ ብዙ ጉዳት አድረሰዋል
2ኛ/በፍልስፍና
ክርስቶስ በተገለጠበት ዘመን ግሪክ በፍልስፍና የታወቀችበት ዘመን ነበር
ግሪኮች እራሳቸውን እንደጥበበኛ አድርገውም ይመለከቱ ነበር
ቅዱስ ጳውሎስም
" የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ"
(1ኛቆሮ 1:22)ያላቸው ለዚህ ነው
እነዚህ ሰወች እውቀታዊ ሃይማኖት
Gnostic Religion በመፍጠር
ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያንን ተዋግተዋታል
እነዚህ ሰዎች ግንስቲክ ሲባሉ አስተምህሯቸውም ግኖስቲዝም Gnosticismይባላል::
ሲያስተምሩም
ክፉና ደግ ሁለት አማልክት አሉ
ክፉው አምላክ ክፉትን ፈጠረ
ደጉ አምላክ ደግ ደጉን ፈጠረ ይሉ ነበር
የክፉውም ሆነ የደጉ ትንንሽ አማልክት ልጆች አሏቸው
ከደጉ አምላክ ልጅ አንዱ ትንሹ አምላክ ክርስቶስ ነው ለማለት ኤኑስ Aeons ይሉት ነበር
ዛሬ ያሉ መናፍቃን
ወልድን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ማሳነስ ከእነዚህ የተማሩት ነው
ይህ ብቻ አልነበረም ክርስቶስ አልተሰቀለም አልሞተም ይሉም ነበር
ይህንን Substitutions theory የምትክ ጽንሰ ሃሳብ ከእነርሱ #በሒራ ሰርጁስ የተባለ ካቶሊካዊ መነኩሴ በሰባተኛው መክዘ ለተነሳው ለእስልምና መስራች ለነቢዩ #መሐመድ አስተማራቸው
እርሳቸውም #በቁራናቼው በሱራ አል ኒሳ 4:157 ""እኛ የአላህን መልክተኛ የመሬምን ልጅ አል መሲህ ኢሳን ገደልን በማለታቸው እረግመናቸዋል አልገደሉትም አልሰቀሉትም ነገር ግን ለእርሱ የተሰቀለው ሰው በኢሳ ተመሰለ ""በማለት የዓለምን ድኅነት ከንቱ የሚአደርግ ሃሳብ አስቀመጡ
በአጠቀላይ ስለ ኃጢአት ስለ ነፍስና ሥጋ ስለ ድኅነት
የግኒስቲኮች አስተምህሮ በጣም የተወሳሰበ ነው
ይህንና የመሳሰለውን አስተምህሯቸውን በእውነተኞቹ ሐዋርያት ስም መጽሐፍ በመጻፍ ኑፋቄያቸውን በማስገባት ብዙ ደክመዋል::
ለምሳሌ
የበርናባስ ወንጌል የጴጥሮስ ወንጌል የሚባሉት ጥቂቶቹ ናቸው
ቤተ ክርስቲያን እነዚህን የኑፋቄ መጽሐፍት ከደኖቹ መጽሐፍት ለመለየት
200 ዓመት ፈጅቶባታል::
ይህ አስተምህሮ በዘመኑ በነበሩት ሁለት የአንጾኪያና የእስክንድርያ የቴኦሎጅ ትምህርት ቤቶች በመግባቱ
ከዚህ አስተምህሮ አየተጎነጪ የመጡ ብዙ መናፍቃን ናቸው
ብዙዎቹን ለመጥቀስ ባልችልም የታወቁትን ለመግለጽ ያክል
1ኛ/#አርዮስ
አርዮስ በሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሊቢያ የተወለደ ቄስና በአንጾኪያ የተማረ ሰው ::
ይህ ሰው ከፍልስፍናው ኑፋቄ ቀድቶት በመጣው ትምህርት ወልድን ፍጡር ያለ ሰው ነው
ክርስቶስ በባህሪ metaphysical የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም በጸጋ የጸጋ አምላክ ነው ይል ነበር::
በመጨረሻም እርሱንም አስተምህሮውንም 325 ዓ.ም 318ቱ ሊቃውንት በኒቅያ አውግዘውታል
የእርሱን አስተምህሮ እንደገና በማደስ እነ#ቻርልስ ራስል የጀሆቫን እምነት መሠረቱ::

2ኛ/ #ንስጥሮስ
ንስጥሮስ 428-431 ዓ.ም የነበረ የቁስጥንጥንያ ዛሬ ኤስታፑል ቱርክ ሊቀ ጳጳስ ነበር
ይኽ ሰው ክርስቶስን ሁለት አካል ነው
ሰዉአዊ አካልና አምላካዊ አካል አለው የሚኖረው በተዋህዶ ሳይሆን ተደራርቦ ነው ይል ነበር::
እመቤታችንም ወላአዲተ አምላክ Theotokos አትባልም ይል ነበር
በመጨረሻም 431 ዓ.ም በኤፌሶን ተወገዘ::
3ኛ/#ሄሊቪዲየስ
ይኽ ሰው 4ኛው መቶ ዓመት የነበረ ሮማዊ ሰው ነው
ይኽ ሰው
የድንግልና ህይወት ምንም ጥቅም የለውም ያለና
ለመጀመሪያ ጊዜ የመቤታችን ድንግልና የተቀወመ ከክርስቶስ ሌላ ሌላ ልጅ አላት ብሎ ያለ መናፍቅ ሲሆን በጊዜው የነበሩት አባ ሄሮኒመስ (ጄሮም)ለዚህ አድስ ኑፋቄ መልስ በመመለስ አፉን ዘግተውታል::
4ኛ/ #ማርቲን ሉተር
ይህ ሰው አሁን ያለውን ፕሮቴስታት ኑፋቄ መስራች ነው
ይኽ ሰው 1483 ዓ.ም አይስሌበን በተባለች ስፍራ በጀርመን የተወለደ ሲሆን ጣዖት አምላኪ የነበረ ሰው ነው
ይኽ ሰው ከሐዋርያት አስተምህሮ እየራቀች የሠጣችውን የካቶሊክን እምነት በመቃወምና የሮማ ካቶሊክ አገዛዝ ያንቀጠቀጠውን ህዝብ በማሰባሰብ በመጨረሻ 95 (Ninety five theses)የተቃውሞ ነጥቦችን በዊተንበርግ በይፋ ለጠፈ::ዕምነቱም ፕሮቴስታት ተባለ፠
ይቀጥላል

ከዲያቆን ገብረክርስቶስ ካሳ
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ
(ሚያዝያ 23 እረፍቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥር 20 ቀን በ277 ዓ.ም ተወለደ። ሀገሩ ፍልስጤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይባላል። ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት ነው። አባቱ ዞሮንቶስ የተባለ የልዳ መኳንንት እናቱ ቴዎብስታ ትባላለች። ማርታና እስያ የሚባሉ እህቶች ነበሩት። 10 ዓመት ሲሞላው አባቱ ስለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ከቤቱ ወስዶ አሳደገው። በጦር ኃይልም አሠለጠነው። ሃያ አመት ሲሞላው መስፍኑ የ15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እርሷን አግብቶ ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ጌታ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ። እርሱም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሄደ።
በቤሩት ደራጎንን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል። ወደፋርስ ቢመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ሲሰግድ ሲያሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖቱ ቀናዒ ነውና ከቤተመንግስቱ ገብቶ “እኔ ክርስቲያን ነኝ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ” አለው። እርሱም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ “አንተማ የኛ ነህ በ10 አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ” አለው። ቅዱስ ጊዮርጊስም “ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክድም” አለ። በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት እርሱ ግን “ይህን ከሀዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ”በማለት እግዚአብሔርን የለመነና እንደጸሎቱ የተደረገለት። በእምነቱም ጽናት የሰው ልጅ ሊሸከም የማይችለውን መከራ የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው።
ከእነዚህም መከራዎች ውስጥ፡-
1. በእንጨት አስቀቅሎ ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶት ሂድ አለው። ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል። በሰባ (70) ችንካር አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ። ሥጋውን በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነስንሶበት ሥጋው ተቆራርጦ ወደቀ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ “ገና 6 ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣ 3 ጊዜ ትሞታለህ፣ በ4ኛው ታርፋለህ።” አለው።
2. ዱድያኖስ ደንግጦ “የሚያሸንፍልኝ ቢኖር ወርቅ እሰጠዋለሁ” ቢል አትናስዮስ የተባለ መሰርይ ከንጉሱ ላምን በጆሮዋ ሲያንሾካሹክባት ለሁለት ተሰንጥቃ ገድሏት ፈቃድን ተቀበለ። ሆድ በጥብጦ አንጀት ቆራርጦ የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞ ሰጠው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል። ጠንቋዩም ማረኝ ብሎት ከእግሩ ወደቀ። መመለሱን አይቶ የቆመባትን መሬት በእግሩ ረግጦ ውሃን አፍልቆ ወደ ጌታችን ቢያመለክት ሐዋርያው ቶማስ በመንፈስ መጥቶ አጥምቆት ጥር 23 ቀን አንገቱን ለሰይፍ ሰጥቶ በሰማዕትነት አርፏል። እሱን ግን በመንኮራኩር አስፈጭቶ ከትልቅ ጉድጓድ ጥሎት ደንጊያ ዘግቶበት አትሞበት ሄዷል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተፈጨውን ሥጋ በእጁ ዳስሶ መንፈሱን መልሶ አንስቶታል፤ ተመልሶም “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” ብሏቸዋል።
3. በብረት አልጋ አስቸንክሮ ከበታቹ እሳት አንድዶበታል። እሳቱም ደሙ ሲንጠባጠብ ጠፍቷል። ዱድያኖስ “ኢየሱስ አምላክ መሆኑን አሳየኝ” ቢለው የለመለሙትን ዕፅ አድርቆ፣ የደረቁትን አለምልሞ፣ ከሞቱ 430 ዓመት የሆናቸውን ሙታንን አስነስሰቶ አሳይቶታል። ነገር ግን ልቡ ክፉ ነውና በረሀብና በጽም ይሙት ብሎ ምንም ከሌላት መበለት ቤት አሳስሮታል። እርሷም የሚቀመስ ስትፈልግ ቤቷን በእህል አትረፍርፎ የታሰረበት ግንድ አፍርቶ ልጇ ጆሮው የማይሰማ ነበርና ፈውሶላት መበለቲቷን ከነልጆቿ አጥምቆ ቅዱስ ሚካኤል ከእስራቱ ፈትቶት ተመልሷል። ዳግም በመንኩራኩር ፈጭታችሁ ደብረ ይድራስ ወስዳችሁ ዝሩት ብሎ አስፈጭቶ ሥጋውን ቢዘሩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ “ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር፣” እያሉ አመስግነዋል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነስቶታል። ሔዶም “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” አላቸው። ጭፍሮቹ ደንግጸው ከእግሩ ስር ወደቁ። ከመሬት ውሃ አመንጭቶ ቅዱስ ዮሐንስ አጥምቋቸዋል።
4. “ንጉሡ ልሹምህ ለአጵሎን ስገድ” ብሎ ቢለምነው እሺ ብሎ ገብቶ ሲጸልይ የንጉሱ ሚስት እለእስክንድርያ “ምን እያልክ ነው?” ብትለው አስተምሯት አሳምኗታል። ሲነጋ ንጉሱ በአዋጅ ህዝብን አሰብስቦ “ጊዮርጊስ ለጣዖቴ ሊሰግድ ነው’ ብሎ በተሰበሰበ ህዝብ መካከል አንድን ብላቴና (የመበለቷን ልጅ) “የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ጊዮርጊስ ይጠራሃል” በል ብሎ ወደጣዖቱ ቢልከው ጣዖቱ ላይ ያደረው ሰይጣን እየጮኸ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለበት ቦታ መጣ፤ አምላክ አለመሆኑን አናዞት መሬት ተከፍታ እንድትውጠው አደረገ። ብዙ ሰዎች ይህንን ተዓምር አይተው አመኑ። ንጉሱን ሚስቱ እንዲመለስ ብትነግረው በአደባባይ አሰቅሎ አሰይፏት ሞታለች ደሟን ጥምቀት አድርጎላት ሰማዕት ሆናለች። በመጨረሻም በሰይፍ እንዲመተር አስደረገ። ቅዱስ ጊዮርጊስም ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን ተገብቶለት በ27 ዓመቱ በሚያዝያ 23 ሰማዕት ሆኗል። አንገቱ ሲቆረጥም ውሃ፣ ደም እና ወተት ወጥቷል።
ከሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከት ይክፈለን!!!
(ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ)
(በሶሎሞን።አያሌው) https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
† “ንብ የምትሞተው መቼ ነው?” †
የጥበበኛ ነፍስ መገለጫዋ ይሄ ነውና ሁል ጊዜ የምታመሰግኑ ሁኑ፡፡ ክፉ ደረሰባችሁን? ይህስ እናንተ ከፈቀዳችሁ ክፉ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜ አመስግኑ፤ ክፉ የሆነባችሁም መልካም ይሆንላችኋል፡፡ ከተወደደው ኢዮብ ጋር ሆናችሁ “የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን” እያላችሁ አመስግኑ /ኢዮብ.1፡21/፡፡
እስኪ ንገሩኝ! ደረሰብኝ የምትሉት ክፉ ነገር ምንድነው? በሽታ ነውን? ታድያ ይሄ እኮ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥጋችን መዋቲና ለስቃይ የተጋለጠ ነውና፡፡ ሀብት ንብረት ማግኘት አለብኝ የሚል መሻት ነውን? ታድያ ይሄ እኮ ምግኘት የሚቻል ነው፤ ካገኙት በኋላ ግን መልሶ የሚጠፋና በዚህ ዓለም ብቻ የሚቀር ነው፡፡ ከወንድሞች የሚደርስ ሐሜትና የሐሰት ወቀሳ ነውን? ታድያ ተጐጂዎቹ’ኮ የሚያሙንና በሐሰት የሚመሰክሩብን እንጂ እኛው አይደለንም፡፡ “ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ ትሞታለች” እንዲል ተጐጂዎቹ ይህን ኃጢአት የሚሠሩት እንጂ እኛው አይደለንም /ሕዝ.18፡4/፡፡ ተጐጂው ምንም በደል ሳይኖርበት ክፉ የሚደርስበት ሰው ሳይሆን ክፉ የሚያደርሰው ሰው ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምዉት በሆነ ሰው ልትቈጡ አይገባም፤ ከዚያ ይልቅ ከሞት ይድን ዘንድ ልትጸልዩለት ይገባል፡፡ ንብ መቼ እንደምትሞት አይታችሁ ታውቃላችሁን? የምትሞተው ሌላውን ስትናደፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚህች ፍጥረት በወንድሞቻችን ላይ ልንቈጣ እንዳይገባ ያስተምረናል፡፡ እኛው የምንቈጣ (የምንናደፍ) ከሆነ ግን ቀድመን የምንሞተው እኛው ነን፡፡ ስንቈጣቸው የጐዳናቸው ይመስለን ይሆናል፤ ነገር ግን እንደዚያች ንብ ተጐጂዎቹ እኛው ነን፡፡…
© ከ "ሰማዕትነት አያምልጣችሁ" መጽሐፍ የተወሰደ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ይነበብ

በትንሽ ድንጋይ እስክትመታ አትጠብቅ!!

የኮንስትራክሽን ተቆጣጣሪው ከ 6ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ የሚስራውን ሰራተኛ ይጠራዋል፣ ስራተኛው ሊስማው አልቻለም፡፡ ስራተኛው የአሰሪውን ጥሪ ሊስማው ስላልቻለ ተቆጣጣሪው መላ ዘየደ፡፡ እናም የሰራትኛውን ሃሳብ ልማግገኘት ሲል ተቆጣጣሪው ከላይ ብር ጣለለት ብሩም ከሰራተኛው እግር ስር አረፈ፣ ሰራተኛው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አሰገብቶ ስራውን ቀጠለ…… በድጋሜ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት ተቆጣጣሪው መጀመሪያ ከጣለው ብር በላይ ሌላ ብር ጨምሮ ጣለለት፣ የቀን ሰራተኛውም ልከ እንደ መጀመሪያው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አስገብቶ ስራውን ቀጠለ፡፡ በመጨረሻ ሌላ መላ ዘየደ ብር በመጣል የሰራተኛውን ሀሳብ ማግኘት ስላልቻለ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት አነስ ያለ ድንጋይ አነሳና ወደ ሰራተኛው ወረወረው፣ ድንጋዩም የሰራተኛውን ጭንቅላት አገኝው በዚህ ሰዓት ነበር ሰራተኛው ወደ ላይ የተመለከተው እና ከተቆጣጣሪው ጋር መነጋግር የጀመረው፡፡ : : ይሄ ታሪክ ከእኛ ህይወት ጋር ይመሳሰላል ፈጣሪ ከኛ ጋር መገናኘት ይፈልጋል ነገር ግን እኛ በጣም በ አለማዊ ስራ ራሳችንን ጠምደናል ከዛ ፈጣሪ ትንሽ ስጦታ ይሰጠናል እኛም ስራችንን እንቀጥላለን ከየት እንዳገኘነው ቀጥ ብለን ለማየት ጊዜ የለንም፡፡ በድጋሜ ፈጣሪ ከመጀመሪያው የተሸለ ስጦታን ይሰጠናል አሁንም ልክ እንደ መጀመሪያው ስጦታውን ወስደን ምስጋናም ለፈጣሪ ሳናቀርብ እድልኞች ነን ብቻ ብለን ስራችንን እንቀጥላልን ከየት እና ከማን እንዳገኘነው ቀና ብለን ለማየት አንሞክርም፡፡ እናም በትንሽ ድንጋይ ስንመታ፣ ማለት ትንሽ ችግር ቢጤ ስታገኘን ወደ ላይ ማየት እና መጮህ ከዚያም ከፈጣሪ ጋር መነጋገር እንጀምራለን፡፡ ስለዚህ ምንግዜም በህይወታችን ስጦታን ስናገኝ በፍጥነት ፈጣሪን ማመስገን አለብን በጭራሽ በትንሽ ድንጋይ እስክንመታ መጠበቅ የለብንም ሁሌም ቢሆን ከፈጣሪ ጋር እንገናኝ፡፡
#እግዚአብሔር ፍቅር ነው
#እግዚአብሔር መልካም ነው
#እግዚአብሔር የልብን መሻት ይፈፅማል
#ግን እስኪ ልክ እደ ሰራተኛው ድንጋይ እስኪጣልብን አንጠብቅ እውነት የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር እኮ መልካም ነው ምህርቱ ብዙ ነው https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
(1875 - 1928)

* ልጅነትና አስተዳደግ
~~~~~~~~~~~
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም. ሰላሌ ላይ (በፍቼ ከተማ) ተወለዱ። ገና ህፃን ሳሉ ዘመዶቻቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ወስደው ከባህታዊ ተድላ ትምህርት ቤት አስገቧቸው። በዚያም ለጀማሪዎች የተመደበውን የቤተ ክህነት ትምህርት እየተማሩ አደጉ። ስማቸው ኃይለማርያም ነበር።

* በትምህርት ቤት
~~~~~~~~~~
ገና ወጣት ሳሉ ቅኔ ተምረው ተቀኙ። እንደገናም ወደ ዋሸራ ሄደው ለመምህርነት የሚያበቃውን ትምህርት ፈፅመው ለቅኔ አስተማሪነት ተመረቁ። ጥቂት ዘመን በጎንደር ዜማ ቀፀሉ። ከዚያም በኋላ ወሎ (ቦሩ ሜዳ) ላይ ከታላቁ ሊቅ መምህር አካለ ወልድ ብሉያትንና ሐዲሳትን ሊቃውንትንም አካሄዱ። በ19 መቶ ዓ.ም. ከምስካበ ቅዱሳን ገዳም (አማራ ሳይንት) ገብተው 9 ዓመት ቅኔና መፃህፍትን አስተማሩ።

* ምንኩስና
~~~~~~~
በ1909 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኮሱ። ወዲያው ማዕርግ ቅስና ተቀብለው በቤተ መቅደስ ተልእኮ ያዙ። በ1910 ዓ.ም. ለደብረ መንክራት ገዳም መምህር ተብለው ከደብረ ሊባኖስ ተሾሙ። በ1916 ዓ.ም. በዝዋይ ደሴት የገዳሙ መምህር ሆኑ። በ1919 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥት የግርማዊነታቸው አበ ንሰሃ ሆኑ።

* ጵጵስና
~~~~~
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (ግርማዊ ንጉሥ ተፈሪ እየተባሉ ሳለ) በ1921 ዓ.ም. አራት ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በእስክንድርያ በቅዱስ ማርቆስ መንበር ባለው ፓትርያርክ ጵጵስና እንዲሾሙ ባደረጉ ጊዜ ከተመረጡት መነኮሳት አንደኛው መምህር ኃይለ ማርያም ናቸው። በግንቦት 13 ቀን የጵጵስናውን ማዕርግ ሲቀበሉ ስማቸው ጴጥሮስ ተብሎ ተሰየመ።
ከኢትዮጵያ አውራጆች የደረሳቸው ሀገረ ስብከት መንዝና ወሎ ነበር።
. . . . .
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ:

ተወዳጆች ሆይ! ትዘምራላችሁ፡፡ [ከጸሎታቱ ትሳተፋላችሁ፡፡ ቅዳሴውን አስቀድሳችሁ] እምነታችሁን ትመሰክራላችሁ፡፡ ይህን ኹሉ አድርጋችሁ ስታበቁ ግን አትቆርቡም፡፡ ለምን? ከሰማያዊው ማዕድ የማትሳተፉት ለምንድን ነው? አንዳንዶቻችሁ፡- “እኔ ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ ልቆርብ አይገባኝም” ብላችኋል፡፡ እንዴ! እንደዚህ’ማ ካላችሁ ከመዝሙሩም፣ ከጸሎታቱም፣ ከቅዳሴውም ልትሳተፉ አይገባችሁማ!

እስኪ ንገሩኝ! የንጉሥ ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ መላእክት “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” እያሉ የሚያመሰግኑት የሚያገለግሉትም ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ ንጉሡ በፊታችሁ አለ፡፡ ታዲያ እናንተ እንዲሁ ቁልጭልጭ እያላችሁ ትቆማላችሁን? ልብሳችሁ አድፎ ተዳድፎም ሳለ ምንም እንዳልተፈጠረ ኾናችሁ ወደ ቤታችሁ ትመለሳላችሁን?

ወደ መንግሥተ ሰማያት፣ ወደ ሰማያዊው ንጉሥ ማዕድ ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠርቶን ሳለ ተዘጋጅተን እንደ መቅረብ ወደ ኋላ እንላለንን? እንደዚህ የምናደርግ ከኾነ ታዲያ ተስፋ ድኅነታችን ምንድን ነው?

“መቅረብ ያልቻልኩት’ኮ” ብለን ደካማ መኾናችንን እንደ ሰበብ ማቅረብ አንችልም፡፡ ተፈጥሮአችንን እንደ ምክንያት ማቅረብ አንችልም፡፡ እንዳንቀርብ የሚያደርገን ደካማ መኾናችን አይደለም፡፡ አዎን ከሰማያዊው ማዕድ እንዳንሳተፍ የሚያደርገን እንዲሁ ሳንዘጋጅ ልል ዘሊላን ኾነን መቅረባችን እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት አይደለም፡፡

ስለዚህ እማልዳችኋለሁ! [ንስሐ ገብተን እንደ ቸርነቱም ተዘጋጅተን] በፍርሐትና በረዓድ ኾነን [በግድ] እንቅረብ እንጂ “ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ” ብለን አንራቅ፡፡ [ከኃጢአት ኹሉ የሚያነጻን የክርስቶስ ደም እንጂ ኃጢአተኛ ነኝና አይገባኝም ብለን መራቃችን አይደለምና፡፡] ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ በድፍረት ወደ እርሱ መቅረብ ይቻለን ዘንድ ዛሬ በፍርሐትና በረዓድ ኾነን ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡ ያኔ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” ከሚላቸው ጋር ዕድል ፈንታችን ፅዋ ተርታችን በመንግሥተ ሰማያት ይኾን ዘንድ ዛሬ ወደ ሰማያዊው ማዕድ እንቅረብ

ከ ሃና አለም https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ቅዱስ ያሬድ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከመሰከረው ምስክርነት በጥቂቱ
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

1) ቅድስት ድንግል ማርያም በአምላክ ኅሊና ታስባ ስለመኖሯ ካስተማረው
በባሕርዩ ኹሉን የሚያውቅ ምንም የማይሰወረው ምንም የማይሳነው የባሕርይ አምላክ ልዑል አምላክ በኋላ ዘመን ሥጋን ተውሕዶ ዓለምን እንደሚያድን በባሕርይ ዕውቀቱ ቀድሞዉኑ የሚያውቅ ነው፤ ሥጋዌዉ በርሱ ከታወቀ ሥጋዋን ተውሕዶ ሰው የሚኾነው ከቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ናትና ለደኀሪ ልደቱ እናቱ ርሷ እንደኾነች ቅድመ ዓለም በኅሊናው የሚያውቃት ናትና ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የቅድስት ድንግል ማርያምን በአምላክ ኅሊና የመታሰቧን ነገር በድጓው ላይ እንዲኽ አላት፦
“ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር ወዘእንበለ ይሣረር ምድረ ገነት ሀለወት ስብሕት ቅድስት ወቡርክት ይእቲ ማርያም እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ጽዮን ቅድስት እሞሙ ለሰማእት ወእኅቶሙ ለመላእክት”
(የመላእክት እኅታቸው የሰማዕታት እናታቸው ቅድስት ጽዮን የክርስቲያን ሰንበት የተባለች የተመሰገነች በንጽሕና በድንጋሌ የተለየች ርሷ ማርያም ሰማይና ምድር ሳይፈጠር የገነት ምድር መሠረት ሳይጣል ነበረች)

2) ቅድስት ድንግል ማርያም በአምላካዊ ጥበብ ከመርገመ ሥጋና ከመርገመ ነፍስ ተጠብቃ የኖረች ንጽሕት ዘር ስለመኾኗ፦
ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ እንዲኽ መሰከረ፡-
“ማርያምሰ ተሐቱ እምትካት ውስተ ከርሡ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዐዳ”
(ማርያምስ ከጥንት ዠምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች)
በማለት ዕንቈ ባሕርይ ክርስቶስን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች፤ ዐዲስ መዝገብ የተባለች ቅድስት ድንግል ማርያም አዳም አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስን በመብላቱ ምክንያት ከመጣበት የሥጋና የነፍስ መርገም በጌታ ጥበብ ተጠብቃ የኖረች መኾኑን ሲገልጥ እንደ ነጭ ዕንቊ ታበራለች ብሏል፡፡
ምስጢሩም ይኽቺን ነጭ ዕንቊ ከደፈረሰ ባሕር ውስጥ ቢጥሏት እንኳን የደፈረሰው ባሕር የርሷን ጥራት ሳይለውጥ በደፈረሰው ባሕር ውስጥ ሳለች አብርታ እንድታይ ኹሉ፤ ልክ እንደ ዕንቁዋ ቅድስት ድንግል ማርያምም በአዳም ትእዛዝ መተላለፍ ከመጣ መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ በአምላካዊ ጥበብ ተጠብቃ፤ በንጽሕናና በቅድስና ጸንታ የተገኘች መኾኗን ሊቁ በጒልህ ገልጾታል፡፡

3) ቅዱስ ያሬድ የእመቤታችንን ውበት በመጽሐፍ ብቻ ሳይኾን ቅዱስ ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ አስከትላ በመምጣት ተገልጻለት አይቷታልና እንዲኽ ይላታል፡-
☞ ☞ “እምሥርወ እሴይ ሠሪጻ ወእምዘርዐ ዳዊት ተወሊዳ ታዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ ወከመ ሮማን መላትሒሃ፤ ኅብስተ ሕይወት በየማና ወጽዋዐ ወይን በፀጋማ ጸሎታ ወስእለታ ይኩነነ ወልታ”
(እመቤታችን ከእሴይ ባሕርይ ወጥታ፤ ከዳዊት ዘር ተወልዳ፤ ሰውነቴ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች አለች፤ ከንፈሮቿ እንደ ፍሕሶ አበባ ቀይ ናቸው፤ ጉንጮቿም እንደ ሮማን ናቸው፤ የሕይወት እንጀራ በቀኝዋ በጽዋ ውስጥ ያለ ወይንም በግራዋ አለ፤ ጸሎቷ ልመናዋ ጋሻ ይኹነን) (መጽሐፈ ዝማሬ)
☞ ☞ “ነጽሩ ሊተ ድንግለ ኅትምተ መዐዛ አፉሃ ይጼኑ ዕፍረተ”
(የአፏ እስትንፋስ እንደ መልካም ሽቱ የሚያውድ የታተመች አዳራሽ ድንግልን እዩልኝ) (መጽሐፈ ድጓ)፡፡
☞ ☞ “ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ንባብኪ አዳም ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍርኪ፤ መዐዛ አፉሃ ከመ ኮል ኢሳይያስኒ ይቤላ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ሰሎሞን ይቤላ እምአርምሞትኪ አዕይንትኪ ዘርግብ”
(መልካማዪት ርግቤ ድንግል ሆይ ነዪ፤ አነጋገርሽ ያማረ ነው፤ ከንፈርሽ እንደ ፍሕሶ (ቀይ) አበባ ነው፤ የአፏ መዐዛ እንደ እንኮይ ነው፤ ኢሳይያስም ዐዲሲቱ ዕንቦሳ ይላታል፤ ሰሎሞንም ከዝምታሽ የተነሣ ዐይኖችሽ የርግብ ዐይኖችን ይመስላሉ አላት) (መጽሐፈ ድጓ)
☞ ☞ “ርግብ ዘመክብብ ማርያም በብሩር ዘግቡር አክናፊሃ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ ወከመ ኮል መዐዛ አፉሃ፤ ወከመ ሮማን ቂሐተ መላትሒሃ ሶበ አእመረ ዮሴፍ ንጽሐ ሥጋሃ ሰገደ ላቲ ወአምኃ”
(ክንፎቿ በብር የተለበጡ የመክብብ የሰሎሞን ርግብ ማርያም ከንፈሮቿ እንደ ፍሕሶ አበባ ቀይ ናቸው፤ የአፏ መዐዛም እንደ እንኮይ ነው፤ የጒንጯ ቅላትም እንደ ሮማን ቅርፍት ነው፤ አረጋዊ ዮሴፍ ንጽሐ ሥጋዋን ባወቀ ጊዜ ሰግዶ ሰላምታ አቀረበላት) (መጽሐፈ ድጓ)
☞ ☞ “እግዝእትየ ቃልኪ ሠናይ ሐሊብ ወመዓር ይውሕዝ እምታሕተ ልሳንኪ፣ ቆምኪ ሠናይ ወገጽኪ ልሑይ ይሤኒ እምኲሎን አንስት፤ ቃል ቅዱስ አይኅአ እምሰማይ ተሠገወ እምኔኪ፤ እንዘ እሳት እግዚአ ኲሉ ዓለም ኀደረ ውስተ ከርሥኪ ዋዕየ መለኮት ተጸውረ በማሕፀንኪ”
(እመቤቴ ንግግርሽ መልካም ነው፤ ወተትና ማር ከአንደበትሽ ይፈስሳል፤ ቁመናሽ መልካም ነው፤ ፊትሽም የወዛ ነው፤ ከሴቶች ኹሉ ያምራል፤ አካላዊ ቅዱስ ቃል ከሰማይ ወርዶ ከአንቺ ሥጋን ተዋሐደ፤ የዓለሙ ኹሉ ጌታ እሳት ሲኾን በማሕፀንሽ ዐደረ የመለኮት ዋዕይ በማሕፀንሽ ተወሰነ) (መጽሐፈ ድጓ)
እያለ ሊቁ ማሕሌታይ በመንፈስ ተቃኝቶ እንዲኽ ይመሰክርላታል፤ አይ መታደል! አይ መባረክ! ለካ ቤተ ክርስቲያናችን እንደነዚኽ ያሉ ሊቃውንትን የወለደች ናት!
የቅዱስ ያሬድ እመቤት ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ይደርብን፨
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ፨

እንኳን ለእመቤታችን የልደት ቀን የሆነው ዐመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
እመቤታችን ተወለደች ማለት ጌታ ሊወለድ 15 ዓመት ቀረው ፣ የዘመኑ ፍጻሜ ደረሰ ማለት ነበር። እግዚአብሔር ሃና እና ኢያቄምን ሳይወልዱ ያዘገያቸውም ለዚህ ታላቅ ክብር እንዲበቁ ነበር። ክርስቶስ ፀሐይ ከሆነ የዛሬው ዕለት ሰማይዋ የተዘረጋችበት ዕለት ነው። ክርስቶስ የሕይወት ውኃ ከሆነ ዛሬ ምንጭዋ የፈለቀችበት ዕለት ነው። ወንጌል በመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ይላል። በእመቤታችን መወለድ ምን ያህል ሰዎች ደስ ይላቸው ይሆን? የእመቤታችን ልደት በብዙ ሀገራት ብሔራዊ በዓል ሆኖ ይከበራል። እኛም በሊባኖስ ተራሮች (አድባረ ሊባኖስ) መወለድዋን በማሰብ ከደጅ ወጥተን ቅድም አያቶችዋ በጨረቃ ተመስላ በህልማቸው ያዩአትን የጨረቃችንን (በግሪኩ ሶልያና) ልደት ጨረቃን እያየን እናከብራለን። የልደትዋ ቀን ልደታችን ነው!
እንኳን ለእመቤታችን ልደት በሰላም አደረሳችሁ።
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
አላማህን ለማሳካት ያለህን አቅም ሁሉ ተጠቀም!-;

አባትና ልጅ በጫካ ውስጥ በመጓዝ ላይ ሳሉ ልጁ አባቱን ጥያቄ ይጠይቀዋል። "አባቴ ይህን ዛፍ ብገፋው ቅርንጫፎቹን ማነቃነቅ አልችልም?" አለው። "እንዴታ! ሙሉ አቅምህን ተጠቅመህ ከሞከርክ የማትችለው ነገር የለም።" ሲል መለሰለት። ልጁም ሙከራውን ጀመረ። ይሁንና ግን ዛፉ ትልቅ በመሆኑ ቅርንጫፎቹን ሊወዘውዝ አልቻለም።
"አባቴ ተሳስተሀል። እኔ ይህን ማድረግ አልችልም" አለው።
"እንደገና ሞክር!" አለው አባቱ።
ልጁ የቻለውን ያህል ዛፉን ቢገፋም ቅርንጫፎቹ አልነቃነቅ አሉ። ብዙ ሞከረ ግን አልሆነም። "አባቴ አልችልም!" አለው ተስፋ በመቁረጥ።
አባቱም "ልጄ አቅምህን በሙሉ ተጠቀምና ሞክር ነበር ያልኩህ ግን አላደረከውም" ሲል መለሰለት።
"ከዚህ በላይ?" ልጁ ግራ ተጋባ።
"አዎ! እኔን መች ለእርዳታ ጠየከኝ?" ሲል ልጁ ያልጠበቀውን ምላሽ መለሰለት።
**********************
በዙሪያችን ያሉትን አማራጮች፣ እድሎች፣ ድጋፎች፣ ተስፋዎች፣ ብርታቶች...ሳንጠቀም አንድ ነገር "አልተሳካልኝም!" ብለን ተስፋ መቁረጥ አይገባንም። ማንም በራሱ ሙሉ አይደለም። ድጋፍ ይፈልጋል፣ እርዳታ ይፈልጋል። በሌላው ተስፋ አለመቁረጥ ውስጥ፣ በሌላው ብርታት ውስጥ፣ በሌላው መጽናናት ውስጥ ሀይላችንን ልናገኘው እንችላለን። .......እርዳታ የጠየቅናቸው ሰዎች ባይተባበሩን የተሳሳተ ሰው መጠየቃችንን እንጂ፣ ወይም አጠያየቃችንን መለወጥ እንዳለብን እንጂ፣ ወይም በሌላ ጊዜ መጠየቅ እንዳለብን እንጂ እርዳታ መጠየቃችን ነውር ነው ማለት አይደለም። በዙሪያችን ያለውን እድል ሁሉ አሟጠን መጠቀም ለህልማችን መሳካት መሰረት ነው።
ከ ዲ/ን ማቴዎስ ተሾመ
Join us
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ይቅር_ባይነት

ይቅር ባይነት ከታላላቅ ክርስትያናዊ ተግባራት አንዱ ነው።በእግዚአብሔርና በስው ፣ እንዲሁም በሰውና በሰው
መካከል ላለ ግንኙነት መሠረት ይቅር ባይነት ነው። እግዚአብሔር እኛን ከጥንት ከመጀመሪያው ጀምሮ ስንበድለው በይቅር ባይነቱ ይቅር ባይለን ኖሮ የህልውናችን ሁኔታ እጅግ ከባድና አሳሳቢ ይሆን ነበር ።
" እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን
ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።በነፍሳችሁ ዝላችሁ
እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ።ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም"(ዕብ 12፥1-4) ሕጉን ስናፈርስ ፣ ከእርሱ ይልቅ የዲያብሎስን " አምላክ ትሆናላችሁ" ባዶ ስብከት ስናምን ፣ ሰውነታችንን በተለያየ ኃጢአት ስናጎሳቁል፣ እግዚአብሔር ቸር መሐሪና ይቅር ባይ
ስለሆነ ይቅር ይለናል። ይህ የእርሱ ይቅር ባይነት አንዳችን ከሌላችን ጋር ላለን ግንኙነትም መሠረታችን ሊሆን ይገባል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ ፥ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው ይቅር
ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።"( ቆላ 3፥13)
እንዳለን እኛም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ኃጢአት ይቅር ብሎ ለእኛ ሲል በፈቃዱ መከራን በመቀበል እንደ
ሞተልንና በደላችንንም ይቅር እንዳለን ሁሉ እኛም ማንም የበደለን ቢኖር ይቅር ማለት ይኖርብናል። " እርስ በርሳችሁም
ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።"(ኤፌ 4:32) ተብለናልና።
ምናልባት ደግመው ደጋግመው የሚበድሉን ሰዎች ቢኖሩ እነርሱን ስንት ጊዜ ይቅር ማለት እንደሚገባንም ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንን ጠየቀው።"በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።ኢየሱስ እንዲህ አለው። እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።አለው። ይህም ይህን ያህል ጊዜ ብቻ ይቅር እንድንባባልና ከዚ በኋላ ይቅር አልልም እንድንል
ሳይሆን ያለ ምንም ገደብ ይቅርታ ልናደርግ እንደሚገባ የሚገልጽ ነው።"(ማቴ18፥21-22) እግዚአብሔር መጠን በሌለው ይቅርታ እኛን ይቅር እንደሚለን ሁሉ የክርስቲያንም ይቅርታው በቁጥር የሚወሰን ስላልሆነ
የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን ካለ ምን ጊዜም የሚበድሉንን ይቅር ልንል እንችላለን ። ጌታችንና መድኃኒታችን
ለሰው ካለው ፍቅርና ከሩኅሩኅነቱ የተነሣ ምንም ብንበድለው እንኳን
" ኢየሱስም። አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት።"(ሉቃ23:34) በማለት ኃጢአታችንን ይቅር ብሎ በፈቃዱ በመስቀል ላይ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ አዳነን " ስለ ብዙዎች
ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።"(የማቴ 26:28)እንዳለን ።
ንጹሕ ባሕርይ የሆነው እርሱ የእኛን በደል ይቅር ካለን ፣ ኃጢአተኞች የሆንን እኛ እንደ እኛ ደካሞች የሆኑ የወገኖቻችንን
በደል ይቅር ማለት ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔር ለይቅርታ ዝግጁ የሆነ ልቡናን ይስጠን https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
እንኳን ለባእታ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ::
ቅድስት አርሴማ ሰማዕት ዘአርማንያ

የቅድስት አርሴማ ወላጆች አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትናትያስ ይባላሉ:: በፈሪሃ እግዚአብሔር በአምልኮ ጸንተው በሕጉ ተመርተው የኖሩ ደጋግ ሰዎች ናቸው:: ልጅ አጥተው መካን ሆነው ሲኖሩ ዘር እንዲሰጣቸው ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር:: እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ ደም ግባቷ ያማረ መልከ መልካም የሆነች እንደ ጸሐይ የምታበራ ልጅ ሰጣቸው፡፡ ቅድስት አርሴማ የነበረችበት ዘመን ዘመነ ሰማዕታት ይባላል::

ዲዮቅልጥያኖስ የሮም ቄሳር ሆኖ የነገሰበት (እኤአ ከ284ዓ/ም - 305 ዓ/ም) : አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉበትና አብያተ ጣኦታት ተከፍተው ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስም ልዩ ልዩ መከራና ሰማዕትነት የሚቀበሉበት ዘመን ነበር:: ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ” እንዳለ ዕብ 11:35-37 ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ሔደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ ሠራዊቱን በየሀገሩ ሰደደ። ይህች ቅድስት አርሴማ በሮሜ ሀገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ከሌሎች ማኅበረ ደናግል ጋር ነበረች:: እየፈለጉ ሲሄዱ እሷን አይተው ሥዕሏን ሥለው ወስደው ሰጡት። መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል ሄዳችሁ አምጡልኝ አላቸው። እርሷም በመንፈስ አውቃ እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ እንጂ ከአረማውያን ጋር አንድነት የለኝም ብላ ከ39 ደናግል ጋር ወደ አርማንያ ተሰደደች::
ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም: ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ሰምቶ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ አስፈልገህ ላክልኝ ብሎ ላከበት። ንጉሥ ድርጣድስ ደናግሉ ከተሰወሩበት አስፈልጎ አገኛት። እሱም የቅድስት አርሴማን መልከ ቀናነቷን አይቶ ይህችንስ አሳልፌ አልሰጥም ብሎ መሪያቸው አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት። እሷም አይሆንም ያልሁ እንደሁ ጸብ አጸናለሁ ብላ እሺ አለችው እሷን ግን ለመንግሥተ ሰማያት የታጨሽ ነሽና ይህ እንዳያረክስሽ እወቂ ብላ ልቧን አስጨከነቻት። ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ቀላቀለችው። እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለነበር በታናሽ ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ:: ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት:: ከዚህ በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው (እመምኔት) አጋታ ጋር በሰይፍ አስመትቷቸዋል። ሥጋቸውም በተራራ ጫፍ ላይ እንዲጣል ተደረገ፡፡
ሰማዕታት ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ:: ወዳጆቹም በዳነልን እያሉ ሲጨነቁ የታዘዘ መልአክ መጥቶ እኅቱን ከጎርጎርዮስ በቀር የሚያድነው የለም አላት። ንጉሥ ድርጣድስ የአርማንያውን ሊቀጳጳስ ቅዱስ ጎርጎርዮስን በሃይማኖት ምክንያት ተጣልቶ ከአዘቅት ጉድጓድ ውስጥ አስጥሎት ነበርና የሞተ መስሏቸው ደነገጡ። እርሱ ግን መልአኩ ለአንዲት መበለት ነግሮለት ምግቡን እየጣለችለት ይኖር ነበርና ምናልባት አምላኩ ጠብቆት ይሆናል ብለው ገመድ ቢጥሉ መኖሩን ለማሳወቅ ገመዱን ወዘወዘው። ቢጎትቱት በ15 ዓመቱ ከሰል መስሎ ወጥቷል የንጉሡ እኀት ወንድሜን አድንልኝ አለችው። ቅዱስ መጀመሪያ አጽመ ሰማዕታትን አሳዩኝ ብሎ አሳይታው ያን አስቀብሮ ካለበት ሄዶ ባድንህ በፈጣሪዬ ታምናለህን? አለው። ግዕዛኑን ፈጽሞ አልነሳውም ነበርና በአዎንታ ላሱን ነቀነቀ። የተደረገለትን እንዳይዘነጋ ከእጁ ከእግሩ የእርያ ምልክት ትቶ ጸልዮ አድኖታል። አመንኩ አጥምቀኝ አለው ለማጥመቅስ ሥልጣን የለኝም አለው። በአንጾኪያው ሊቀጳጳስ ተጠመቀ። እሱንም ሊቀጳጳስነት አሹሞት ብዙ ተግሳጻት ጽፎ ብዙ ድርሳናትን ደርሶ ብዙ የቱሩፋትን ሥራ ሠርቶ አርፏል። ዕረፍቱ ታሕሣስ 15 ቀን ነው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን: እኛንም በእናታችን በቅድስት አርሴማ አማላጅነት በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን: በረከታቸውም ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ::
ተወዳጆች ሆይ! አንድ እንግዳ ወደ ቤታችን ሲመጣ ቤታችንን እንደምን እንደምናሰናዳው ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ሁላችንም እንግዳችንን ደስ የሚያሰኘው ነገር ለማድረግ የምንቻኰል አይደለንምን? ለእንግዳችን የሆነ ነገር ባናደርግለት፥ እንግዳችን በመምጣቱ ደስ ተሰኝተን እርሱን ደስ የሚያሰኝ ነገር ባናደርግለት፥ ግን ደግሞ በመምጣቱ ደስ እንደተሰኘን ብንነግረው እንግዳችን በፍጹም አያምነንም፡፡ በእንግዳችን መምጣት ደስ እንደተሰኘን ከቃላት ባለፈ በገቢር መግለጥ አለብንና፡፡ እንኪያስ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወታችን ከመጣ ደስ መሰኘታችንን በገቢር ልንገልጽ ያስፈልጋል፡፡ እንግዳችን ክርስቶስን የሚያስቈጣ ነገር ልንፈጽም አይገባንም፡፡

እንግዳ ሲመጣ ቆሻሻ ልብስ አይለበስም፡፡ እንግዳ ሲመጣ የሚያስጸይፍ ነገር አይነገርም፡፡ ክርስቶስ በሕይወታችን ውስጥ እንዲኖር ስንፈልግም ቆሻሻ ልብሳችንን (ማንነታችንን) አውልቀን ልንጥል ያስፈልጋል፤ አስጸያፊ ነገራችንን ልንተው ያስፈልጋል፡፡ እንግዳ ሲመጣ ቤት ያፈራው ሁሉ ይቀርብለታል፡፡ ክርስቶስ ወደ ቤታችን ሲመጣም የሚበላ ነገር ልናቀርብለት ይገባል፡፡ ለመሆኑ የክርስቶስ መብል ምንድነው? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጥያቄ ሲመልስልን እንዲህ ብሏል፡- “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው” ዮሐ.፬፡፴፬፡፡

እንኪያስ ክርስቶስ የራበው ይኸው ነውና እንመግበው፤ ኢየሱስ የጠማው ይኸው ነውና እናጠጣው፡፡ እርሱም ይቀበለናል፡፡ አንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ብንሰጠው እንኳ ይቀበለናል፡፡ ስለብዛቱ ሳይሆን ስለፍቅሩ ብሎ ይቀበለናል፡፡ እኛን ስለመውደዱ ይቀበለናል፡፡ የምንወደው ሰው የሰጠነውን የሚቀበለን ስለ መጠኑ አይደለም፤ ስጦታው የወዳጅ ስለሆነበት እንጂ፡፡ ሰው ወዳጁ ጌታም ሁለት ሳንቲም ብንሰጥ እንኳ ብዙ እንደሰጠን አድርጐ ይቀበለናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጦታችንን የሚቀበለው ድሃ ስለሆነ አይደለም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድሃውም የባለጸጋውም ስጦታ እኩል የሚቀበለው ስለ ልቡናችን ኀልዮት እንጂ ስለ ስጦታው ትልቅነት ወይም ዋጋ አይደለም፡፡ ስለዚህ ክርስቶስን እንደምንወደው ለመግለጽ የግድ ብዙ ወይም በውድ ዋጋ የተገዛን ስጦታ መስጠት አያስፈልገንም፡፡ ስጦታችን እርሱ ወደ እኛ ስለመጣ ደስ የመሰኘታችን መግለጫ ነውና ስለ ስጦታችን መጠን ልንመለከት አይገባም፡፡

ቅዱስ  ዮሃንስ አፈወርቅ
†††አባ መርትያኖስ ዝሙትን እንዴት ድል እንዳደረገ†††

አባ መርትያኖስ በትኅርምቱና በቅድስናው የታወቀ ገዳማዊ አባት ነው፡፡ እንዲሁ ደግሞ በዝሙትና በክፉ ሥራዋ የታወቀች አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ይህች ሴት ስለ አባ መርትያኖስ ቅድስና ስትሰማ ስለ እርሱ ጻድቅነት የሚያወሩትን ‹በዱር ስለሚኖር ነው እንጂ ሴት ቢያይ ኖሮ ይስት ነበር፤ የኔን ውበት ቢያይ በዝሙት ይወድቅ ነበር› ስትል ሞገተቻቸው፡፡ ክርክራቸው አድጎ ‹አስተዋለሁ ፣ አታስችውም› በሚል ተወራረዱና በመጨረሻም በውርርዱ ካሸነፈች ገንዘብ ሊሰጡአት ተስማሙ፡፡ ጌጦቿን ፣ ልብሶቿንና ሽቱዎቿን ይዛ ወደ ቅዱሱ በዓት ሔደች፡፡ እስኪመሽ በአካባቢው ቆየችና እንደመሸ በሩን አንኳኩታ ‹የሩቅ መንገደኛ ነኝ አውሬ እንዳይበላኝ ያሳድሩኝ› ስትል ጠየቀችው፡፡ አባ መርትያኖስም ‹እምቢ ብል አውሬ ይበላታል፣ ባስገባት በዝሙት ልፈተን ነው፣ ምን ይሻላል› ብሎ ከራሱ ጋር ከመከረ በኋላ አስገባትና በዓቱን ትቶላት ሌላ ቦታ ፈቀቅ አለ፡፡ እርሷ ግን የዝሙት ልብሷን ለብሳ ፣ በጌጦቿ ተኳኩላና አጊጣ እንዲሁም ሽቱዋን ተቀብታ ወደርሱ ሔደች፤ ልታስተውም አፍ አውጥታ ‹ማንም የሚያየን የለም› አለችው፡፡ አባ መርትያኖስም የሰይጣን ፈተና መሆኑን ተረድቶ ‹ቆይ አንድ ጊዜ› ካላት በኋላ ታላቅ እሳትን አንድዶ እግሩን ከውስጡ ጨመረበት፡፡ ነፍሱንም ‹የሲዖልን እሳት የምትችዪ ከሆነ ኃጢአትን ሥሪ> አላት፡፡ በዚህ ጊዜ ሴቲቱ ደንግጣ ከእሳቱ ጎትታ ቅዱሱን አወጣችው፡፡ ወደ ንስሐም ተመለሰች፤ ልብሷንና ጌጧን ሁሉ ጣለች፡፡ ስለ ነፍሷ ድኅነትም እንዲረዳት ከእግሩ ሥር ተደፍታ ለመነችው፡፡ እርሱም አስተምሮ ሴቶች ገዳም እንድትገባ አደረጋት፤ ሴቲቱም እስከ ሕይወት ፍጻሜዋ ጸንታ ኖረች፤ የፈውስ ጸጋም ተሰጥቷት ብዙዎችን ትፈውስ ነበር፡፡
†††
አባ መርትያኖስ ከዚህ በኋላ ድጋሚ በዝሙት እንዳይፈተን ሰው ወደሌለበት ሩቅ ቦታ ለመሔድ ተመኘ፡፡ በባሕር መካከል ወዳለች ወደ አንዲት ደሴትም ገብቶ ብዙ ዓመታትን በተጋድሎ ኖረ፡፡ ሆኖም በአንድ ወቅት አንድ መርከብ በማዕበል ተሰባብሮ ሰጥሞ በውስጡ ከነበሩት ተጓዦች አንዲት ሴት ብቻ ስባሪ እንጨት ይዛ እየተንሳፈፈች ተረፈች፡፡ የተረፈችውም አባ መርትያኖስ የነበሩበት ደሴት ላይ በማረፍ ነበር፡፡ እርሱም ሴቲቱን አስተምሮ አመነኮሳትና ‹አብረን መኖር አይገባም› በማለት ደሴቱን ትቶላት ራሱን ባሕር ውስጥ ወረወረ፡፡ የታዘዘ አሳ አንበሪም ውጦት የብስ ላይ ተፋው፡፡ ከዚህ በኋላም አንድ ቦታ እንዳይቀመጥ የሚዞር ሆነ፤ በመቶ ስምንት አገሮች የሚገኙ ገዳማትንም ጎበኘ፡፡
†††
አባ መርትያኖስ በልጅነቱ በአንድ አረጋዊ ቅዱስ እጅ ከመነኮሰ በኋላ ሐመረ ኖህ ወደምትባል ገዳም ገብቶ ብዙ ተጋድሎን አድርጓል፡፡ ስድሳ ሰባት ዓመት በመጋደሉም ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት ብዙዎች በቅድስናው እንዲያውቁት ሆኗል፡፡ የዕረፍቱ ጊዜ በቀረበ ጊዜም በአንድ በዓት ተወስኖ ነበር፤ ስለ ገድሉም ኤጲስቆጶሱን ጠርቶ ነግሮታል፡፡ ኤጲስቆጶስም ስለ ቅዱሱ ዕረፍት ተገልጦለት ስለነበር ከዕረፍቱ በኋላ ገንዞ ቀብሮታል፡፡ ዕረፍቱም ግንቦት 21 ቀን ነው፡፡ በየካቲት 19 ደግሞ ሥጋቸው ወደ ሀገረ ሙላዳቸው ፈልሷል።†††

የአባ መርትያኖስ በረከት በሁላችን ላይ ይደር፡፡ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
[የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት]
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ነገረ ክርስቶስ ክፍል አንድ ከሚለው 622 ገጾች ካሉት መጽሐፌ በጥቂቱ የተወሰደ
የባሕርይ አምላክ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ለሐዋርያት መጽሐፈ ኪዳንን እያስተማራቸው ለ፵ ቀናት በምድር ላይ ቆየ:: ስለምን ፵ ቀናት ቆየ ቢሉ?
፩ኛ. ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አለማድረጉ መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ነው ብለው እንዳያስቡ ሲኾን፤
፪ኛ. አዳም በተፈጠረ በ፵ ቀኑ አግኝቶ ኋላ በምክረ ከይሲ ያጣውን የጸጋ ልጅነትን እንደመለሰለት ለማጠየቅ ለ፵ ቀናት ለሐዋርያት እየተገለጸ መነሣቱን ሲያስተምራቸው ከቈየ በኋላ በ፵ኛው ቀን ኹሉንም ወደ ቢታንያ አውጥቶ በአንብሮተ እድ ባርኮ የሥልጣነ ክህነትን ጸጋ ሰጥቷቸው በክብር በምስጋና ዐርጓል፡፡
፫ኛ በአርባ ቀናት ፅንሱ ተስዕሎተ መልክዑ ተፈጽሞለት ሙሉ እንዲኾን የእግዚአብሔርም ልጅ ሐዋርያቱን በእምነት ፍጹም አደረገ፤ በአርባ ቀናት የአዋጁን መንገድ ፍጹም አደረገ፤ እስትንፋስን ያይደለ መንፈስ ቅዱስን በሐዋርያቱ ላይ እፍ አለባቸው (ዮሐ ፳፥፳፪) እንዲል (ቅ. ያዕቆብ ዘሥሩግ)
ከዚያም “አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኀይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ” ብሎ አዝዟቸው፤ እስከ ቢታንያ ድረስ አውጥቶ በደብረ ዘይት እጆቹን አንሥቶ በአንብሮተ እድ ሥልጣነ ክህነትን ሾማቸው፡፡ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳ፣ በሰማርያ ምስክሩ እንደሚኾኑት ነግሯቸው፤ መጋቢት ፳፱ እሑድ ዕለት እንደተነሣ፤ ዕርገቱን ደግሞ በዕለተ ኀሙስ ግንቦት ፰ አድርጎታል፡፡
ለምን በዚኽ በግንቦት ወር ወደ ሰማይ ዐረገ? ቢሉ
ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በዚኽ ወር የጽድቅ ፀሓይ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ማረጉን ከፀሓይ አኪያኺያድ ጋር እያስተባበረ በጥልቅ ሃይማኖታዊ ዕውቀቱ እንዲኽ ይተነትነዋል፡-
“ርሱ ጌታ በካኑን (በታኅሣሥ) ወር ወረደ (ተወለደ)፤ ልክ ፀሓይ በዚኽ ወራት ከቦታዋ ከምሕዋሯ ዝቅ እንድትል፤ በግንቦት ወር ዐረገና በብርሃኑ ጨለማን አጠፋው፤ በብርሃን ወር ፀሓይ ከፍ ወደ አለ ቦታዋ (ምሕዋሯ) ከፍ ከፍ ትላለች፤ በርሷም አንጸባራቂው (አማናዊዉ ብርሃን) ወልድ እየተመሰገነ ከፍ ከፍ አለ (ዐረገ)… በግልጽ ለሚመለከታት በመንገዷ ላይ ፀሓይ የእግዚአብሔርን ልጅ መውረድና ማረግ ታሳያለች፤ በታኅሣሥ ወር ልደቱ ነው፤ በርሷም ፀሓይ እጅግ ዝቅ ትላለች፤ ደማቁ ፀሓይ ወደ ምድር መውረዱንም ታውጃለች፤ እንደገናም በወርኀ ግንቦት ፀሓይ በምሕዋሯ ከፍ ከፍ ብላ በመውጣት የብርሃንን ነገር ገልጣ በማሳየት ምስጉን መሲሕ በዚኽ ወራት ማረጉን ትገልጣለች” እንዲል (ቅ. ያዕቆብ ዘሥሩግ በእንተ ዕርገተ እግዚእ)
ጌታችን ዐርጎ በአባቱ ቀኝ የመቀመጡን ነገር ወንጌላዊዉ ማርቆስ “ወእግዚእነሰ ኢየሱስ እምድኅረ ተናገሮሙ ዐርገ ውስተ ሰማይ ወነበረ በየማነ እግዚአብሔር አቡሁ” (ጌታ ኢየሱስም ካነጋገራቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱ በእግዚአብሔር ቀኝም ተቀመጠ) ይለናል (ማር ፲፮፥፲፱)፡፡
ምሉእ በኲለሄ ለኾነው ለእግዚአብሔር ቀኝ ግራ፤ ላይ ታች ያለው ኾኖ አይደለም፤ ሊቁ ሕርያቆስ ስለዚኽ ነገር፡-
አኮ ዘቦቱ ለመለኮት ግድመ ወኑኅ ላዕል ወታሕት የማን ወፀጋም አላ ምሉዕ ውእቱ እንተ በኲለሄ ወበኲሉ” (ለመለኮት ወርድና ቁመት፤ ላይና ታች፤ ቀኝና ግራ ያለው አይደለም በኹሉ የመላ ነው እንጂ) ብሏል፡፡
በመኾኑም ቀኝ የተባለው ዕሪና፣ መተካከልን፣ ኀይልን፣ ሥልጣንን የሚያመለክት አገላለጥ ኾኖ እናገኘዋለን፡፡ ሊቃውንትም “እስመ ብሂለ የማን ይመርሕ ኀበ ተዋሕዶቶሙ በክብር” እንዲሉ፤ “የማን” (ቀኝ) የባለቤትነት፤ “ነበር” (ተቀመጠ) የሥጋ እንግድነት ሲኾን፤ አንድም “ነበረ” (ተቀመጠ) ማለት ቅሉ የባለቤትነት ነው፤ እንግዳን “ንበር” (ተቀመጥ) ይሉታል እንጂ “ነበረ” (ተቀመጠ) እንዳይሉት ይላሉ፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እንደ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ስለ ጌታችን ዕርገት እያራቀቀ እንዲኽ ይተነትነዋል፡-
☞ “ወእንዘ ይመስሕ ምስሌሆሙ ለአርዳኢሁ በደብረ ዘይት አንበረ እዴሁ ላዕለ አርዳኢሁ…” (በደብረ ዘይት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲመገብ እጁን በደቀ መዛሙርቱ ላይ አኖረ፤ እያንዳንዳቸውንም ባረካቸው ከዚያም የእሳት ደመና ተቀበለው፤ ከእነርሱም ሰወረው፤ በጨርቅ የጠቀለሉት ይኽ ሥጋ በኪሩቤል ክንፎች ተጋረደ፤ በጒልበት ያቀፉት ይኽ ሥጋ በእሳት ሠረገላ ተቀመጠ፤ በዚኽ ዓለም የተራበና የተጠማ ይኽ ሥጋ እኽል መብላት፤ ወይን መጠጥን ውሃም መጠጣት ወደ ማይሻበት ወደ አርያም ከፍታ ወጣ፤ በሊቀ ካህናቱ አገልጋዮችና በጲላጦስ አደባባይ ራቁቱን የቆመ ይኽ ሥጋ በምስጋና መብረቅ ተሸፈነ፤ በእሳት ደመናም ተጋረደ፤ ጉንጮቹን በጥፊ የተመታ ይኽ ሥጋ ከፍ ከፍ አለ፨
የሰማይ ሰራዊት የእሳት ክንፎች እየተርገበገቡለት በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ፤ በዕፀ መስቀል ላይ እጁን የዘረጋ ይኽ ሥጋ በቀኝና በግራ በላይና በታች ተንሰራፋ ወደ ሰማያት ባረገ ጊዜ የመንግሥት ክብር ከፀሓይ መውጫ እስከ ፀሓይ መግቢያ ከሰሜን ዳርቻ እስከ ደቡብ ዳርቻዎች ድረስ ተዘረጋ፤ ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ ኾምጣጤ ያጠጡት ይኽ ሥጋ ከአብ የወጣውን ከርሱም የተነሣ የእሳት መጠጥ ለደቀ መዛሙርት አጠጣቸው፤ ይኸውም የጽድቅ መንፈስ የሦስትነቱ ምልክት ነው (የሐዋ ፪፥፪-፬)፤
ሞትን የቀመሰ ይኽ ሥጋ የሞት ሥልጣን ወደሌለበት መላእክት ሊጐበኙት ወደሚመኙበት ስፍራ ደረሰ፤ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት የቆየ ይኽ ሥጋ ግንቧ ወደማይናድ መሠረቷም ወደማይፈርስ የብርሃን ሠረገላ ወደ ተተከለባት የእሳት ድንኳንም ወደ ተደኰነባት እሳት የተሣለባቸው አራት ገጽ ያላቸው አራቱ እንስሳ ወደ ሚያመሰግኑበት ኻያ አራቱ ሰማያውያን ካህናት ተቀባይነት ያለውን ዕጣንና ያማረውንም መዐዛ የአንጥረኛ እጅ ባልሠራው በወርቅ ማዕጠንት ወደ ሚያቀርቡበት በጽርሐ አርያም ለዘለዓለም ተቀመጠ (ራእ ፬፥፰-፲፩)) ብሏል፡፡
የዕርገተ ክርስቶስ ልዩነት
የጌታ ዕርገት አስቀድመው ካረጉ ከነሔኖክ፣ ከነኤልያስ ከነዕዝራ ሱቱኤል ዕርገት ይለያል፤ እነዚያ ዐረጉ ቢባሉ በራሳቸው ሥልጣን አይደለም፤ ርሱ ግን በገዛ ሥልጣኑ ነውና፡፡ እነርሱ ዐረጉ ቢባሉ በአሳራጊ መላእክት ነው፤ ርሱ ግን መላእክትን የፈጠረ ነውና ይኽነን አይሻውም፡፡
ለምሳሌ ሔኖክን እግዚአብሔር እንጂ የወሰደው በራሱ ሥልጣን እንዳይደለ በዘፍ ፭፥፳፬ ላይ “ሔኖክም አካኺያዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም እግዚአብሔር ወስዶታልና” ይላል፡፡
ነቢዩ ኤልያስንም መላእክት እንዳሳረጉት በ፪ኛ ነገ ፪፥፲፩ ላይ “እነሆ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች በመኻከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ” ይለናል፡፡
ዕዝራ ሱቱኤልንም መላእክት ነጥቀው ወደ ብሔረ ሕያዋን እንዳስገቡት በዕዝ. ሱቱ. ምዕ ፲፫፥፵፱ ላይ “ያን ጊዜ ይኽነን ኹሉ ከጻፈ በኋላ ዕዝራን ይዘው እንደ ርሱ ያሉ ሰዎች ወዳሉበት ሀገር ወሰዱት” ይለናል፡፡
ጌታችን ግን የማንንም ርዳታ ሳይሻ ማረጉ በገዛ ሥልጣኑ የተደረገ ነው፡፡
ይኽነን ልዩ ዕርገቱን ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እንዲኽ ይተነትነዋል፡-
☞ “ወልደ እግዚአብሔርሰ ዐርገ እንበለ ሰዋስው በሳሕወ ደመና ዘያንበለብል ...” (የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለ መሰላል በሚንቦገቦግ የደመና ተን (ጉም) ዐረገ... ነገደ መናብርት ሊያሳርጉት አልመጡም ርሱ ራሱ በመለኮቱ ኀይል አብን ተካክሎ በቀኝ በኩል ተቀመጠባቸው) እንዲል
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም ፵፮ኛውን የዳዊትን መዝሙ
ር በተረጐመበት መጽሐፉ ላይ የክርስቶስን ዕርገት ድንቅነት እንዲኽ ይገልጠዋል፡-
☞ “ይቤ ዐርገ እግዚአብሔር በቃለ ቀርን መዊዕ ወኢይቤ አዕረግዎ አላ ለሊሁ ዐርገ …” (ድል መንሣት ባለበት የነጋሪት ድምፅ እግዚአብሔር ዐረገ አለ (መዝ ፵፮፥፭)፤ ርሱ ዐረገ አለ እንጂ መላእክት አሳረጉት አላለም፤ በፊቱ መንገድ የሚመራ አልፈለገም፤ በዚያው ጐዳና ርሱ ዐረገ እንጂ፤ ኤልያስ በዚያ መንገድ እንደ ክርስቶስ እንዲኽ ሊያርግ አልቻለምና የኤልያስ ባሕርይ በዚኽ መንገድ ሊያርግ አልቻለም፤ መላእክት ወደታዘዙበት ቦታ ወሰዱት እንጂ (፪ኛ ነገ ፪፥፲፩)፤ አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሚኾን የእግዚአብሔር ቃል መላእክትን የፈጠረ ነውና በሥልጣኑ ዐረገ (፩ኛ ጴጥ ፫፥፳፪፤ ፩ኛ ጢሞ ፫፥፲፮)፤ ስለዚኽም ወንጌላዊ ሉቃስ የሐዋርያትን ሥራ በሚናገር መጽሐፍ ወደ ሰማይ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ርሱ አቅንተው ያዩ እንደነበረ ተናገረ፤ አሳረጉት አላለም ወይም ተሸከሙት አላለም፤ ያረገበት ቦታ ገንዘቡ ነውና (የሐዋ ፩፥፱-፲፪)) (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ምዕ 67፤ ክፍል 13፤ ቊ 12-15፤ ገጽ 222)
ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም የጌታን ዕርገት በተናገረበት ድርሳኑ ላይ የጌታችን ዕርገት ከነኤልያስ ዕርገት በእጅጉ የተለየ እንደኾነ እንዲኽ ያስተምራል፡-
☞ “በራሱ ሥልጣን ተነሣ፤ ርሱን ያስነሣው ማንም አይደለም፤ በሚያርግም ጊዜ ማንም ርሱን ያሳረገ አይደለም፤ ኤልያስን አስመልክቶ ዕርገቱ በጌታ አማካይነት የኾነ ነውና እንዲያርግ ያደረገው ጌታ ነው፤ ከዚኽም የተነሣ በሠረገላ እና በእሳት ፈረስ የከበረ ሥነ ሥርዐት ተደረገለት (፪ኛ ነገ ፪፥፲፩)፤ ምክንያቱም ወደ ዐረገበት ቦታ በራሱ ማረግ አይቻለውምና፤ የጌታችን ግን እንደተጻፈው ተለየ፤ ወደ ላይ ለመነሣት ምንም ዐይነት መንኰራኲር አላስፈለገውም፤ በአንድ ቦታ በተወሰነ ጊዜ የሚቀመጡት ሰው በአጋዥ መውጣት ያስፈልገዋል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ብቻ ነውና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱ እግዚአብሔር ነውና መንኰራኲር አያስፈልገውም” እንዲል (ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በእንተ ዕርገተ እግዚእ)
ነገረ ክርስቶስ ክፍል አንድ ከሚለው 622 ገጾች ካሉት መጽሐፌ በጥቂቱ የተወሰደ፤ ሰፊውን ምስጢር ለማወቅ መጽሐፉን ያንብቡ፡፡
ዳዊት በመዝሙሩ “አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፤ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ … እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል” (መዝ ፵፮፥፭-፰) ብሎ የተናረለት በብርሃን፣ በቅዳሴ ወደ ሰማይ ላረገው ለአምላካችን ለክርስቶስ ምስጋና ይኹን አሜን፡፡
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks