Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
Hope Entertainment
January 20 at 7:07 PM ·
#ዳዊት_ፅጌ #የኔ_ዜማ❤️

ፍቅር ነው መንገዴ
ይቅርታ ነው ልቤ
ስኖር ከሱ በላይ
ምንም ነገር አላይ
የአበቦቹም ውበት ያልፋል
ብርቱም ያሉት ይሸነፋል
የሰማዩም የምድሪቱ
ፍቅር ላይ ነው መሰረቱ
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
❤️
ዳገት ቁልቁለቱን ተራራዉን በግሬ
የኔ ዜማ ፍቅር
አይሰለቸኝ ብጮኸ ስለፍቅር ዞሬ
የኔ ዜማ ፍቅር
እሾህ አያስቆመኝ አይገታኝ ጋሬጣ
የኔ ዜማ ፍቅር
ሁሉን አልፈዋለሁ በፍቅር የመጣ
የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር
❤️
እርካታ ነው ፍቅር ፀጋው
ተከባብሮ ለሚያወጋው
ውጤት አለው ሁሉም ነገር
ሰላም ፍቅር ሲሆን ሀገር
❤️
በማለዳ ልነሳ በፍቅር የተነሳ
ልገስግስ ይሄኛው ቀኔ
ፅድቅ የፍቅር ምናኔ
ፍቅር...ፍቅር...ፍቅር
እንደ አክሱም ድንቅ ነው እንደ ላሊበላ (የኔ ዜማ ፍቅር)
ከፊት የሚቀድም ያነፁት ከኋላ ( የኔ ዜማ ፍቅር)
ኖረውት አልፈዋል እነ ማቱ ሳላም (የኔ ዜማ ፍቅር)
እድሜያቸው ይመስክር ያገኙትን ሰላም (የኔ ዜማ ፍቅር)
የኔ ዜማ ፍቅር (2) የልቤ ዜማ ፍቅር
❤️
ራሴን ላድን ከጥላቻው
በማለዳ በመባቻው
ጣሽ ሳይነቃ ነቃሁና
ወደ ፍቅር ሄድኩኝ ገና
የኔ ዜማ ፍቅር የልቤ ዜማ ፍቅር..........
የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
❤️
❤️
shear to your friend for more lyrics @ethiopian_music_lyrics