Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#የሄለን በርሄ ፍቅር
ባትኖርማ ካጠገቤ ከጎኔ ብትለየኝም
እኔስ ኣይሃለው ኣንተ ባታየኝም
ሳየሳየው×2 ባድር ብውል ኣይወጣልኝም
ፍቅር ያንተስ×2
ካጠገብህ ሁኜ ባላጫውትህም
ገላህን ኣቅፌ ምንም ባልስምህም
በመንፈስ ካንተው ነኝ መቼም ኣልለይህ
በሀሳብ መነፅር ሁሌ ነው የማይህ
ውቅያኖስ ባህሩ ኣድማስ ቢጋርደኝ
ወዳንተ መምጣቴ ኣያግደኝ
መምጫ መንገድ ሁሉ ቢዘጋ ቢታገድ
ፍቅር ያደርሰኛል በሀሳብ ኣየር መንገድ
የኔ ፍቅር ..ፍቅር.. ኣገናኝተህ ከምትለየኝ
ምነው በፊት ባታሳየኝ.
ወይ ውሰደኝ ወይ ኣምጣልኝ
ካለዝያ እማ ጉዴ ነው እንጃልኝ
ባትኖርማ ካጠገቤ ከጎኔ ብትለየኝም
እኔስ ኣይሃለው ኣንተ ባታየኝም
ሳየሳየው×2 ባድር ብውል ኣይወጣልኝም
ፍቅር ያንተስ×2
ቀኑ በትካዜ ብቻዬን ሳወራ
ደሞ ሊተካልኝ ለሊቱ በተራ
ከና ጋድም እንዳልኩ ከኣልጋው ስንገናኝ
የሀሳብ ሰመመን ጉዞ ነው ሚቀናኝ
ድንገት ከተፍ ስል ካለህበት ቦታ
እየተላቀስን በናፍቆት በደስታ
ታድያ ምን ያደርጋል ነበር ቢሆን ለኔ
ለካስ በህልሜ ነው የማገኝህ እኔ
የኔ ፍቅር ..ፍቅር.. እውን ኣርገው ፍታው ህልሜ
እንድወጣው እራብ ጥሜ
ወይ ውሰደኝ ወይ ኣምጣልኝ
ካለዝያ እማ ጉዴ ነው እንጃልኝ shear to your friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics