Ethiopian music lyrics
275 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
ንዋይ_ደበበ #አልዋሽም
ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን አስባለው
ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ እተክዛለው
ጨዋታና ሳቅሽን አስታውሼ እህ እላለው
እተክዛለው አስባለዉ አስባለው
እንግዲያው አንቺም ከተለየሽ ከራቅሺኝ አስታዉሺኝ
በፍቅር ከልብ ቆንጂት ከሆድሽ ዉስጥ አታውጪኝ
እንዳረሳውሽ አደራ አንቺም አትርሺኝ
አስታውሺኝ ፍቅሬ አስቢኝ አስቢኝ አስታውሺኝ
እንደምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
እንደምነሽ? እንደምነሽ
ከተሰናበትሺኝ ከሄድሽ'ኮ ቆየሽ
እጠብቅሻለው መች ትመለሻለሽ
ለብቸኝነቴ ለብቸኝነቴ፥ ላዲሱ እንግዳዬ
ትካዜ ብቻ ነዉ መሰናገጃዬ
እንደምነሽ ብዬ ሁሌ አስብሻለዉ
በቃል ኪዳን ፅናት እጠብቅሻለዉ
በቃል ኪዳት ፅናት እጠብቅሻለዉ የኔ ፍቅር
በቃል ኪዳን ፅናት እጠብቅሻለው
አልዋሽም ስበላ አሰብኩሽ
አልዋሽም ስጠጣ አሰብኩሽ
አልዋሽም ሲመሽ አሰብኩሽ
ሲነጋ አሰብኩሽ
አልዋሽም እኔ አልዋሽም
የምነት የዉነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም
ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን አስባለዉ
ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ እተክዛለው
ጨዋታና ሳቅሽን አስታዉሼ እህ እላለው እተክዛለዉ አስባለዉ
አስባለው
እንደምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
እንደምነሽ? እንደምነሽ
ከተሰናበትሺኝ ከሄድሽ'ኮ ቆየሽ
እጠብቅሻለዉ መች ትመለሻለሽ
ናፍቆትሽ ባይኔ ላይ
ናፍቆትሽ ባይኔ ላይ ከተመላለሰ
የፍቅር እመቤቴን አንቺን ካስታወሰ
እንደምነሽ ብዬ አስታዉስሻለዉ
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለዉ
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለዉ የኔ ፍቅር
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለው
አልዋሽም ስበላ አሰብኩሽ
አልዋሽም ስጠጣ አሰብኩሽ
አልዋሽም ሲመሽ አሰብኩሽ
ሲነጋ አሰብኩሽ
አልዋሽም እኔ አልዋሽም
የምነት የዉነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም
shear to your friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics