Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
ዳዊት_ፅጌ #ቻል_ዘንድሮ ❤️

ተይ ለማለት እንኳን እያቃተኝ መናገር ደፍሮ
ቻል አርጌው ልደር እስኪ ልክረም ልግፋው ዘንድሮ
ከተባለ ይሄም ኑሮ ይሄም ኑሮ
ለመርሳት ለመራራቅ እሷን እርም ብሎ
መሸሽማ ያኔ ነበር ድሮ
ተላምዳኝ በልቤ ላይ ፍቅሯ እየነደደ
የት ይኬዳል ዛሬ ከረፈደ
መክረም እንጂ ችሎ ይሄን ኑሮ
ይሄን ኑሮ ይሄን ኑሮ
❤️
ተወት አርጋው የኔን ገላ
በሰው ብታስቀናኝ በሌላ
ላይሳሳት ቃል ተነናግሮ
ከእንግዲህ ላይጠላት ምሎ
ከእንግዲህ ላይጠላት
ልቤ ተቀብላል ምሎ ይሄን ኑሮ
❤️
በል ሆዴ ሆዴ ቻላት
እሷም ለኔ ግድ የላት
ከማስቀየም ተናግሮ
መክረም ይሻላል ችሎ /2x
❤️
ሆዴ ሆዴ ቻል ዘንድሮ
ከተባለ ይኽም ኑሮ /2x
❤️
አንድም ቃል ላይተነፍስ አምኖ እየተቀጣ
ምን ያደርጋል ሰው አቅሙን ካጣ
ተላምዳኝ በልቤ ላይ ፍቅሯ እየነደደ
የት ይኬዳል ዛሬ ከረፈደ
መክረም እንጂ ችሎ ይሄን ኑሮ
ይሄን ኑሮ ይሄን ኑሮ
❤️
ተወት አርጋው የኔን ገላ
በሰው ብታስቀናኝ በሌላ
ላይሳሳት ቃል ተነናግሮ
ከእንግዲህ ላይጠላት ምሎ
ከእንግዲህ ላይጠላት
ልቤ ተቀብላል ምሎ ይሄን ኑሮ
❤️
ሆዴ ሆዴ ቻል ዘንድሮ
ከተባለ ይኽም ኑሮ /2x
❤️
❤️
for more lyrics shear to your friend @ethiopian_music_lyrics