Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ታደለ_ሮባ #ሰው_በናፍቆት_ታሞ
ሰው በናፍቆት ታሞ ከተነጣጠለ
በዚህ አለም መኖሩ ይቅራ ምን አለ /2x
ክፉሽን ብሰማ እንዴት እሆናለሁ
ስመጣ ያጣሁሽ እለት የት ብዬ ገባለሁ
እባክህ አምላኬ አታስነካት ክፉ
ፀፀቱ ለኔው ነው ተመልሶ ትርፉ
ቀን ከሌት ሳልምሽ ስናፍቅሽ ኖሬ
ድንገት የለች ቢሉኝ ስገባ መንደሬ
ሀዘኔ መራር ነው እኔ አልሄድም ቆሜ
ልፈወስ ብመጣ በናፍቆት ታምሜ
ሰው በናፍቆት ታሞ ከተነጣጠለ
በዚህ አለም መኖሩ ይቅራ ምን አለ
መከራን መሸከም አይችልም አንጀቴን
የሷን ክፉ ከማይ እመርጣለሁ ሞቴን
አልጣሽ ስመጣ ካለሽበት ስፍራ
አምላክ ይጠብቃት እንዬን አደራ
አይኖችሽን ማየት በጣም ናፍቂያለሁ
ድምፅሽን ለመስማት እኔስ ጓጉቻለሁ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics