Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ዲጄ_ሮፍናን# ፒያሳ_ላይ

ትዝ ይለኛል እንደ ትላንት
የመጀመሪያ ቀን ሳያት
ያኔ የቬል ሱሪው ነገር
አፍሮ ብጥር ብጥር ብጥር
ከአዲስ ከተማ በቶሎ
(አይ በቶሎ)
ጎዞዬ ቤቴ አራት ኪሎ
(አይ አራት ኪሎ)
ልጅት ነች ከናዝሬት ስኩል
(ናዝሬት ስኩል)
ነገሯ በአራዳ በኩል።
በግርግሩ መሀል ተያየን
አኔ እና እሷ ያኔ ተገናኘን
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ትዝ ይለኛል አይኔ ከአይንሽ
መጀመሪያ ስተዋወቅሽ
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ታሪክ ያለው እጅ ወደላይ።
አዲስ አበባን
ሳያት ሰባዎቹ መሀል
ትዝ ይለኛል ብዙ ነገር
ሮሀ እና የአንቺ ፍቅር
አባትሽ ያ ጀነራል
(ያ ጀነራል)
አስረው ሲገርፉ ወንድሜን
(ወነድሜን ወንድሜን)
እኔ እና አንቺ ግን አልፈናል
(አው አልፈናል)
ፍቅርን በባለአንጣዎች መሀል
(አዬ አዬ)
አስታውሳለው መፅሀፍቶቹን
ሳመጣልሽ የሀዲስ በአሉ ሎሬት ፀጋዬን
ከአራዳው ስር ብለን ተቀጣጥረን
አውቶቢሷ ሳትመጣ በእግሬ እቀድማት ነበር።
በግርግሩ መሀል ላይሽ
ከራዳው ስር አንቺን ላገኝሽ
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
አይረሳም የጥንቱ ነገር
ያሳለፍነው ከደጉ መንደር
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ታሪክ ያለው እጅ ወደላይ።
ጨዋታ ጨዋታ ከአራዳው ቦታ
(ጨዋታ ጨዋታ ከአራዳው ቦታ)
ሳሚልኝ ቤቱን ጊዮርጊስን አዬ
(ሳሚልኝ ቤቱን ጊዮርጊስን አዬ)
ጥምቀት ነው ጨዋታ ከአራዳው ቦታ
(ጥምቀት ነው ጨዋታ ከአራዳው ቦታ)
ሸኘው ታቦቱን አድዋ ዘማቹን አዬ (ሸኘው ታቦቱን አድዋ ዘማቹን
አዬ)
ዘራፍ ዘራፍ ዘራፍ

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጨረቃን
#ዲጄ_ሮፍናን
ለፍጥረት ሁሉ ፥ ይመሻል፤
ለውበትሽ ፥ ያኔ ይነጋል፤
ታምሪያለሽ ልክ ፥ ሌቱ ሲጀምር፤
እንደውቧ ፥ እንደጨረቃ፤
ሲመሽ ነው ፥ መልክሽ ሚፈካው፤
እጅ ነሳው ፥ አልኳት አደርሽ እንደምን፤
ሚያበራልሽ ፥ አትፈልጊም፤
በሌላ ብርሀን ፥ አትፈኪም፤
ቁንጅናሽ የራስሽ ነው ፥ አንቺ አትለኪም፤
ያ ውበትሽን ፥ እንዳገኘው፤
በመሸ ብዬ ፥ ተመኘው፤
ጀምበሪቱ ውረጂ ፥ ስል ተገኘው።
ሲመሻሽ ፥ ትደምቂያለሽ፤
ጨረቃን ፥ ትመስይኛለሽ፤
ሲመሻሽ ፥ ታምሪያለሽ፤
ጨረቃን ፥ ትመስይኛለሽ።
እኔ ፥ ሱሰኛሽ፤
ያንቺ ፥ ምርኮኛሽ፤
ከቡስካው በስተጀርባ ፥ ላየው ውበትሽን፤
ፀሀይ ፀሀይ ፥ እንድትወርድ [አስመኘሽኝ፤]፪*
ኢቫንጋዲው ምሽት ላይ ፥ ጨዋታ አልምደሽኝ፤
ፀሀይ ፀሀይ ፥ እንድትወርድ [አስመኘሽኝ።]፪*
ሲመሻሽ ፥ ትደምቂያለሽ፤
ጨረቃን ፥ ትመስይኛለሽ፤
ሲመሻሽ ፥ ታምሪያለሽ፤
ጨረቃን ፥ ትመስይኛለሽ።

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics