Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.75K photos
141 videos
2 files
411 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ወደ ቪዬትናም ለመጓዝ ተዘጋጅተዋል?! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 3 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቪዬትናም ዋና ከተማ ሀኖይ በረራ የሚጀምር መሆኑን ለውድ ደንበኞቹ በደስታ ያበስራል። ይህ በረራ የአየር መንገዳችንን ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ከማስፋቱም በተጨማሪ በአፍሪካ እና ደቡብ ምስራቅ እስያ መካከል ለሚጓዙ መንገደኞች ምቹ የበረራ አማራጮችን ለማቅረብ የሚያስችለን ነው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-to-launch-new-passenger-service-to-hanoi-vietnam
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሀኖይ
አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢታሃድ ኤርዌይስ የአየር ትራንስፖርት ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ይህ ስትራቴጂያዊ ስምምነት ለደንበኞች የተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ ለማቅረብ በሁለቱ አየር መንገዶች መካከል “የኮድ ሼር” አገልግሎት እና በአዲስ አበባ እና አቡዳቢ መካከል የበረራ አገልግሎት መጀመርን ያካተተ ነው። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሀምሌ 8 ቀን 2017 ጀምሮ ከአዲስ አበባ አቡዳቢ እንዲሁም ኢታሃድ አየር መንገድ ከመስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከአቡዳቢ አዲስ አበባ ቀጥታ የበራራ አገልግሎት የሚጀምሩ ይሆናል።
በስምምነት መርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ እና የኢቲሀድ ኤርዌይስ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሞሀመድ አሊን ጨምሮ የሁለቱም አየር መንገዶች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች `የተገኙ ሲሆን ስምምነቱን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም በኢትሀድ ኤርዌይስ በኩል የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶላዶ ኔቬስ ፈርመዋል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-and-etihad-launch-strategic-joint-venture-and-new-flights-between-addis-ababa-and-abu-dhabi
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ግርማ ሞገስ የተላበሱ ተራሮችን፣ አስደማሚ መልክዓ ምድር እና የጫሞ ኃይቅ ላይ ልዩ ትዕይንትን ጨምሮ ውብ ተፈጥሮን በማየት የማይረሳ የጉዞ ትውስታ ያኑሩ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አርባምንጭ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢቲሃድ ኤርዌይስ ያደረጉት በጋራ የመስራት ስምምነት።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በክብር ልንቀበልዎ ተዘጋጅተናል፤ ይምጡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምቾትዎን ጠብቀን እርስዎን በብቃት ማገልገላችን የሁልግዜም ኩራታችን ነው!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በምቾት እና በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ዓለምን ይጎብኙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የማይረሳ እና አስደሳች በረራ ከእኛ ጋር ያድርጉ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @Salih_Mohammed2 ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አርቸር አቪዬሽን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለማዋል የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱ ዘመኑ የደረሰበትን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ከማስቻሉም በላይ ለአየር ንብረት መጠበቅ የራሱ አስተዋፅዖም ያበረክታል።
ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-africa-s-largest-carrdier-and-archer-sign-an-agreement-to-deploy-midnight-under-the-launch-edition-program
የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች መንደር (ET Village) ህፃናት እና ታዳጊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝተው ያደረጉትን ጉብኝት በዛሬው የኢትዮጵያ መርሐግብር ይዘንላችሁ ቀርበናል። ተከታተሉን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው ዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ምኞቱን ይገልፃል።
ዒድ ሙባረክ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ