Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.75K photos
141 videos
2 files
411 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታላቁን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል የኢፍጣር መርሐግብር አካሄደ።

በኢፍጣር መርሐግብሩ ላይ የተከበሩ ሼህ አብዱልአዚዝ አብዱልወሌ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ፣ የተከበሩ ዶ/ር ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሀላፊ አቶ ለማ ያዴቻ ፣ የአየር መንገዱ አመራር አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ የኢፍጣር መርሀግብር ከማዘጋጀት ባሻገር በርካታ በረራዎችንና ሰራተኞችን በመመደብ የሀጅ ተጓዦችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ በማጓጓዝ፣ለሐጅ ተጓዦች ብቻ የሚውል መስገጃና ማረፊያ ያለው ተርሚናል ማዘጋጀት፣በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን በኩል በተለያዩ ጊዜያትና ሁኔታ በመንገደኞች የተረሱ ሃይማኖታዊ መጻሕፍትን ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በክብር በማስረከብ እና በተለያዩ ተያያዥ አገልግሎቶች ሀገራዊ ሀላፊነቱን አቅም በፈቀደ መጠን ሲወጣ ቆይቷል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከ140 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቻችን በምቾት እና ከልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ጋር ይብረሩ። መልካም የእረፍት ቀናት ይሁንልዎ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከምርጥ መስተንግዶ ጋር በክብር ልናገለግልዎ ተዘጋጅተናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስተማማኝ፣ ፈጣን እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቪ.አይ.ፒ እና ልዩ ቻርተር በረራ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ቦይንግ 737-800 ቢዝነስ አውሮፕላን መረከቡን ሲገልጽ ደስታ ይሰማዋል። ይህ የቢዝነስ አውሮፕላን በተለይም በአፍሪካ የንግድና ኢንቨትመንት ስራዎቻቸውን ለማሳለጥ በርካታ ጉዞዎችን ለሚያደርጉ በከፍተኛ ንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና ደረጃውን የጠበቀ ልዩ ልዩ የቻርተር በረራ አገልግሎት ለሚሹ ተጓዦች በሙሉ አየር መንገዱ ልዩ አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችለዋል።

በአቀባበል ስነስርዐቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የቦይንግ ኩባንያ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተወካዮች ተገኝተዋል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-expands-charter-service-with-new-boeing-737-800-business-jet

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በደማቅ ፈገግታ ተቀብለን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደ ቪዬትናም ለመጓዝ ተዘጋጅተዋል?! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 3 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቪዬትናም ዋና ከተማ ሀኖይ በረራ የሚጀምር መሆኑን ለውድ ደንበኞቹ በደስታ ያበስራል። ይህ በረራ የአየር መንገዳችንን ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ከማስፋቱም በተጨማሪ በአፍሪካ እና ደቡብ ምስራቅ እስያ መካከል ለሚጓዙ መንገደኞች ምቹ የበረራ አማራጮችን ለማቅረብ የሚያስችለን ነው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-to-launch-new-passenger-service-to-hanoi-vietnam
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሀኖይ
አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢታሃድ ኤርዌይስ የአየር ትራንስፖርት ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ይህ ስትራቴጂያዊ ስምምነት ለደንበኞች የተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ ለማቅረብ በሁለቱ አየር መንገዶች መካከል “የኮድ ሼር” አገልግሎት እና በአዲስ አበባ እና አቡዳቢ መካከል የበረራ አገልግሎት መጀመርን ያካተተ ነው። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሀምሌ 8 ቀን 2017 ጀምሮ ከአዲስ አበባ አቡዳቢ እንዲሁም ኢታሃድ አየር መንገድ ከመስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከአቡዳቢ አዲስ አበባ ቀጥታ የበራራ አገልግሎት የሚጀምሩ ይሆናል።
በስምምነት መርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ እና የኢቲሀድ ኤርዌይስ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሞሀመድ አሊን ጨምሮ የሁለቱም አየር መንገዶች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች `የተገኙ ሲሆን ስምምነቱን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም በኢትሀድ ኤርዌይስ በኩል የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶላዶ ኔቬስ ፈርመዋል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-and-etihad-launch-strategic-joint-venture-and-new-flights-between-addis-ababa-and-abu-dhabi
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ግርማ ሞገስ የተላበሱ ተራሮችን፣ አስደማሚ መልክዓ ምድር እና የጫሞ ኃይቅ ላይ ልዩ ትዕይንትን ጨምሮ ውብ ተፈጥሮን በማየት የማይረሳ የጉዞ ትውስታ ያኑሩ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አርባምንጭ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢቲሃድ ኤርዌይስ ያደረጉት በጋራ የመስራት ስምምነት።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በክብር ልንቀበልዎ ተዘጋጅተናል፤ ይምጡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምቾትዎን ጠብቀን እርስዎን በብቃት ማገልገላችን የሁልግዜም ኩራታችን ነው!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በምቾት እና በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ዓለምን ይጎብኙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ