Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.75K photos
141 videos
2 files
411 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በአፍሪካ አህጉር ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ላይ አተኩሮ በጋና አክራ በተካሄደው አመታዊው የ “2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” ላይ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጫወተ ላለው ሚና ላሳዩት የላቀ የአመራርነት ሚና የ “Leadership in Connecting Africa through Transport Award” ተሸላሚ ሆነዋል።
ይህ ሽልማት አፍሪካን እርስ በርስ በማገናኘት ቁርጠኛ የአመራርነት አስተዋፅዖ ላበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና የሚሰጥበት ሲሆን የዘንድሮው የ “2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የታላላቅ አህጉር ዓቀፍ የንግድ ተቋማት መሪዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተገኙበት በጋና አክራ ተካሂዷል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-group-ceo-honored-with-prestigious-leadership-in-connecting-africa-through-transport-award
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የበረራ አድማሱን ከግዜ ወደ ግዜ እያሰፋ የመጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተጨማሪ አዳዲስ አለም ዓቀፍ መዳረሻዎች በረራ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቅቋል።
እነዚህ አዳዲስ መዳረሻዎቻችንን መገመት ይችላሉ?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደ በርካታ አለም ዓቀፍ መዳረሻዎቻችን አብረውን ይጓዙ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ