Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.76K photos
141 videos
2 files
412 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መንደር (ET-Village) ሕፃናት እና ታዳጊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ጉብኝት አደረጉ። በጉብኝታቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ልቆ እንዲቀጥል ያስቻሉትን የተለያዩ የስራ ክፍሎች እና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሕፃናትና ታዳጊዎቹ በተለያዩ የአየር መንገዱ ባልደረቦች ገለፃና ማብራሪያ የተደረገላቸው ሲሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዙሪያ የተዘጋጀ ጥያቄና መልስ ውድድርና መሰል አስተማሪና አዝናኝ መርሐግብሮች ተሳትፈው የተዘጋጀላቸውን የማስታወሻ ሽልማቶች ተቀብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መኖሪያ መንደር (ET- Village) አየር መንገዱ ለሰራተኞች ምቹ የስራ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ለ5ሺህ ሰራተኞች የምዕራፍ ሁለት የመኖሪያ መንደር ግንባታ እያካሄደ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በአፍሪካ አህጉር ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ላይ አተኩሮ በጋና አክራ በተካሄደው አመታዊው የ “2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” ላይ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጫወተ ላለው ሚና ላሳዩት የላቀ የአመራርነት ሚና የ “Leadership in Connecting Africa through Transport Award” ተሸላሚ ሆነዋል።
ይህ ሽልማት አፍሪካን እርስ በርስ በማገናኘት ቁርጠኛ የአመራርነት አስተዋፅዖ ላበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና የሚሰጥበት ሲሆን የዘንድሮው የ “2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የታላላቅ አህጉር ዓቀፍ የንግድ ተቋማት መሪዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተገኙበት በጋና አክራ ተካሂዷል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-group-ceo-honored-with-prestigious-leadership-in-connecting-africa-through-transport-award
#የኢትዮጵያአየርመንገድ