Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከ Heart Attack Ethiopia Inc “ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱ Heart Attack Ethiopia Inc የተሰኘው ድርጅት በኢትዮጵያ ለልብ እና ስትሮክ ህመም የሚሰጠውን የበጎ ፍቃድ ህክምና አገልግሎት ብሔራዊ አየር መንገዳችን በተለያዩ መንገዶች እገዛ እንዲያደርግ ያስችለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተፈራረመው ይህ ስምምነት የበጎ ፍቃድ የህክምና አገልግሎቱ የበለጠ እንዲጠናከር እና ተደራሽ እንዲሆን የሚያግዝ ሲሆን አየር መንገዳችን ከመደበኛ የስራ እንቅስቃሴው በተጨማሪ የማሕበራዊ አገልግሎት በመስጠት ረገድም ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ባልተቋረጠ ትጋት እና ስኬት እርስዎን ማገልገላችንን እንቀጥላለን! አጓጊ የበረራ አማራጮቻችንን ይቃኙ!
https://www.ethiopianairlines.com/et
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
 
ምቹ እና አስደሳች የበረራ ግዜ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር!
 
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻይና አዲስ አመትን በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በድምቀት አከበረ። ይህን በዓል አስመልክቶ በተካሄደው መርሃግብር ላይ ቻይና ወደሚገኙ መዳረሻዎቻችን ለሚጓዙ መንገደኞቻችን ልዩ ልዩ ስጦታዎች የተበረከተ ሲሆን ወደ ቻይና መዳረሻዎቻችን በሚያቀኑ በረራዎቻችንም ላይ በድምቀት ይከበራል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በየትኞቹ የአውሮፐላኖቻችን አይነቶች ተጉዘው ያውቃሉ? #የኢትዮጵያአየርመንገድ
Anonymous Poll
54%
ዲ. ኤች-8 (Q-400)
49%
ቦይንግ -737
39%
ቦይንግ -777
38%
ቦይንግ -787 ድሪም ላይነር
40%
ኤርባስ A350
ከአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ተቋም የተውጣጣ የምሁራን ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ጉብኝት አደረገ።
የምሁራን ቡድኑ “የሲቪል አቪዬሽን ትራንስፎርሜሽን” በተሰኘ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የማማከር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ከአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት እንዲሁም የአየር መንገዱን የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። የምሁራን ቡድኑ አጠቃላይ የአቪዬሽን ሴክተርን የማዘመን ስራ ላይ በማተኮር እየሰራ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ