በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ የተመራ ከፍተኛ የኢቢሲ የስራ ሀላፊዎች ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጥር ግቢ በመገኘት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሀላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት እንዲሁም የስራ ጉብኝት አደረገ።
የኢቢሲ አመራሮች በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አቪዬሽን ልህቀት ቀዳሚ እንዲሁም በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉትን የስራ ክፍሎችና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ሁለቱ ብሔራዊና አንጋፋ ተቋማት በቅርበት በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ Ethiopian Broadcasting Corporation

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት 22 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተደረገበትንና ከ 1,300 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ለበረራ ሙያ ባልደረቦች የተገነባ ባለ 8 ወለል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ ለምረቃ አበቃ።
ይህ በ48,000 ስኩዌር ካሬሜትር ላይ ያረፈ እጅግ ዘመናዊ ህንፃ በአንድ አመት ከአንድ ወር ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን በውስጡም ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆነ፣ በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ የተገጠመለት፣ እንዲሁም ድንገተኛ የእሳት አደጋን መቋቋም እንዲያስችል ተደርጎ በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ የተገነባ ነው።
ይህ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ህንጻ ቻይና ጂያንግሱ በሚባል ህንጻ ተቋራጭ ድርጅት እና K2N አርክቴክቸር እና ኢንጅነሪንግ አማካሪ ድርጅት የተገነባ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የቻይና ጂያንግሱ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር ባሻገር የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት በ2ኛ ዙር የቤት ግንባታ ፕሮግራም ለ5000 ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ