Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.6K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው የኡጋንዳ “ኢኩላ ቱሪዝም ሽልማት” የ2024ዓ.ም ምርጥ የቢዝነስ ክፍል ዘላቂ አገልግሎት (Best Sustainable Airline of 2024-Business Class Category) ሽልማትተቀዳጀ። መርሐግብሩ በካምፓላ ሸራተን ሆቴል የተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኡጋንዳ ቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማቱ ተበርክቶለታል። በዚህ ዓመታዊ ሽልማት ለሀገሪቱ ቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት በጎ አሻራ ያሳረፉ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዕውቅና ይሰጣቸዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮፕላን ምስለ በረራ (Flight Simulator) ቴክኖሎጂ ዘመኑ የደረሰባቸው ዘመናዊ ምስለ በራራዎች ባለቤት ሲሆን እነዚህ ምስለ በረራዎች በአውሮፕላኑ ላይ ተጨማሪ ስልጠና ሳያስፈልግ ወደ በረራ የመግባት ክህሎትን የሚያስጨብጡ የአቪዬሽኑ ኢንደስትሪ የልሕቀት ማሳያዎች ናቸው።”
ካፒቴን ፍሰሀ ተስፋዬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍላይት ኦፐሬሽን የስልጠና ክፍል ዳይሬክተር
https://www.youtube.com/watch?v=g3aigMvftMg&t=121s
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኒውዮርክ ሲያደርገው የነበረውን አራት ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ ከህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ከተማዋ እለታዊ በረራ የሚጀምር መሆኑን እያበሰረ ደንበኞች በድረ ገፅ www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app በመጠቀም ትኬታቸውን ቆርጠው በዕለታዊ በረራ አገልግሎቱ እንዲጠቀሙ ይጋብዛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ የመንገደኞች በረራውን ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2017 ዳግም ጀምሯል።

በፕሮግራሙ ላይ የላይቤርያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ሰርሊፍ ቴይለር፣በኢትዮጵያ የላይቤርያ አምባሳደር ሉዊስ ሻሬን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአፍሪካ አቪዬሽን ኢንደስትሪ የመሪነት ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር የማገናኘት መርሁን ይበልጥ በማጠናከር በቅርብ ግዜ ወደ ፖርት ሱዳን እንዲሁም ባንግላዴሽ ዳካ በረራ የጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ወደ ላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ ዳግም በረራ ጀምሯል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ “Asian Infrastructure Investment Bank” (AIIB) ፕሬዝደንት ጂን ሊኩን የተመራ የልዑክ ቡድን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጥር ግቢ ተገኝቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም ከአየር መንገዳችን አመራር አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት አደረገ።

የልዑክ ቡድኑ ከውይይቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እስቅስቃሴ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን አየር መንገዳችን በአፍሪካ አህጉር በመሪነት የሚጠቀስባቸውንና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ያስጠበቀባቸውን የስራ ክፍሎችና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች ተመልክቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላይቤርያ ሞንሮቪያ ዳግም የጀመረው የመንገደኞች በረራ ሞንሮቪያ ሲደርስ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ጆሴፍ ናዩማ ቦካይ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎለታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ እና በላይቤርያ መካከል የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በመጀመር የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ብሎም አፍሪካን እርስ በርስና ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት እየተጫወተ ያለውን የመሪነት ሚና አጠናክሮ ይቀጥላል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ