የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ክፍል መንገደኞች የተዘጋጀ አዲስ የበረራ ላይ ዝርዝር የምግብ አማራጮችን የማስተዋወቅና የቅምሻ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል አካሄደ። መርሐግብሩ አዲሱን የበረራ ላይ ምግብ አማራጮች ከማስተዋወቅ ባለፈ ከኢኮኖሚ እና ቢዝነስ ክፍል መንገደኞቻችን ተገቢውን ግብረ መልስ ለማግኘት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ቅርንጫፍ ቢሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች ያስተዋወቀ ልዩ መርሐግብር በኪንሻሳ አካሄደ። በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመኑ የደረሰባቸውን አዳዲስ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ በማስተዋወቅና አህጉሪቱን ከመላው ዓለም ጋር በማገናኘት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋፅዎ የተገለፀ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏትን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶችና ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሰፊው ተዋውቀውበታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘመናዊነትንና ዕምቅ ባህላዊ ይዘቶችን አለም አቀፍ ዕውቅና ከተቸራቸው ሙዚየሞች ጋር አጣምራ ወደያዘችው ፍራንክፈርት ከተማ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አስደሳች የበረራ ጉዞ ያድርጉ!
#ፍራንክፈርት #የኢትዮጵያአየርመንገድ
#ፍራንክፈርት #የኢትዮጵያአየርመንገድ