Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ሌላኛዋ የምዕራብ አፍሪካ መዳረሻችን የሆነችው የጋና ዋና ከተማ አክራ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን በከፍተኛ ድምቀት በኮቶካ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተቀብላለች።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ትልቁ ተራራ መገኛ ወደሆነው ታንዛኒያ ኪሊማንጃሮ የአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ከፍ ብለን ለመብረር ዝግጅታችንን አጠናቅቀናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲሸልስ “አንድ ትኬት ይግዙ አንድ በነፃ ይሸለሙ” የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቷል:: በዚህ ልዩ ቅናሽ የ 2 ምሽት ቆይታ በማድረግ ዘና ይበሉ! ስለ ልዩ የጉዞ ጥቅሉ ተጨማሪ መረጃ በአቅራቢያዎ የሚገኙ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችንን አሊያም የጉዞ ወኪልዎን ማግኘት ይችላሉ።
ደንብና እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሲሸልስ
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በምቾት ይጓዙ ። ቀጣይ የጉዞ መዳረሻዎን የት አስበዋል?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ ኅዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ በቡድን ወደ ሲንጋፖር ከተማ ለሚጓዙ ደንበኞቹ ልዩ የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቷል። ትኬትዎን አሁኑኑ ይግዙ ፤ ጉዞዎን ከኅዳር 22 ቀን እስከ ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ያድርጉ። በድረ ገፃችንን www.ethiopianholidays.com ፣በኢሜል አድራሻችን ETHolidays@ethiopianairlines.com እንዲሁም በስልክ ቁጥሮቻችን +251115174207/4203/4504 ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ተጨማሪ ዕለታዊ በረራዎች ከዳሬሰላም ወደ 140 በላይ መዳረሻዎች ከኅዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያአየርመንገድ ጋር!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲንጋፖር ቅርንጫፍ ቢሮ ለተለያዩ የስራ አጋሮቹ የምስጋና እና የማበረታቻ ሽልማት ምሽት አዘጋጀ። በምስጋና እና በማበረታቻ ሽልማት መርሐግብሩ ላይ የአየር መንገዱ ደንበኞች፣ የጉዞ ትኬት ሽያጭ ወኪሎችና የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት ሰጪዎች የተካተቱ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲንጋፖር በሚያደርገው በረራ በአፍሪካ እና በሲንጋፖር መካከል እያደገ ለመጣው የንግድ እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር እንዲሁም የባህል ልውውጥ እያበረከቱ ላሉት የላቀ አስተዋፅዖ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ