የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኦስትሪያ ቪዬና በረራ የጀመረበትን 10ኛ ዓመት በቪዬና በደማቅ ሁኔታ አከበረ። በአከባበር ስነ ስርዐቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአመራር አባላት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የቪዬና ኤርፖርት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ይህ የበረራ መስመር ላለፉት 10 ዓመታት በአውሮፓ ታላላቅ ስብሰባዎችን፣ ኮንቬንሽኖችን እና የሙዚቃ ትርዒቶችን በማስተናገድ የምትታወቀውን ቪዬና ከተማ ከአፍሪካ አሕጉር ብሎም ከመላው ዓለም ጋር በማገናኘትና ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትስስርን በማሳለጥ ረገድ ጉልህ አስተዋፅዖ አበርክቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍23🥰11❤6
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ አክሱም ከተማ ዳግም በረራውን በአክሱም አጼ ዮሐንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገ ደማቅ ስነስርዓት ጀምሯል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
❤83👍24🎉10👏7