Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኦስትሪያ ቪዬና በረራ የጀመረበትን 10ኛ ዓመት በቪዬና በደማቅ ሁኔታ አከበረ። በአከባበር ስነ ስርዐቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአመራር አባላት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የቪዬና ኤርፖርት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ይህ የበረራ መስመር ላለፉት 10 ዓመታት በአውሮፓ ታላላቅ ስብሰባዎችን፣ ኮንቬንሽኖችን እና የሙዚቃ ትርዒቶችን በማስተናገድ የምትታወቀውን ቪዬና ከተማ ከአፍሪካ አሕጉር ብሎም ከመላው ዓለም ጋር በማገናኘትና ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትስስርን በማሳለጥ ረገድ ጉልህ አስተዋፅዖ አበርክቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍23🥰116