Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.76K photos
141 videos
2 files
412 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ማሕበራዊ ሀላፊነቱን በተለያዩ ግዜያት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን የሚወጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በ 2015 ዓ. ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ባስገነባው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል።

በማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙ ላይ አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር አባላትና ሰራተኞች ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወዳሰቡት መዳረሻዎ በምቹ አገልግሎት እና በኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነ የሰርግ ዝግጅት የሶስት ሰራተኞቹን የጋብቻ ስነ ስርዓት በድምቀት ያከበረ ሲሆን በስካይላይት ሆቴል የተደረገውን ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም ተከትሎ ጥንዶቹ አየር መንገዱ ባዘጋጀው የሶስት ምሽት የጫጉላ ሽርሽር የጉዞ ጥቅል ወደ ዛንዚባር ተጉዘዋል። የሙሽሮች የዛንዚባር ቆይታ እንዳያመልጥዎ ይከታተሉን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያንሆሊደይስ #ስካይላይትሆቴል #ዛንዚባር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባዘጋጀው ልዩ ቅናሽ ተጠቅመው በመጪው የፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ በመታደም ልዩ ግዜ ያሳልፉ። ትኬትዎን እስከ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ይግዙ ከ ሰኔ 24 ቀን እስከ ሐምሌ 12 ፣2016 ዓ.ም ይጓዙ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጉዘው ሊያዩት የሚሹት መዳረሻ የት ነው?
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠንካራ የስራ ባሕልን ከማዳበር ጎን ለጎን ቤተሰባዊነትን የተላበሰ የስራ አካባቢን ለመፍጠር ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል። አየር መንገዱ ባዘጋጀው የሶስት ምሽት የጫጉላ ሽርሽር የጉዞ ጥቅል ወደ ዛንዚባር የተጓዙት ሙሽሮች የስራ ባልደረቦቻችን ተጨማሪ ምስሎች እነሆ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያንሆሊደይስ #ስካይላይትሆቴል #ዛንዚባር
በስካይ ላይት ሆቴል የተጀመረው የሰራተኞቻችን ልዩ የሰርግ ስነ-ስረአት በውቧ ዛንዚባር በሀገሬው ባህል ደማቅ አቀባበል ሞቅ ብሎ ቀጥሏል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያንሆሊደይስ #የጫጉላሽርሽርጥቅል #የዛንዚባርበረራ #ስካይላይትሆቴል #ዛንዚባር