በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙሉ የመጓጓዣ ወጪያቸው ተሸፍኖ ወደ ህንድ ሀገር ለህክምና ከሚሄዱት አንድ መቶ ሕፃናት መካከል ለመጀመሪያዎቹ አራት ሕፃናት የሽኝት ፕሮግራም ተካሔደ። በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ሽሪ ሮበርት ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ እና የሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ሓላፊዎች ተገኝተዋል።
👍77❤21🥰10👏5😍2
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ የነበራቸውን ቆይታ በማራኪ ምስል ያጋሩን @MariaAklilu ናቸው እናመሰግናለን። እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ የነበርዎትን ቆይታ በመልዕክት ሳጥን መቀበያ ይላኩልን ፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍68🥰19❤16👏7
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ካምፓኒ ጋር በመተባበር ከ12,000 ፓውንድ በላይ የሚመዝኑ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ ቁሳቁሶችን በቅርቡ በተረከባቸው ሶስት አዲስ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ አጓጓዘ። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3P74KlL
❤49👍37🥰5🎉5
ለየብስ ትራንስፖርትዎ ሁነኛ አማራጭ አዘጋጅተናል! በመዳረሻዎ ያለ ሃሳብ እንዲንቀሳቀሱ ተሽከርካሪ መከራየት እና፣ወይም ከአየር ማረፍያ የየብስ መጓጓዣ አገልግሉት እና ተሽከርካሪ ከነሹፌሩ መከራየት የሚችሉበትን አማራጭ አመቻችተናል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ። https://bit.ly/3uxfEaH
👍41❤20👏6
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ለ "Top Shop Awards 2023" ሽልማት በእጩነት ቀርቧል። በአፍሪካ የአውሮፕላን ጥገና መስክ ቀዳሚና በአለም ተመራጭ ከሆኑት የጥገና ማዕከላት አንዱ ለሆነው ኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል ድምፅዎን ይስጡ። https://bit.ly/3Hod5zo
👏97👍47❤31🎉10🥰9
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሜሪካው “Global Traveller” መፅሔት ከመንገደኞች በሚያሰባስበው ድምፅ መሰረት በሚያበረክተው የእውቅና ሽልማት “የ2022 ዓ.ም ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።
https://bit.ly/3uO0uOF
https://bit.ly/3uO0uOF
👏98👍49❤13🎉12🥰2