Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቦይንግ ካምፓኒ አየር መንገዳችን የመጀመሪያውን ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን የተረከበበትን 10ኛ አመት በድምቀት አከበሩ። ላለፉት አስር አመታት አየር መንገዳችን ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላንን መካከለኛ እና ረጅም ርቀት ባላቸው መዳረሻዎቻችን ላይ በብቃት ያበረረ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን አውሮፕላን ተረክቦ በማብረር በአፍሪካ የመጀመሪያው እንዲሁም በአለም ደግሞ ሁለተኛው አየር መንገድ ነው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://bit.ly/3Vz3muX
👍437👏6
የአህጉራችን ትልቁ የልህቀት ማዕከል የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ በዛሬው ቀን በመልቲ ክሩ ፓይለት ፍቃድ ፕሮግራም እና በንግድ ፓይለት የስልጠና ፍቃድ መርሃ ግብር 236 ፓይለቶችን አስመርቋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍10565👏19🎉19🥰18
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሔደው "Aviators Africa Tower Awards 2022" በሶስት ዘርፎች ተሸላሚ ሆነ። እንዲሁም የአየር መንገዳችን የቦርድ ሊቀ መንበር አቶ ግርማ ዋቄ የ "Aviators Africa Hall of Fame 2022" ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራንስፖርት ትስስር ፣ በአቪዬሽን ስልጠና እና ሴቶችን በማብቃት ዘርፎች ተሸላሚ ሆኗል።
84👍67🎉9👏5🥰4