Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.7K subscribers
3.83K photos
144 videos
2 files
414 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ 45 % ድርሻ በዛምቢያ መንግስት ከሚተዳደረው “Industrial Development Corporation” ጋር የዛምቢያን ብሔራዊ አየር መንገድ አቋቁሞ ስራ ለማስጀመር ዝግጅት አጠናቅቋል። በጋራ የመስራት ስምምነቱን አስመልክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም “ስምምነቱ አየር መንገዳችን በ 2025 እቅዱ ያስቀመጠው በአፍሪካ በርካታ የአቪዬሽን ቢዝነስ ማዕከል የመፍጠር ስትራቴጂ አካል ነው” ብለዋል።
https://bit.ly/3pc8FAX
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ''ቢዝነስ ትራቭለርስ '' መጽሄት የሚያዘጋጀውን “የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች የአፍሪካ ምርጥ” አሸናፊ ሆነ ። አየር መንገዳችን ሽልማቱን ሊያገኝ የቻለው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያያዘ እየወሰዳቸው ያሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች ፣ ከጉዞ ትኬት ጋር በተገናኘ የሚሰጠው ፈጣን ምላሽ እንዲሁም በወረርሽኙ ወቅት ለተከሰቱ የጉዞ መስተጓጐሎች ለሰጠው የተቀላጠፈ የጉዞ ማስተካከያ አገልግሎት እና ተያያዥ መስፈርቶች በቢዝነስ መንገደኞች በመመረጡ ነው።
https://bit.ly/3pkNHQH
ከአውሮፕላን የበረራ ብቃትና አስተማማኝነት በስተጀርባ ያሉ ድንቅ የጥገና ባለሙያዎቻችን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍3
ከመላው አለም ወደ ኢትዮጵያ ለሚደረገው #ታላቅጉዞወደሐገርቤት እስከ 30% ቅናሽ ማዘጋጀታችንን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን።
ከአሁን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 11 2014 ዓ.ም ተመዝግበው ትኬትዎን ይግዙ ። ከታህሳስ 23 2014 ዓ.ም እስከ ጥር 23 2014 ዓ.ም ይጓዙ ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካር ትራውለር ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመንገደኞች የመኪና ኪራይ እና የማስተላለፊያ አገልግሎት ጀመረ። አገልግሎቱ ተጓዦች ተሽከርካሪዎችን ከሦስተኛ ወገን የመኪና አከራይ አቅራቢዎች እንዲከራዩ የሚያስችል ሲሆን ተጓዦች ከየትኛውም ሥፍራ ሆነው በአየር መንገዱ ድረ-ገጽ እና በሞባይል ስልክ መተግበሪያ አማካኝነት ቦታ ማስያዝ እንዲችሉ አገልግሎቱ በዲጅታል ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ተደርጓል።
https://bit.ly/3lIXX3U
ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
እለታዊ የበረራ አገልግሎት ወደ ሰመራ ከታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በመንገዳችን ሁሉ የላቀ ስኬት እያስመዘገቡ ማለፍ የሁል ግዜ ባህላችን ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የፈካ እና የደመቀ የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ትልቅ ያልሙ፤ በስኬት ከፍታ ይብረሩ!
#የኢትዮዽያአየርመንገድ
የአክብሮት ሰላምታችን ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል በያላችሁበት ይድረስ።
መልካም ቀን ይሁንልዎ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኦን ላይን ቼክ ኢን ማድረጊያ ኪዮስኮች የቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ታላቅጉዞወደሐገርቤት የትኬት ሽያጭ እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2014 መራዘሙን በደስታ ይገልጻል። ለበለጠ መረጃ ከስር ያለውን ማስፈንጠርያ ይጫኑ፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://www.ethiopianairlines.com/en-na/great-ethiopian-home-coming
በዓለማችን በሚበርባቸው አገራት ብዛት የ4ኛ ደረጃን የያዘ ግዙፍ አየር መንገድ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://insightsartist.com/largest-airlines-in-the-world-by-countries-served/
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) በፋርማሲዩቲካል ሎጅስቲክስ የገለልተኛ ገምጋሚ (CEIV Pharma) የልህቀት ማዕከልነት ሰርተፍኬት አገኘ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን ሰርተፍኬት በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ ነው፡፡ ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ።

https://bit.ly/3esbngF
ታዋቂዋ የሆሊውድ ተዋናይት ፣ኮሜድያንና ደራሲ Tiffany Haddish በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመብረሯ ኩራት ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ውበት እና ኩራት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው የካቲት ወር ጀምሮ ወደ በርበራ ሶማሌ ላንድ በረራ ይጀምራል።እርሶም ጉዞዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያድርጉ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍2